Category: ዒባዳ

Home የፈትዋ ገጽ
ሶላት ውስጥ ከፋቲሐ ጋር ድምፅን ከፍ አድርጎ “ቢስሚላሂር-ራሕማኒር-ረሒም” ማለት

ጥያቄ፡- ድምጽን ከፍ አድርጎ በሚሰገድባቸው ሶላቶች ውስጥ ፋቲሐን ስንቀራ ድምፅን ከፍ አድርጎ ቢስሚላሂ ማለት ግዴታ ነው? ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ የማያነባትን ሰው ተከትለን አንስገድ ወይስ ድምፅን ከፍ ማድረግም ሆነ ዝግ ማድረግ እኩል ነው? መልስ፡- በሶላት ውስጥ “ቢሰሚላሂን…” ከፍ ባለ ድምፅ ማንበብ (አል-ጃህር ቢበስመላህ) ዑለሞች የተለያዩበት ጉዳይ ነው። ሻፊዒዮቹ ድምፅን ከፍ ማድረግ ሱና ነው ብለው ያምናሉ። ሌሎች […]

በቀብር ወቅት ዱዐ ማድረግ

ጥያቄ:-  የሞተን ሰው የሚሸኙ ሰዎች ምን ያድርጉ? ድምፃችንን ከፍ አድርገን በህብረት ለሞተ ሰው ዱዐ ማድረግ እንችላለን?  መልስ:- ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- ከቀብር ስነስርዐት በኋላ ሸኚዎቹ በቀብሩ ላይ ቆይተው ለሟቹ ዱዐ ማድረግ ይወደድላቸዋል። ምክንያቱም አቡዳዉድና ሐኪም- በሶሒሕ ሰነድ- ከዑስማን ይዘው እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞተን ሰው ቀብረው ካገባደዱ በኋላ ቀብሩ ላይ በመቆም እንዲህ ይሉ ነበር:-  استغفروا […]

ከሴት ልጅ ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ብይን

ጥያቄ:- በእርግዝና ወራትም ሆነ በሌላ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ከሴት ልጅ ማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ብይኑ ምንድነው? ነጃሳ ነውን? ዉዱእ ማድረግን ያስገድዳልን? መልስ:- ሴት ልጅ በንጽሕና ጊዜያት አሊያም በእርግዝና ወቅት ልጅ በሚወጣበት በኩል የሚፈሳት ፈሳሽ ጠሃራ (ንፁህ) ነው። ደም የተቀላቀለበት ካልሆነ በስተቀር። ዉዱእ ያበላሻል የሚል ማስረጃም የለም። በሽንት መውጫ በኩል የሚወጣው ፈሳሽ ግን ከሽንት መጣራቀሚያ ፊኛ ጋር […]

ኃጢያተኛ ኢማም

ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል? መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው። የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡- ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው […]

የጀናዛ ሶላትን ለማስገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው

ጥያቄ:- የጀናዛ ሶላትን ለማሰገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው ማነው? የመስጂዱ ኢማም ወይስ የሟቹ የቅርብ ዘመድ? መልስ፡- ዑለሞች በሟች ላይ ሶላት ለማሰገድ እጅግ ተገቢው ሰው የትኛው ነው በሚለው ቅደም ተከተል ላይ ወጥ አቋም መያዝ አልቻሉም። ከፊሎቹ ጭቅጭቅና ዉዝግብን ለማስወገድ ሲባል ሥልጣኑ ያለው- ማለትም የሥልጣን ባለቤት የሆነው ክፍል እንዲያሰግድ፣ ኹጥባ እንዲያደርግና ለሌላም ነገር የወከለው መደነኛ ኢማም ነው ተገቢው […]

ከዘዋል (ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት) ጠጠር ስለመወርወር

ጥያቄ፡- የሐጅ ስነስርዐት ላይ- በተለይም ጠጠር በሚወረወርበት ወቅት ከፍተኛ ግፊያ እናስተውላለን። የተሸሪቅ ቀናት ላይ ጠጠርን ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት ጠጠር መወርወር እንችላለን? መልስ፡- የዙልሒጃ ወር አስራ አንደኛው፣ አስራ ሁለተኛው እና አስራ ሶስተኛው ቀን ወይም የተሸሪቅ ቀናት ተብለው በሚጠሩት ቀናት ላይ ጠጠር መወርወር የሚገባው ፀሀይ ወደ ምዕራብ ካጋደለች በኋላ ነው። ነገርግን አንዳንድ ዑለሞች ከፍተኛ ግፊያ የሚፈጠር […]

ኢሕራም ላይ ያለ ሰው ቀበቶ መታጠቅ ይችላል?

ጥያቄ፡- ገንዘብ እና ልዩልዩ መረጃዎቼን ለመያዝ እንዲመቸኝ የተሰፋ ቀበቶ መታጠቅ እችላለሁ? መልስ፡- ብዙ ሰዎች ኢሕራም ላይ ያለ ሰው የተሰፋ ልብስን በምንም መልኩ መልበስ እንደማይችል ያስባሉ። ነገርግን ጉዳዩ እንዲህ በጥቅሉ ሳይሆን ማብራሪያ ይፈልጋል። ኢሕራም ውስጥ ባለ ሰው ላይ እርም የሚሆነው ልብስ በአካላት ልክ የተሰፋ- እንደ ሱሪና እና እንደ ቀሚስ ያለ ልብስ- ነው። ክር የነካውን ልብስ ሁሉ እርም […]

ሐጅ ላይ ያለ ሰው በምን አይነት ስራ ይጠመድ?

ጥያቄ፡- በሐጅ ጊዜ ውስጥ ሐጀኛ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ስራዎች ምንድን ናቸው? መልስ፡- ታላቁ ዐሊም ዶክተር ዩሱፍ አል-ቀረዳዊ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡- “ሐጀኛ በሐጅ ጊዜው አላህን በማውሳት-በዚክር-፣ በዒባዳ፣ የአላህን ትዕዛዛት በመከወን እና ወደ አላህ የሚያቃርቡ በሆኑ በጎ ሥራዎች-በሶደቃ፣ ደካሞችን በማገዝ፣ እውቀት የሌላቸውን በማስተማር…- ራሱን መጥመድ ነው ያለበት። ባገኘው አጋጣሚ አብዝቶ ቁርኣንን ማንበብ ይወደድለታል። በቻለው አቅም ታላቁ መስጂድ (መስጂዱል-ሐረም) […]

የሴቶች ኢሕራም ፊትን መግለጥ የሆነበት ብይን እና ጥበብ

ጥያቄ፡- ኢሕራም ላይ ያለች ሴት ፊቷን መሸፈን ወይም ኒቃብ መልበስ እርም ይሆንባታል? ፊቷን ብትሸፍን ኃጢያተኛ ትሆናለች ማለት ነው? ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ሴት ኢሕራም ላይ ፊቷን እንድትገልጥ የታዘዘበት ጥበብ ምንድን ነው? መልስ፡- አብዝሃኞቹ ዑለሞች በኢሕራም ወቅት ሴት ፊቷን መሸፈን እርም እንደሚሆንባት ያምናሉ። ስለዚህ ኒቃብም ሆነ ጓንት አትለብስም። ምክንያቱም የሴት የኢሕራም መገለጫ ፊቷን መክፈቷ ነው። የሐዲስ ኢማሞቹ ቡኻሪይ፣ […]

ሐጅ ላይ ሁለት ኒያዎችን መሰብሰብ

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ጾም ሱና የሆነበትን ቀን ከአንድ በላይ በሆነ ኒያ ከጾመው ምንዳው በኒያው ልክ እንደሆነ አውቃለሁ። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ኢነመል አዕማሉ ቢኒያ” (ስራ ሁሉ የሚለካው በኒያ ነው) ብለዋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው፡- ሰውየው ግዴታ የሆነበትን ሐጅ በሑለት ኒያዎች መፈፀም ይችላል? ለምሳሌ አንዲትን ሐጅ ለራሱ እና ለአንድ ወላጁ ሊነይትባት ይችላል? አላህ ይስጥልኝ! መልስ፡- የአንድ ሰው ጫንቃ- […]