Category: ጾምና ኢዕቲካፍ

Home የፈትዋ ገጽ
መንገደኛ መቼ ነው የሚያፈጥረው?

ጥያቄ፡- ሰውየው ጉዞ ለመውጣት ከወሰነ በኋላ መቼ ነው ማፍጠር የሚፈቀድለት? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ሰማንያ አምስት ኪሎ ሜትር እና ከዚያ በላይ የሚጓዝ መንገደኛ በረመዷን የማፍጠር ፍቃድ አለው። ነገርግን በሌላ ጊዜ ያፈጠረውን ያካክሳል። በመንገደኛ ሰው ላይ የተገደቡ ህግጋት የሚጀምሩት መቼ ነው በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ዑለሞች የተለያየ ሀሳብ ሰንዝረዋል። የተሻለው ሃሳብ- ወላሁ […]

ኢፍጣርና የመግሪብ ሶላት፤ የቱን ላስቀድም?

ጥያቄ፡- የቱን እናስቀድም? ኢፍጣርን ወይስ የመግሪብን ሶላት?  ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ከመግሪብ ሶላት በፊት ትንሽ በመቅመስ ጾምን መፍታት ይበቃል ወይስ ሙሉ ምግብ መመገብ ይቻላል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በእሸት ተምርና በደረቅ ተምር ያፈጥሩ እንደነበር ተዘግቧል። ይህን ካላገኙ ግን በውሃ ያፈጥሩም ነበር። ጸሀይ መጥለቋን እንዳረጋገጡ ፊጥራቸውን ያቻኩሉ ነበር። ፊጥርን […]

ሱሑር በጾም ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ

ጥያቄ፡- ሱሑር መመገብ ግዴታ ነው? “ሱሑር ተመገቡ። ሱሑር መመገብ ውስጥ በረከት አለ።” የሚለው ሐዲስ ውስጥ በረክት/በረካ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ሱሑር ሱና ነው እንጂ ግዴታ አይደለም። ግዴታው ሰውየው በለሊት ከንጋት በፊት ኒያ አድርጎ ማደሩ ብቻ ነው። ኒያ በየዕለቱ መሆን አለበት ወይስ ለሙሉው ወር አንድ ኒያ ይበቃል […]

በረመዷን በቀን የፍትወት ፈሳሽን ማውጣት (ማስተርቤሽን)

ጥያቄ፡- በረመዷን በቀን ፍትወትን አውቆ ማፍሰስ እንዴት ይታያል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ጥያቄውን እንደሚከተለው እንመልሳለን፡፡ ፍትወትን ለማውጣት ብልትን በእጅ መነካካት የፍትወት ፈሳሽን እስካላወጣ -እንደ ሐነፊዮቹ እይታ- ጾምን አያፈርስም፡፡ በእጁ ሲነካካ ፍትወቱ የፈሰሰ ከሆነ ግን ጾሙ ይፈርሳል፡፡ ነገርግን ሰውየው ቀዷ መክፈል ብቻ ነው ግዴታ የሚሆንበት፡፡ ነገርግን ሰውየው ከዚህ ቆሻሻ ተግባር ሰውየው […]

ለይለቱል ቀድር

ጥያቄ፡ ያለሁበት ለሊት ለይለቱል ቀድር መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? ይህን የተከበረ ለሊት እንዴትስ ላሳልፍ? ሶላት በመስገድ ወይስ ቁርአን በመቅራት? መልስ፡ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሒም ለይለቱል ቀድርን (የውሳኔዋን ለሊት) ህያው ማድረግ እንደሚወደድ የሚጠቁሙ ብዙ ሐዲሶች ተዘግበዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- ”من قام رمضان إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه “ ”ومن قام ليلة القدر […]

እርጉዝ ሴት ፆም ማፍጠር ይፈቀድላታል?

ጥያቄ፡- እርጉዝ ሴት በረመዳን ውስጥ በቀን ማፍጠር ይፈቀድላታል? መልስ፡- ማፍጠር ይፈቀድላታል። ነገር ግን ከወለደችና ጥንካሬዋ ከተመለሰ በኋላ ቀዷ ማውጣት ግዴታ ይሆንባታል። ይህም ለተከታታይ ብዙ አመታት መፆም የማትችልበት ወሊድና ማጥባት ካልተከታተለባት ነው። ለተከታታይ አመታት ወሊድና ማጥባት ላይ ካሳለፈች ግን ላፈረሰችው እያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን (ደሀ) እየመገበች ታፈጥራለች። ከዚህ ውጭ ምንም የለባትም። አላህ የተሻለ ያውቃል!

የረመዷን አስተምህሮ ምንድን ነው?

ጥያቄ፡- በረመዷን ውስጥ ትኩረት የሚሰጣቸው አስተምህሮዎች ምንድን ናቸው? እነዚህን አስተምህሮዎችስ እንዴት ማስተላፍ ይቻላል? በተለይም እኔ የጀመዓ አሚር ነኝ… መልስ፡- የተከበርክ ወንድማችን ሆይ የረመዷን አስተምህሮዎች ብዙ ናቸው። ከነርሱ መሀል የተወሰኑትን እንጠቅስልህ፡- ረመዷን የተቅዋ ወር ነው። ስለዚህ ይህ ቃል (ተቅዋ) ለሚያካትታቸው ነገሮች ሁሉ ትኩረት ስጥ። ይህ ቃል የሚያካትታቸው ጥቅል ነገሮች ሁለት ናቸው። የአላህን ትእዛዝ መፈፀም እና ክልክሉን […]

በቀን ሚስትን መሳም ፆምን ያበላሻል?

ጥያቄ፡- ባል ሚስቱን መሳሙ ፆሙን ያበላሽበታል? መልስ፡- ቡኻሪ እና ሙስሊም እንዲሁም አስሐቡ ሱነን የተሰኙት የሀዲስ ዘጋቢዎች ዓኢሻ (ረ.ዓ) እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፡- كان رسول الله ـ صلى الله عليه وسلم ـ يُقَبل بعض أزواجه وهو صائم وكان أملكَكم لإِرْبِه “የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፆመኛ ሁነው ሚስቶቻቸውን ይስሙ ነበር። ታዲያ እርሳቸው ከማናችሁም በላይ ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር።” (ቡኻሪና ሙስሊም) […]

ግዴታ ፆም እያለበት ለሞተ ሠው ምን ይደረግ

ጥያቄ፡- አስሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱሁ። ባለቤቴ ባለፈው ዓመት በረመዷን ውስጥ ታሞ ነበር። ከዚያም ሞተ። ከረመዷን ያፈጠረባቸው (ያልፆመባቸው) ቀናትን ምን ላድርግለት? መልስ፡- ወዓለይኩሙስ-ሰላም ወረሕመቱሏሒ ወበረካቱሁ። ቢስሚላሂር ራህማኒር ረሂም የአላህ ድንጋጌዎች ከሠው ችሎታ (አቅም) ጋር የተመጣጠኑ ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡- “አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡” (አል-በቀራህ 2፣ 286) ፆም ከምግብና ከመጠጥ ታቅበን መቆየት በመቻል ላይ የሚመሰረት አምልኮ […]

ውሃ እየጠጣሁ አዛን አለ

ጥያቄ፡- “እያንዳንዳችሁ የውሀ እቃ በእጃችሁ ሆኖ (እየጠጣችሁ) አዛን ቢል የፍላጎታችሁን ሳትፈጽሙ አትተዉት።” የሚል ሐዲስ እንዳለ ሰምቻለሁ። የፈጅር አዛን መሀል አንድ ሙስሊም መብላቱን ባያቆም እንዴት ይታያል? ፆሙ ይበላሽ ይሆን? መልስ፡- ቢስሚላሂ ርራህማን አልረሂም ነገን እንደሚፆም የሚያስብ ሰው ፈጅር (ንጋት) ከመግባቱ በፊት ከመብላትና ከመጠጣት መታቀብ አለበት። ይህ የብዝሀ (ጁምሁር) ዑለሞች እምነት ነው። የተቀሰው ሐዲስ ደግሞ አቡ ዳዉድ […]