መላኢኮች /መላእክት/ (ክፍል 3)

0
2159

7. በምእመናን በተለይም የዒልም /እውቀት/ ሰዎች በሆኑት ላይ የአላህን እዝነት ስለማውረዳቸው

هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَكَانَ بِالْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا 

“እርሱ ያ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው። መላእክቶቹም (እንደዚሁ ምሕረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው)። ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል)። ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው።” (አል አህዛብ 33፤43)

ከአቢ ኡማማ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.):-

إن الله وملائكته وأهل السماوات والأرض ليصلون على معلم الناس الخير

“አላህ እና መላእክቶቹ የሰማይና የምድር ነዋሪዎች ሰውን መልካም ነገር በሚያስተምሩ ላይ እዝነት ያወርዳሉ።” ብለዋል። (ቲርሚዚ)

8. የዒልም ሰዎችን ማወደሣቸውና ለነሱ መተናነሣቸው

ከአቢ ደርዳእ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.):-

إن الملائكة لتضع أجنحتها لطالب العلم رضًا بما يصنع

“የተሠማራበትን ሥራ በመውደድ መላእክት ክንፎቻቸውን ለእውቀት ፈላጊ ተማሪ ይዘረጋሉ።” ብለዋል። (አቡ ዳዉድና ቲርሚዚ)

9. የብሥራት ዜና ስለመሸከማቸው

ሙስሊም ከአቡሁረይራ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ አሉ:-

إِنَّ رَجُلاً زَارَ أَخاً لَهُ فِى قَرْيَةٍ أُخْرَى، فَأَرْصَدَ اللَّهُ لَهُ عَلَى مَدْرَجَتِهِ مَلَكاً، فَلَمَّا أَتَى عَلَيْهِ، قَالَ: أَيْنَ تُرِيدُ ؟ قَالَ: أُرِيدُ أَخاً لِى فِى هَذِهِ الْقَرْيَةِ، قَالَ: هَلْ لَكَ عَلَيْهِ مِنْ نِعْمَةٍ تَرُبُّهَا ؟ قَالَ: لاَ، غَيْرَ أَنِّى أَحْبَبْتُهُ فِى اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ، قَالَ: فَإِنِّى رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكَ بِأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَبَّكَ كَمَا أَحْبَبْتَهُ فِيهِ

“አንድ ሰው በአንዲት መንደር ውስጥ የሚገኘውን ወንድሙን ለመጎብኘት ተነሣ። አላህም ወደዚያች መንደር በሚወስደው መንገድ ላይ መልአክ አስቀመጠ። ሰውዬው ሲደርስም መልአኩ ለሰውዬው ‘ወዴት እየሄድክ ነው’ አለው ‘በዚህች መንደር የሚገኝ አንድ ወንድሜ ጋ ነው’ አለው። ‘የዋለልህ ውለታ ኖሮ ነው ወይንስ’ በማለት መልአኩም ጠየቀው። ‘አይ አይደለም። ነገር ግን ለአላህ ብዬ ብቻ ስለወደድኩት ነው’ አለ ሰውዬው። መልአኩም ‘እኔ ወዳንተ የተላክሁ የአላህ መልእክተኛ ነኝ አላህ ለሱ ብለህ አንደወደድከው ወዶሃል።’ አለው።” (ሙስሊም)

10. አላህ የሚወዳቸውንና የሚጠላቸውን ሰዎች ስለማወጃቸው

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም እንዲህ አሉ:-

إِنَّ اللَّهَ إِذَا أَحَبَّ عَبْداً دَعَا جِبْرِيلَ فَقَالَ: إِنِّى أُحِبُّ فُلاَناً فَأَحِبَّهُ، قَالَ: فَيُحِبُّهُ جِبْرِيلُ، ثُمَّ يُنَادِى فِى السَّمَاءِ فَيَقُولُ: إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ فُلاَناً فَأَحِبُّوهُ، فَيُحِبُّهُ أَهْلُ السَّمَاءِ، قَالَ: ثُمَّ يُوضَعُ لَهُ الْقَبُولُ فِى الأَرْضِ.. وَإِذَا أَبْغَضَ عَبْداً دَعَا جِبْرِيلَ فَيَقُولُ: إِنِّى أُبْغِضُ فُلاَناً فَأَبْغِضْهُ، قَالَ: فَيُبْغِضُهُ جِبْرِيلُ، ثُمَّ يُنَادِى فِى أَهْلِ السَّمَاءِ: إِنَّ اللَّهَ يُبْغِضُ فُلاَناً فَأَبْغِضُوهُ، قَالَ: فَيُبْغِضُونَهُ، ثُمَّ تُوضَعُ لَهُ الْبَغْضَاءُ فِى الأَرْضِ

“አላህ አንድን ባሪያ የወደደ እንደሆነ ጅብሪልን ይጠራና ‘እኔ እገሌን እወደዋለሁና ውደደው’ ይለዋል። ጅብሪልም ይወደዋል በማስከተልም ‘አላህ እገሌን ይወዳልና ውደዱት’ በማለት በሰማይ ውስጥ ይጣራል። የሰማይ ነዋሪዎችም እገሌን ይወዱታል። በመሬት ውስጥም ተወዳጅነትን ያገኛል። አላህ አንድን ባሪያ የጠላ እንደሆነ ደግሞ ‘እኔ እገሌን እጠላዋለሁና ጥላው’ ይለዋል። ጅብሪልም ይጠላዋል። ሰማይ ነዋሪዎች ውስጥም ‘አላህ እገሌን ይጠላዋልና ጥሉት’ በማለት ይጣራል። የሰማይ ነዋሪዎችም ይጠሉታል በምድር ውስጥ እንዲጠላ ይሆናል።” (ሙስሊም)

11. ሥራዎችን መፃፋቸው

መላእክት የሰውን ልጅ ሥራ በጎም ይሁን እኩይ ይፅፋሉ። ጥሩና መጥፎውን ይመዘግባሉ። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ:-

وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ

“ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን። ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)። ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ።” (ቃፍ 50፤16-18)

وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ كِرَامًا كَاتِبِينَ يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ
 

“በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)። የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ።”(አል-ኢንፍጣር 82፤10-12)

أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُم بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ
 

“ወይም እኛ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ።” (አዝ ዙኽሩፍ 43፡79-80)

እነኚህንም ሥራዎች እነሱ ዘንድ ባለው መዝገብ ውስጥ ለያንዳንዱ ሰው ይመዘግባሉ። ከዚያም ለሰዎች ሥራዎቻቸው የምርመራ ቀን ይቀርቡላቸዋል። አላህም አንዲህ አለ

وَكُلَّ إِنسَانٍ أَلْزَمْنَاهُ طَائِرَهُ فِي عُنُقِهِ وَنُخْرِجُ لَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ كِتَابًا يَلْقَاهُ مَنشُورًا اقْرَأْ كِتَابَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ الْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًا
 

“ሰውንም ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ አስያዝነው። ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ኾኖ የሚያገኘው የኾነን መጽሐፍ እናወጣለታለን። ‘መጽሐፍህን አንብብ። ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ’ (ይባላል)።” (አል-ኢስራእ 17፤13-14)

ሰዎችም የትንሣኤ ቀን የገዛ ሥራቸው ሲቀርብላቸው ያሣለፉት በዱኒያ ላይ የሠሩት ጥሩም ይሁን በጎ ሥራቸውን እንዲያዩ ይደረጋል

وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ وَجَاءَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَّعَهَا سَائِقٌ وَشَهِيدٌ لَّقَدْ كُنتَ فِي غَفْلَةٍ مِّنْ هَٰذَا فَكَشَفْنَا عَنكَ غِطَاءَكَ فَبَصَرُكَ الْيَوْمَ حَدِيدٌ 

“በቀንዱም ውስጥ ይንነፋል። ያ (ቀን) የዛቻው (መፈጸሚያ) ቀን ነው። ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጂና መስካሪ ያለባት ኾና ትመጣለች። ‘ከዚህ ነገር በእርግጥ በዝንጋቴ ውስጥ ነበርክ። ሺፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ። ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው’ (ይባላል)።” (ቃፍ 50፤20-22)

12. ምእመናንን ማፅናት

ምእመናንን በውስጣቸው በሚሠማቸው ጥሩ ነገር ላይ ይፀኑና ይረጉ ዘንድ ያበረታቷቸዋል አላህ እንዲህ አለ:-

إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا 

“ጌታህ ወደ መላእክቱ ‘እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ’።” (አል-አንፋል 8፤12)

لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ أُولَٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ أُولَٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

“በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም። እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል። ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል። ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል። አላህ ከእነርሱ ወዷል። ከእርሱም ወደዋል። እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው። ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው።” (አል-ሙጃደላህ 58፤22)

13. ከነሱ መካከል የሰውን ልጅ ነፍስ ያወጡ ዘንድ የተወከሉ አሉ

حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ
 

“አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ (የሞት) መልእክተኞቻችን እነርሱ (ትእዛዛትን) የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል።” (አል-አንኣም 6፤ 61)

قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
 

“በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል። ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ በላቸው።” (አስ-ሰጅዳህ 32፤11)

14. ሩሃቸውን በሚያወጡበት ጊዜ መልካም ሰዎችን በጥሩ ሁኔታ አቀባበል ያስተናግዷቸዋል

الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

“እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት ‘ሰላም በእናንተ ላይ’ እያሉ የሚገድሏቸው ናቸው። ‘ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ’ (ይባላሉ)።” (አን-ነህል 16፤32)

15. በጀነትም ያበስሯቸዋል

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ نَحْنُ أَوْلِيَاؤُكُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ نُزُلًا مِّنْ غَفُورٍ رَّحِيمٍ 

“እነዚያ ‘ጌታችን አላህ ነው’ ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ ‘አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ’ በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ። ‘እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ። ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ። መሓሪ አዛኝ ከኾነው አላህ መስተንግዶ ሲኾን’ (ይባላሉ)።” (ፋሲለት 41፤ 30-32)

ይህንንም የሚያደርጉት እውነተኛ ኢማንን በአላህ ላመኑትና እሱ ለባሮቹ ባስቀመጠው መንገድ ላይም ለፀኑት ነው። መላኢኮች እነኚህ ዓይነቶቹ ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ ይወርዱና “ከፊት ለፊታችሁ ስላለው ነገር ማለትም ስለ ቀብርና ስለ መጨረሻው ቀን ሁኔታ አትፍሩ፤ ከኋላችሁም ትታችሁት ስለሄዳችሁት ስለ ንብረታችሁና ልጆቻቸችሁ ሀዘን አይግባችሁ፤ አላህ ቃል በገባለችሁ ጀነትም ደስ ይበላችሁ።” ይሏቸዋል። ለምእመናን እንዲህ ሲራሩ አመፀኞችን ግን እንደሚያሠቃዩና ከፊትን ከኋላም እንደሚደበድቧቸው ይታወቃል። አላህ እንዲህ አለ:-

إِنَّ الَّذِينَ تَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ ظَالِمِي أَنفُسِهِمْ قَالُوا فِيمَ كُنتُمْ 

“እነዚያ (ለእምንት ባለመሰደድ) ነፍሶቻቸውን በዳዮች ኾነው መላእክት (በበድር) የገደሉዋቸው (መላእክት ለነርሱ) ‘በምን ነገር ላይ ነበራችሁ?’ አሏቸው።” (አን-ኒሣእ 4፤97)

وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ

“እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ ‘የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ’ (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።” (አል-አንፋል 8፤50)

8. በመላእክት ማመን

በመንፈሣዊው ዓለምም ሆነ ባለንበት በተለመደው ተጨባጭ ዓለም የመላእክት በጎ ሚና በአጭሩ ከላይ የተጠቀሠው ከሆነና እንዲሁም በዚህ ዓለምም ሆነ በመጭው ዓለም ከሰዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ከታወቀ ተከታዩ ነጥብ በነሱ መኖር ማመን ግዴታ መሆኑን ነው። ከነሱ ጋር ነፍስን በማጥራት፣ ቀልብን በማፅዳትና አላህንም ፍራቻ በተሞላበት መልኩ በመገዛት ግንኙነት መፍጠር መሞከርም ያስፈልጋል።

ከመላእክት ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር ነፍስን ያመጥቃታል። አላህ የሰው ልጅን የፈጠረበትን ታላቅ ጥበብ ከግብ ለማድረስም ምክኒያት ይሆናል። ይህም የህይወትን አደራ መወጣት ጭምር ሲሆን በምድር ላይም ምትክ ሆኖ ማገልገልም ነው። ስለሆነም በመላእክት ማመን ከመልካም ነገር እንደሚመደብ ማወቅ ይኖርብናል። ለእውነተኝነትና የአላህ ፍራቻ መገለጫም ነው። አላህ እንዲህ አለ

وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ
 

“ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው” (አል-በቀራ 2፤177)

በዚህ መንፈሣዊ ዓለም ከጥርጣሬ ነፃ በሆነና ብዥታ ባልተቀላቀለበት መልኩ ካላመነ በስተቀር የአንድ ሰው እምነት እውነተኛ ሊሆን አይችልም።

ይህም የአማኞችና የነቢያት መንገድ ነው። እነሱም እውነት ግልጥ ብሎ በታያቸው ጊዜ ስለ ፍጥረተ ዓለሙ ሌሎች የተዘናጉበትንና ያልደረሱበትን ደርሰውበታል።

አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ አለ:-

آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ 

“መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ። ምእምኖቹም (እንደዚሁ)። ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ ‘በአንድም መካከል አንለይም’ (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ። ‘ሰማን፤ ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)። መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው’ አሉም፡:” (አል-በቀራህ 2፤285)

ይህ ድብቅና ሩቅ የሆነው የመላእክት ዓለም በመዳሠስም ሆነ በአዕምሮ በመሣል የሚደረስበት አይደለም። ሸይጧኖች ጭምር ሊደርሱበት አይችሉም

لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الْأَعْلَىٰ وَيُقْذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ
 

“ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም። ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል።” (አስ-ሷፋት 37፤8)

ድብቅ የሆነ ዓለም ነውና ይህን ከሰው ልጅ እይታ የራቀውን ዓለም ሁኔታ ማወቅ የሚቻለው በመለኮታዊው ራእይ ብቻ ነው።

قُلْ إِنَّمَا أَنَا مُنذِرٌ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ ﴿٦٥﴾ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الْعَزِيزُ الْغَفَّارُ ﴿٦٦﴾ قُلْ هُوَ نَبَأٌ عَظِيمٌ ﴿٦٧﴾ أَنتُمْ عَنْهُ مُعْرِضُونَ ﴿٦٨﴾ مَا كَانَ لِيَ مِنْ عِلْمٍ بِالْمَلَإِ الْأَعْلَىٰ إِذْ يَخْتَصِمُونَ ﴿٦٩﴾ إِن يُوحَىٰ إِلَيَّ إِلَّا أَنَّمَا أَنَا نَذِيرٌ مُّبِينٌ ﴿٧٠﴾

“እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ። ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም በላቸው። የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው። በላቸው እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው። እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ። (በአደም ነገር) በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት አልነበረኝም። ወደእኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝም (በል)።” (ሷድ 38፤65-70)

ይበልጥ ልናስብበት የሚገባው ጉዳይ ግን በነሱ ማመንና የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ባመላከቱን መሠረትም ተገቢ በሆነ መልኩ ከነሱ ጋር ወዳጅነታችንን ማጥበቅና ግንኙነታችንን ማጠናከር ነው። ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋልና

إن معكم من لا يفارقكم إلا عند الخلاء وعند الجماع، فاستحيوهم، وأكرموهم

“ከናንተ ጋር በምትፀዳዱበት ወቅት እና የግብረሥጋ ግንኙነት በምትፈፅሙበት ጊዜ ብቻ የሚለዩዋችሁ አሉ እፈሯቸው፤ አክብሯቸውም።”

* * * * *

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here