መላኢኮች /መላእክት/ (ክፍል 2)

0
3242

7.    ከተለመደው ዓለም ጋርም ሆነ ከሰው አንፃር ተግባራቸው

መላኢኮች በፍጥረተ ዓለሙ ውስጥ ነገሮችን በማነባበር ሥራ ላይ የተሠማሩ ናቸው። ከነኚህም መካከል ነፋስንና አየርን መላክ፣ ዳመናን በመሰብሰብ ዝናብ እንዲወርድና አዝመራ እንዲበቅል ማድረግ የመሣሰሉትንና ከሰው ልጅ እይታ ውጭ የሆኑና ሊዳሰሱ የማይችሉ ነገሮችን ያጠቃልላል።

መላኢኮች ህይወቱን በሙሉም ሆነ ከሞት በኋላ ሁሌም ከሰው ልጅ የማይነጠሉና አብረውት የሚሆኑ ፍጡራን ናቸው። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል

إن معكم من لا يفارقكم إلا عند الخلاء, وعند الجماع, فاستحيوهم وأكرموهم

“ከናንተ ጋር በምትፀዳዱበትና የግብረሥጋ ግንኙነት በምትፈፅሙበት ጊዜ ብቻ የሚለዩዋችሁ (መላእክት) አሉና እፈሯቸው፤ አክብሯቸው።”

1. ወደ እውነትና መልካም ነገር እንዲያዘነብሉ በማድረግ በሰው ውስጥ ያለውን መንፈሣዊ ሞራል ማነቃቃት

ከኢብኑ መስዑድ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)

إن للشيطان لمة بابن آدم, وللملك لمة, فـ أما لمة الشيطان, فإيعاد بالشر وتكذيب بالحق, وأما لمة الملك, فإيعاد بالخير وتصـديق بالحق فمن وجـد من ذلك شيئًا, فليعلم أنه من الله, وليحمد الله, ومن وجـد الأخـرى فليتعوذ من الشيطان.. ثم قرأ:

الشَّيْطَانُ يَعِدُكُمُ الْفَقْرَ وَيَأْمُرُكُمْ بِالْفَحْشَاءِ وَاللَّهُ يَعِدُكُمْ مَغْفِرَةً مِنْهُ وَفَضْلاً وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

“ለሰው ልጅ ለሸይጧን የሆነ ውስጣዊ ምልከታና ጥቆማ (ጉትጎታ) አለው። ለመልዓክም እንዲሁ ከውስጥ የሆነ መልካም ጥቆማና ምልከታ አለው። የሸይጧን ውስጣዊ ምልከታና ጥቆማ የሰው ልጅ መጥፎውን ነገር እንዲላመድና እውነትን እንዲያስዋሽ ማድረግ ነው። የመልአክ ውስጣዊ ምልከታና ጥቆማ ደግሞ የሰው ልጅ መልካም ነገርን እንዲላመድና እውነትን እንዲቀበል የሚያደርግ ነው። ከነኚህ (መልካም) ነገሮች አንድ ነገር ያገኘ ሰው ከአላህ መሆኑን ይወቅ፤ አላህንም ያመስግን። በተለየ መልኩ ያጋጠመው ግን ከሸይጧን በአላህ ይጠበቅ።አስከትለውም የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡ

“ሰይጣን (እንዳትለግሱ) ድኽነትን ያስፈራራችኋል። በመጥፎም ያዛችኋል። አላህም ከርሱ የኾነን ምሕረትና ችሮታን ይቀጥራችኋል። አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው።” (አል በቀራህ 2፤268)

2. መላእክት ለአማኞች ዱዓእ ያደርጋሉ

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከምህረቱ ስፋትና ባሮቹን ከመውደዱ የተነሣ ወደሱ ለሚመለሱ ሰዎች ምህረት እንዲያደርግና ከመልካም ባሮቹ ውስጥም ያስገባቸው ዘንድ በዱዓእ ወደሱ ተናንሰው ይለምኑ ዘንድ መላእክቱን ያዛቸዋል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ رَبَّنَا وَأَدْخِلْهُمْ جَنَّاتِ عَدْنٍ الَّتِي وَعَدتَّهُمْ وَمَن صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ وَقِهِمُ السَّيِّئَاتِ وَمَن تَقِ السَّيِّئَاتِ يَوْمَئِذٍ فَقَدْ رَحِمْتَهُ وَذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
 

“እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ። በእርሱም ያምናሉ። ‘ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል። ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው። የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው።’ እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ። ‘ጌታችን ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣ የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው። አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና። ከቅጣቶችም ጠብቃቸው። በዚያ ቀንም የምትጠብቃውን ሰው በእርግጥ አዘንክለት።’ ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው።” (ጋፍር 40፤7-9)

ሙስሊም እንደዘገቡት ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም:-

ما من يوم يصبح العباد فيه إلا وملكان يدعوان, يقول أحدهما: اللهم أعط ممسكًا تلفًا, ويقول الآخر: اللهم أعط منفقًا خلفًا

“አንድም ቀን የለም ባሮች ባነጉ ቁጥር ሁለት ዱዓእ የሚያደርጉ መላኢኮች ወርደው አንደኛው ‘አላህ ሆይ! የማይለግስ የሆነን ሰው አጥፋበት (አክሥረው)፤ ሌላኛው ደግሞ ‘አላህ ሆይ! የሚለግስን ሰው ተካለት የሚል ቢሆን እንጂ።’ ብለዋል” (ሙስሊም)

3. ከሰጋጆች ጋር አሚን ማለታቸው

መላኢኮች ከአማኞች ጋር “አሚን” ይላሉ። ከአቢ ሁረይራ እንደተዘገበው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.)

إذا قال الإمام:

غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلا الضَّالِّينَ

فقولوا: آمين, فإن الملائكة يقولون: آمين, وإن الإمام يقول: آمين, فمن وافق تـأمينه تـأمين الملائكة غفر له ما تقدم من ذنبه

ኢማሙ:-

  (በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ /ምራን፤ በሉ/ [አል-ፋቲሃ 1፤7 

ባለ ጊዜ እናንተ ‘አሚን’ በሉ፤ መላኢኮች ‘አሚን’ ይላሉ። ኢማሙም አሚን ይላል። የሱና የመላኢኮች ‘አሚን’ ማለት የተገጣጠመለት ሰው ከወንጀሉ ያለፈው ሁሉ ይማርለታል።’ ብለዋል” 

(አህመድ፣ አቡ ዳዉድና ነሳኢ

4. በየቀኑ በሱብሂና በዐስር ሠላት ላይ ስለመገኘታቸው

ቡኻሪይ ከአቡ ሁረይራ እንደዘገቡት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.):

فضل صلاة الجميع على صلاة الواحد خمس وعشرون درجة, وتجتمع ملائكة الليل وملائكة النهار فى صلاة الفجر يقول أبو هريرة رضى الله عنه: اقرءوا إن شئتم:

وَقُرْآنَ الْفَجْرِ إِنَّ قُرْآنَ الْفَجْرِ كَانَ مَشْهُوداً

የጀመዓ ሰላት በግል ከሚሰገደው ሰላት በሀያ አምስት ደረጃ ያህል ይበልጣል። የለሊትና የቀን መላኢካዎች የፈጅር ሰላት ላይ ይገናኛሉ። አቡሁረይራ አስከትለውም ከፈለጋችሁ:-

“የጎህ ሶላት /መላእክት/ የሚጣዱት ነውና” (አልኢስራእ [1778])

 የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አንብቡ አሉ። ” (ቡኻሪይ)

ቡኻሪና ሙስሊም ከአቢሁረይራ በዘገቡት ሌላ ሀዲስ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.):-

يتعاقبون فيكم ملائكة بالليل وملائكة بالنهار، ويجتمعون فى صلاة الفجر وصلاة العصر، ثم يعرج الذين باتوا فيكم، فيسـألهم ربهم وهو أعلم بهم: كيف تركتم عبادى ؟ فيقولون: تركناهم وهم يصلون، وأتيناهم وهم يصلون

“በናንተ ላይ የለሊትና የቀን መላኢኮች ይፈራረቃሉ። በሱብሂ እና በዐስር ሰላትም ይገናኛሉ። እናንተ ዘንድ ያደሩት ወደ ሰማይ ይወጣሉ። ጌታቸውም እያወቀ ‘ባሮቼን በምን ሁኔታ ላይ ነው ትታችሁ የመጣችሁት?’ በማለት ይጠይቃቸዋል። እነሱም ‘በመስገድ ላይ እያሉ ትተናቸው የመጣነው በመስገድ ላይ ሣሉም ተመለስንባቸው’ ይላሉ።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

5. ቁርኣን በሚቀራበት ወቅት የሚወርዱ መሆናቸው

መላእክት የተከበረው የአላህ ቁርኣን በሚነበብበት ወቅት ይወርዳሉ፤ ያዳምጣሉም።

ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ እንደተዘገበው:-

“ኡሰይድ ኢብኑ ሁደይር አንድ ቀን ምሽት በጎጆው ውስጥ ሆኖ ቁርኣን በማንበብ ላይ ሣለ ፈረሱ ደነበረች። ኡሰይድ ማንበቡን ቀጠለ። ፈረሷ አሁንም ደነበረች። ኡሰይድ ግን ማንበቡን ቀጠለ አሁንም ደነበረች። ኡሰይድ እንዲህ ይላል “የህያን ትረግጣለች ብዬ ስለፈራሁ ተነስቼ ወደዚያ ስሄድ ውስጡ ብርሃን ያዘለ ዳመና መሠል ነገር በላዬ ላይ ሲንሣፈፍ አየሁኝ። ቀጥሎም ከዐይኔ እስክትጠፋ ድረስ ወደ ሰማይ ወጣች። ከሰዓት በኋላ የአላህ መልእክተኛ ዘንድ ሄድኩና ትናንት ምሽት በጎጆዬ ውስጥ ሆኜ ቁርኣን በማንበብ ላይ ሣለሁ ፈረሴ ደነበረች።” አልኳቸው። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም “የኹደይር ልጅ ሆይ! አንብብ” አሉት። ኹደይርም “አነበብኩኝ” አለ። አሁንም ደነበረች። አነበብኩኝ አሁንም ደነበረች። የህያ በአቅራቢያው ስለነበር ትረግጠዋለች ብዬ በመስጋት ተነሣሁኝ። ከዚያም ብርሃን የያዘ ዳመና መሠል ነገር ከዐይኔ እስኪሠወር ድረስ ወደ ላይ ሲወጣ አየሁኝ። የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ. እንዲህ አሉ “እሷ መላኢካ ናት፤ እያዳመጠችህ ነበር። በቂርኣትህ ብትቀጥል ኖሮ ሰዎች ንጋት ላይ በግልፅና ምንም ሣይሸፍናቸው ያዩዋት ነበር’ አሉት።” (ጠበራኒ በደካማ ሀዲስ እንደዘገቡት)

6. በዚክር /አላህ በሚወሣባቸው/ ቦታዎች ላይ መገኘታቸው

መላኢኮች አላህ የሚወሣባቸውን ቦታዎች ያነፈንፋሉ። ይህንንም የሚያደርጉት እራሣቸውን በመንፈሣዊው ሀይል ለማበልፀግ ነው። ከአቢ ሁረይራ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል:-

إِنَّ لِلَّهِ مَلاَئِكَةً يَطُوفُونَ فِى الطُّرُقِ، يَلْتَمِسُونَ أَهْلَ الذِّكْرِ، فَإِذَا وَجَدُوا قَوْماً يَذْكُرُونَ اللَّهَ تَنَادَوْا هَلُمُّوا إِلَى حَاجَتِكُمْ، قَالَ: فَيَحُفُّونَهُمْ بِأَجْنِحَتِهِمْ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا. قَالَ: فَيَسْأَلُهُمْ رَبُّهُمْ وَهْوَ أَعْلَمُ مِنْهُمْ: مَا يَقُولُ عِبَادِى ؟ قَالُوا: يَقُولُونَ: يُسَبِّحُونَكَ، وَيُكَبِّرُونَكَ، وَيَحْمَدُونَكَ وَيُمَجِّدُونَكَ، قَالَ: فَيَقُولُ: هَلْ رَأَوْنِى ؟ قَالَ: فَيَقُولُونَ: لاَ وَاللَّهِ مَا رَأَوْكَ، قَالَ: فَيَقُولُ: وَكَيْفَ لَوْ رَأَوْنِى ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: لَوْ رَأَوْكَ كَانُوا أَشَدَّ لَكَ عِبَادَةً، وَأَشَدَّ لَكَ تَمْجِيداً، وَأَكْثَرَ لَكَ تَسْبِيحاً، قَالَ: يَقُولُ: فَمَا يَسْأَلُونِى ؟ قَالَ: يَسْأَلُونَكَ الْجَنَّةَ، قَالَ: يَقُولُ: وَهَلْ رَأَوْهَا ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: لاَ وَاللَّهِ يَا رَبِّ مَا رَأَوْهَا، قَالَ: يَقُولُ: فَكَيْفَ لَوْ أَنَّهُمْ رَأَوْهَا ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: لَوْ أَنَّهُمْ رَأَوْهَا كَانُوا أَشَدَّ عَلَيْهَا حِرْصاً، وَأَشَدَّ لَهَا طَلَباً، وَأَعْظَمَ فِيهَا رَغْبَةً، قَالَ: فَمِمَّ يَتَعَوَّذُونَ ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: مِنَ النَّارِ، قَالَ: يَقُولُ: وَهَلْ رَأَوْهَا ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: لاَ وَاللَّهِ مَا رَأَوْهَا، قَالَ: يَقُولُ: فَكَيْفَ لَوْ رَأَوْهَا ؟ قَالَ: يَقُولُونَ: لَوْ رَأَوْهَا كَانُوا أَشَدَّ مِنْهَا فِرَاراً، وَأَشَدَّ لَهَا مَخَافَةً، قَالَ: فَيَقُولُ: فَأُشْهِدُكُمْ أَنِّى قَدْ غَفَرْتُ لَهُمْ، قَالَ: يَقُولُ مَلَكٌ مِنَ الْمَلاَئِكَةِ: فِيهِمْ فُلاَنٌ لَيْسَ مِنْهُمْ إِنَّمَا جَاءَ لِحَاجَةٍ، قَالَ: هُمُ الْجُلَسَاءُ لاَ يَشْقَى بِهِمْ جَلِيسُهُمْ

“ለአላህ በየጎዳናዎች የሚዘዋወሩና ዚክር የሚያደርጉ /አላህን የሚያወሱ/ ሰዎችን የሚያፈላልጉ መላእክት አሉት። አላህን የሚያወሱ ሰዎችን ያገኙ እንደሆነ ይጠራሩና ‘ፍጠኑ ወደ ጉዳያችሁ!’ ይባባላሉ። እስከ ቅርቢቱ ሰማይ ድረስም ያካብቧቸዋል። ጌታቸው አላህም የሚያውቅ ሆኖ ሳለ ‘ባሮቼ ምን ይላሉ’ ይላቸዋል። እነሱም ‘ይቀድሱሃል፤ ያተልቁሃል፤ ያመስግኑሃል፤ ያከብሩሃል’ ይላሉ።

እሱም ‘አይተውኛል?’ ይላቸዋል። ‘ወላሂ አላዩህም’ ይሉታል።

‘ቢያዩኝ እንዴት ሊሆን ነው?’ ይላቸዋል። ቢያዩህማ ከዚህ በበለጠ መልኩ ይገዙህ ነበር። እጅግም ያከብሩህ በብዛትም ያወድሱህ ነበር።

‘ምንድነው የሚለምኑኝ?’ ይላቸዋል። ‘ጀነት ነው’ የሚለምኑህ ይላሉ።

‘አይተዋታል?’

‘አላዩዋትም ወላሂ ጌታችን ሆይ!’ ይሉታል።

‘ቢያዩዋትስ እንዴት ይሆን?’ ይላቸዋል።

‘ቢያዩዋትማ እሷን ለማግኘት በጣም ይጓጉ፤ በርትተው ይፈልጓትም እጅግም ይከጅሏት ነበር’ ይሉታል።

‘ከምንድነው ጥበቃ የሚፈልጉት?’ ይላቸዋል።

‘ከጀሀነም እሣት ነው ባንተ የሚጠበቁት’

‘አይተዋታል ?’ ይላቸዋል።

‘ወላሂ አላዩዋትም’

‘ቢያዩዋት እንዴት ይሆን?’ ይላቸዋል።

‘ቢያዩዋትማ እጅግ ይሸሹዋት እጅግም ይፈሯት ነበር’

እሱም ‘እናንተ መስካሪዎች ሁኑ እኔ ለነሱ ምህረት አድርጌያለሁ።’ ይላል።”

ከመላኢኮች የሆነ አንዱ መላኢካ ‘እገሌ የሚባል እኮ ከነሱ አይደለም። ለራሱ ጉዳይ ነው የመጣው። እሱም ‘ከነሱ የተቀማመጠ እድለ ቢስ አይሆንም’ ይላል።” (ቡኻሪይ)

በሌላ ዘገባ ደግሞ:-

إِنَّ لِلّهِ تَبَارَكَ وَتَعَالَى مَلاَئِكَةً سَيَّارَةً فُضْلاً يَتَبَّعُونَ مَجَالِسَ الذِّكْرِ، فَإِذَا وَجَدُوا مَجْلِساً فِيهِ ذِكْرٌ قَعَدُوا مَعَهُمْ، وَحَفَّ بَعْضُهُمْ بَعْضاً بِأَجْنِحَتِهِمْ حَتَّى يَمْلَئُوا مَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ السَّمَاءِ الدُّنْيَا، فَإِذَا تَفَرَّقُوا عَرَجُوا وَصَعِدُوا إِلَى السَّمَاءِ، قَالَ: فَيَسْأَلُهُمُ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ – وَهُوَ أَعْلَمُ بِهِمْ – مِنْ أَيْنَ جِئْتُمْ ؟ فَيَقُولُونَ: جِئْنَا مِنْ عِنْدِ عِبَادٍ لَكَ فِى الأَرْضِ، يُسَبِّحُونَكَ، وَيُكَبِّرُونَكَ، وَيُهَلِّلُونَكَ، وَيَحْمَدُونَكَ، وَيَسْأَلُونَكَ، قَالَ: وَمَاذَا يَسْأَلُونِى ؟ قَالُوا: يَسْأَلُونَكَ جَنَّتَكَ، قَالَ: وَهَلْ رَأَوْا جَنَّتِى ؟ قَالُوا: لاَ أَىْ رَبِّ، قَالَ: فَكَيْفَ لَوْ رَأَوْا جَنَّتِى ؟ قَالُوا: وَيَسْتَجِيرُونَكَ، قَالَ: وَمِمَّ يَسْتَجِيرُونَنِى ؟ قَالُوا: مِنْ نَارِكَ يَا رَبِّ، قَالَ: وَهَلْ رَأَوْا نَارِى ؟ قَالُوا: لاَ، قَالَ: فَكَيْفَ لَوْ رَأَوْا نَارِى ؟ قَالُوا: وَيَسْتَغْفِرُونَكَ، قَالَ: فَيَقُولُ: قَدْ غَفَرْتُ لَهُمْ فَأَعْطَيْتُهُمْ مَا سَأَلُوا وَأَجَرْتُهُمْ مِمَّا اسْتَجَارُوا، قَالَ: فَيَقُولُونَ: رَبِّ فِيهِمْ فُلاَنٌ عَبْدٌ خَطَّاءٌ إِنَّمَا مَرَّ فَجَلَسَ مَعَهُمْ، قَالَ: فَيَقُولُ: وَلَهُ غَفَرْتُ، هُمُ الْقَوْمُ لاَ يَشْقَى بِهِمْ جَلِيسُهُمْ

“የተከበረውና ላቅ ያለው ጌታ አላህ የሚወሣባቸውን ቦታዎች የሚያፈላልጉ የሆኑ ተንቀሣቃሽ መላኢኮች አሉ። አላህ የሚወሣበትን መጅሊስ ያገኙ እንደሆነ ከነሱ ጋር ይቀመጣሉ። በክንፎቻቸውም አንዱ ሌላኛውን በማካበብ በመካከላቸውና በቅርቢቱ ሰማይ ያለውን ይሞላሉ። በዚህ ሁኔታ ቆይተው ሲበታተኑ ወደ ሰማይ ይወጣሉ። የተላቀውና የተከበረው አላህ እያወቀ ይጠይቃቸዋል ‘ከየት ነው የመጣችሁት?’ በማለት። እነሱም ‘ባሮችህ ከሆኑት ከምድር ሰዎች ዘንድ ነው የመጣነው። ይቀድሱሃል /ሱብሃነላህ ይላሉ/ ፤ ያተልቁሃል /አላሁ አክበር ይላሉ/፤ ይሀልሉሃል /ላኢላሀ ኢለሏህ ይላሉ/፤ ያመሰግኑሃል /አልሀምዱሊላህ ይላሉ/፤ ይለምኑሃል’

‘ምንድነው የሚለምኑኝ?’ ይላቸዋል ‘ጀነት ነው የሚለምኑህ’ ይላሉ።

‘ጀነቴን አይተዋል?’ ይላቸዋል። ‘አላዩም ጌታችን ሆይ!’

‘ቢያዩ እንዴት ይሆን?’ ‘ቢያዩዋትማ ወዳንተ ይቀርባሉ ወዳንተ ይሸሻሉ’

‘ከምንድነው የሚሸሹት?’

‘ከእሣትህ ነው ጌታችን ሆይ!’

‘እሳቴን አይተዋል?’

‘አላዩም ጌታችን ሆይ!’

‘ቢያዩ እንዴት ይሆን!’

‘ቢያዩማ ካንተ ምህረትን ይጠይቃሉ።’

አላህም ‘ምሬያቸዋለሁ የጠየቁትንም ሠጥቼያቸዋለሁ ከተጠበቁትም ነገር ጠብቄያቸዋለሁ’ እነሱም ‘ጌታ ሆይ! ከመካከላቸው አንድ ጥፋተኛ የሆነ ባሪያ አለ በማለፍ ላይ ሣለ ነው ከነሱ ጋር ቁጭ ያለው።’

እሱም ‘እሱንም ምሬዋለሁ እነሱ ከነሱ ጋር የተቀማመጠ እድለ ቢስ የማይሆንባቸው ሰዎች ናቸውና።’ ይላል።” (ሙስሊም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here