አላህን መፍራት (ክፍል 2)

0
3411

አላህን መፍራት በአኺራ ፍሬዎቹ

1. በአርሽ ጥላ ስር መሆን፡- በዕለተ-ቂያማ የአርሽ ጥላ እንጂ ሌላ ጥላ በሌለበት ወቅት በዚሁ ጥላ ከሚጠለሉት ሰዎች መካከል ይሆናል

ورجل دعته امرأة ذات منصب وجمال فقال: إني أخاف الله

“አንድ ሰው አንዲት በዘሯ የተከበረችና ውበት ያላት ሴት ለብልግና ስትጠራው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለው ነው”

2. የወንጀል ምህረት ማግኛ ምክንያት ነው። ቡኻሪ በዘገበው ሐዲስ እንደተዘከረው

ففي حديث البخاري عن الرجل الذي جمع أبناءه عند موته سائلاً إياهم: “أي أب كنت لكم؟ قالوا: كنت خير أب. قال: فإني لم أعمل خيرًا قط فإذا أنا مت فحرقوني ثم اسحقوني فإذا صرت رمادًا فضعوني في قارورة ثم انتظروا فإذا كان يوم عاصف فذروا نصفي في البر ونصفي في اليم فلئن قدر الله علي ليعذبني عذابًا ما عذبه أحدًا من العالمين فلما مات فعلوا به ما أراد فقال الله له: كن، فكان رجلاً قائمًا فقال الله له: عبدي، ما حملك على ما صنعت؟ قال: خشيتك يا رب. قال الله تعالى له: قد غفرت لك

“አንድ ሠው ሞት ሲመጣው ልጆቹን ሰብስቦ ‘ለእናንተ ምን አይነት አባት ነበርኩ?’ አላቸው። እነሡም ‘ደግ አባት ነበርክ’ አሉት እሱም ‘እኔ በዕድሜዬ ምንም በጎ ስራ አልሰራሁም ስለሆነም ስሞት አቃጥሉኝ። ሠውነቴም ደቆ ወደ አመድነት ሲቀየርም በዕቃ አስቀምጡኝ። ከዚያም የተወሰነ ጠብቁና ዕለቱ ነፋሻማ ሲሆን ግማሹን ወደ የብስ፣ ግማሹን ወደ ባህር በትኑት። አላህ በእኔ ላይ ቻይ ከሆነ በዓለም ላይ ማንንም ቀጥቶት የማያውቀውን ቅጣት እኔን ይቀጣኛል’ አላቸው። አንደሞተም አባታቸው ያላቸውን ፈፀሙ። አላህም (በችሎታው) የተበተነውን አመድ እንደነበርክ ሁን ሲለው ሰውየው ወደነበረበት ተመለሰ። ከዚያም አላህ ‘ባሪያዬ ሆይ ይህን ለመስራት ምን አነሳሳህ?” አለው። እሱም ‘ጌታ ሆይ ይህን ያደረግኩት ላንተ ካለኝ ፍርሃት ነው’ አለ። አላህም ‘ለወንጀልህ ምህረት አድርጌልሀለሁ’ አለው።”

3. የጀነት መንገድ ነው፡- ረሡል (ሰ.ዐ.ወ)

من خاف أدلج ومن أدلج بلغ المنزل، ألا إن سلعة الله غالية، ألا إن سلعة الله الجنة) رواه الترمذي (

“የፈራ ሠው ይማልዳል፤ የማለደ ሠው ቤቱ ይደርሳል። ንቁ የአላህ ዕቃውድ ነች። የአላህ ዕቃ ጀነት ነች” (ቲርሚዚ)

4. ጀነትን መውረሻና ከእሳት መጠበቂያ ነው፡-

قَالُوا إِنَّا كُنَّا قَبْلُ فِي أَهْلِنَا مُشْفِقِينَ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذَابَ السَّمُومِ

“እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን” ይላሉ። “አላህም በእኛ ላይ ለገሰ። የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን።” (አጥ-ጡር 25፤26-27)

5. እጅግ በጣም አስደንጋጭም በሆነው ጊዜ ደህንነትን ማግኛ ነው። ቀደም ብለን እንደጠቀስነው አላህ ሁለት ፍርሃቶችንና ደህንነቶችን በአንድ ላይ አይሰበስብም።

አላህ መፍራት የዱንያ ፍሬዎች

1. ነፍስ ለቸርነት መነሳሳት፡-

إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنْكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا إِنَّا نَخَافُ مِنْ رَبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

“የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው። ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም። ‘እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤’ (ይላሉ)።” (አል-ኢንሳን 76፤9-10)።

2. አላህን መፍራት ጀግና ያደርጋል፡-

فِي بُيُوتٍ أَذِنَ اللَّهُ أَنْ تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ يُسَبِّحُ لَهُ فِيهَا بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ رِجَالٌ لَا تُلْهِيهِمْ تِجَارَةٌ وَلَا بَيْعٌ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ  يَخَافُونَ يَوْمًا تَتَقَلَّبُ فِيهِ الْقُلُوبُ وَالْأَبْصَارُ

“አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)። በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ። አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች (ያጠሩታል)።” (አን-ኑር 24፤36-37)

3. በምድር ላይ የበላይነትን መጎናጸፍ፡- ወዳጄ ሆይ! ሙስሊሙ ኡማ ራሱን የመምራት ዕድል እና በምድ ላይ ተመቻችቶ የመቀመጥ ሁኔታን አላገኘም። ይህን ማግኘት የሚችለው ደግሞ አላህን በመፍራትና በሁሉም እንቅስቃሴው ከአላህ ቁጣ ሲጠበቅ ነው።

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِرُسُلِهِمْ لَنُخْرِجَنَّكُمْ مِنْ أَرْضِنَا أَوْ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَا  فَأَوْحَىٰ إِلَيْهِمْ رَبُّهُمْ لَنُهْلِكَنَّ الظَّالِمِينَ وَلَنُسْكِنَنَّكُمُ الْأَرْضَ مِنْ بَعْدِهِمْ  ذَٰلِكَ لِمَنْ خَافَ مَقَامِي وَخَافَ وَعِيدِ

“እነዚያም የካዱት ለመልክተኞቻቸው ‘ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን፤ ወይም ወደ ሃይማኖታችን በእርግጥ ትመለሳላችሁ’ አሉ። ወደእነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ ‘ከሓዲዎችን በእርግጥ እናጠፋለን። ከእነሱም በኋላ ምድሪቱን በእርግጥ እናስቀምጣችኋለን። ይኸ በፊቴ መቆሙን ለሚፈራ ዛቻዬንም ለሚፈራ ሰው ነው’።” (ኢብራሂም 14፤13-14)

ህይወታቸውን ለእስልምና የሰጡ፣ ለአላህ ብለው ሀብታቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕትነት ያደረጉ፤ እነዚህ ሠዎች ከአላህ ቤት ያደጉ፣ አላህን የፈሩ፣ በቀጠሮው ቀን የተሳቀቁ ናቸው። እነዚህ ሠዎች ለሙስሊሙ ህብረተሰብ የድል መሳሪያ፣ ኡማው በጠላቱ ላይ የበላይነት እዲጎናጸፍ የሚሠውና መገለጫቸውም ጌታቸውን የሚፈሩ ናቸው።

ለቅሶ! … ለቅሶ!

አላህን ፈሪዎች አልቃሻዎች ናቸው። አንድ ጊዜ ዑቅበት ኢብኑ ዓሚር ረሡል /ሰ.ዐ.ወ/ “መድህን የሚገኘው እንዴት ነው?” ብሎ ሲጠይቃቸው:-

أمسك عليك لسانك، وليسعك بيتك وابك على خطيئتك

“ምላስህን ቆጥብ (ያዝ)፣ ቤትህ ይስፋህ፣ በወንጀልህ አልቅስ” ብለውታል።

በሌላ ዘገባም ረሡል (ሰ.ዐ.ወ)

لا يلج النار رجل بكى من خشية الله حتى يعود اللبن في الضرع

“የታለበ ወተት ወደ ጋት እንደማይመለስ ሁሉ ለኣላህ ብሎ ያለቀሰን ሠውም አላህ እሳት አያስገባውም” ብለዋል።

በሌላ ሐዲስም ረሡል እንዲህ ብለዋል

حرمت النار على عين دمعت أو بكت من خشية الله

“ዐይኑ እንባ ያፈሰሰች ወይም ያለቀሰች ሠው እሳቱ በእሱ ላይ እርም ናት“።

ጥያቄዎች

በመጨረሻም አንተ እውነተኛ አላህን ፈሪ ነህን? እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች ራስህን ጠይቅ።

1. “አላህ ሆይ ቀልብን እንደፈለክ የምታገለባብጣት የሆንክ፣ ቀልቤን በሐቁ አርጋት” የሚለውን ዱዓ ታበዛለህ?
2. አላህን በመፍራት ሐራም የሆነ ነገር ከመጠቀም ተቆጥበሀል?
3. ያለፈውንና የአሁኑን ወንጀል በማሰብ አላህን ትፈራለህ?
4. አንድ ቀን እንኳ አላህን ፈርተህ ራስህን ከወንጀል አቅበህ ታውቃለህ?
5. አላህን ስትታዘዘው አይቀበለኝም ብለህ ትሰጋለህ?
6. ከኢስላም ውጪ ሆነህ ሞት ያጋጥመኛል ብለህ ትፈራለህ?
7. ሞትን፣ የቀብርና የቂያማን ቅጣት ትፈራለህ?

ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽህ አዎ ከሆነ እንኳን ደስ ያለህ ላንተ ይህ ትልቅ ብስራት ነው። አላህን ከሚፈሩት ሷሊሆች ያስመድብሃልና። ለምን? ምክንያቱም

وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

“በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት።” (አር-ረሕማን 55፤46)

  • አላህ የሁለት አለም ፍርሀትን በአንድ ላይ አያደርግም።

አላህን በተገቢው መንገድ ያለመፍራት መገለጫዎች

ቀጥለው ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽህ “አዎ” ከሆነ አንተ አላህን እንደሚገባው እየፈራኸው ስላልሆነ ነፍስህን አሁኑኑ መርምር!

  1. አላህ መሃሪና አዛኝ ስለሆነ ሁሉንም ሠው ጀነት ያስገባል ብለህ ታምናለህ?
  2. ምንም እንኳ በዒባዳ ሰነፍ ብትሆን ጀነት እንደምትገባ ታስባለህ?
  3. ያለብህን ግዴታ በተገቢው መንገድ እየተወጣሁነኝ ብለህ ታምናለህ?
  4. አላህ እንዲቀጣህ የሚያደርግ ወንጀል አልሰራሁም ብለህ ታስባለህ?
  5. ከአላህ ይልቅ ሠዎችን የበለጠ ትፈራለህ?
  6. ሠዎች ወይም ጅኒዎች ጥቅምን ወይም ጉዳትን የማምጣትንና የማራቅ ችሎታ አላቸው ብለህ ታስባለህ?
  7. ርሃብን፣ ደህንነትና በሽታን ትፈራለህን?
  8. በመጨረሻህ አለማማርና በቀብር ቅጣት ላይ የተግራራ አቋም ነው ያለህ?

ውድ ወንድሜ እስኪ እራስህን አላህን በመፍራት ጉዳይ የት እንዳለህ ፈትሽ። በዚህ ላይ ያለህ ጥንካሬ ነው የምትሰራው ስራ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድረው። በትእዛዙ ላይ እንድትበረታ ከእዝነቱ ተስፋ እንዳትቆርጥ የሚያደርግህ ይኸው ፍራቻ ነው።

ከጉድለቶች የጠራውና ልቅና የተገባው የመልካም ስምና ባሀሪ ባለቤት የሆነው አላህ እሱን ከሚፈሩት ባሮቹ ያደርገን ዘንድ እማጸነዋለሁ። እንዲሁም ይቅርታውን የሚፈልግ፣ ምንዳውን የሚቋምጥና በእዝነቱ ተስፋ የሚያሳድር የሆነን ፍርሃት እንዲሰጠን አላህን እጠይቀዋለሁ። አለህ በጉዳዩ ላይ የበለጠ ቻይ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here