7. ግብርና
ሙስሊም ሳይንቲስቶች በርካታ የተክል ዓይነቶችን ገልፀዋል። በ 12ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የኖረው አል-አዋም 585 የተክል ዓይነቶችን የጠቀሰ ሲሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎች እንዴት እንደ ሚዘሩም ትንተና ሰጥቷል። አንዳንድ ምሁራን ጥናታቸውን ያካሄዱት ወደሐጅ በሚያደርጉት ረዥም ጉዞ ነበር። በዚህ በኩል አቡል ሀሰን አልነባቲ ተጠቃሽ ነው።
በተግባራዊ ዘርፍ፣ የመስኖ ሥራን አሳድገዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተጠቅመዋል፣ እንዲሁም የከብት እርባታን አሻሽለዋል። ለምእራቡ ዓለም ኮክን፣ ጥጥን፣ ሩዝን፣ ሙዝን፣ እና የሸንኮራ አገዳን ያስተዋወቁት ሙስሊሞች ናቸው።
በኢሰላማዊት እሰፔን አሳን ለምግብነት የሚያረቡ ሠው ሰራሽ ሀይቆች የተለመዱ ነበሩ።[1]
8. ኢንዱስትሪ
በጨርቅ (ሀር፣ ጥጥ እና ሱፍ)፣ በቆዳ፣ በጠርሙስና ብረት ማምረት ላይ ከፍተኛ የሆነ ማሻሻያ አድረገዋል። መድሀኒቶችንና ሽቶዎችን በመሥራት ኬሚስትሪን ተግባር ላይ አውሏል። ለመማር ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ ባግዳድ ውስጥ በ794 ተቋቁሟል። ሪም (Ream)[2] የሚለው ቃል ሪዝማ ከሚለው የአረብኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም ጥቅል ማለት ነው።[3]
9. ንግድ
አንዳንድ የታሪክ ፀሃፍት እንዳስቀመጡት ከሆነ በሙስሊሞች የአገዛዝ ዘመን በአንድ ጊዜ እስከ 850 የሚደርሱ ሳራሴን መርከቦች (Saracen ship) ባካንቶን ወደብ /ቻይና/ ይቆሙ ነበር። በንግድ /trade & commerce/ የተፃፉ ቀደምት መጽሐፍት እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ይመለሳሉ። በንግድ ዙሪያ ከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ መጽሐፍት ተጽፈዋል።
ከሚል ካስቶሪና እንዳሉት ጥቂት የሳራሴን ሳንቲም በእስካንዲኒቪያን ተገኝቷል። ከወርቅ የተሠራ የአንግሎ ሳክስን ሳንቲም፤ በአንደኛው ፊት የንጉስ አፋ ሮክስን ስም የያዘ እና በጀርባው ደግሞ የሙስሊሞችን ሸሀዳ የያዘ ነበር። የቼክስ (cheques)[4] ስርአት የብድር ፎርም ሥነ-ፅሁፍ ጭምር አገልገሎት ላይ ውለው ነበር።[5]
10. ታሪክ
ታሪክን በተመለከተ አብዛኞቹ ሙስሊም የታሪክ አጥኚዎች ትኩረታቸው የነበረው እውነታንና መረጃን በመሰብሰብና በማቅረብ ላይ ቢሆንም አንዳንዶቹ ጥልቅ አስተያየት (critical judgment) መስጠትን እና በስተኋላ በአውሮፖዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ አቀራረቦችን ተጠቅመዋል።
ታዋቂ ከነበሩ የታሪክ አጥኚዎች መካከለ አልጠበሪ (9ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) በጣም ድንቅ የሆኑ ዓለማቀፋዊ ገድሎችን ፅፏል። አል-መስዑዲ 20 ትላልቅ ቅፆች ያሉት መፅሀፍ በጠፉ ታሪኮች ዙሪያ የፃፈ ሲሆን “ሙረጅ አልዘሀብ” /Golden pastures/ የሚለው ስራው አሁንም ድረስ የተጠበቀ ነው። ኢብን አል አልሲር (13ኛው ክፍለ ዘመን) እስከሱ ዘመን ጊዜ ድረስ ያሉትን አለማቀፋዊ ገድሎች ፅፏል።[6]
11. ሥነ ጥበብና ሥነ-ህንፃ
ምንም አንኳን በዚህ ዙሪያ ሙስሊሙ ያለው ቅርስ፣ በሙስሊሙ አስተዳደር ስር ከወደቁ በርካታ የተለያዩ ባህሎች የተወሰደ በመሆኑ፣ የተለያየ ቢሆንም በውስጡ ግን ከእስልምና አስተምህሮት ጋር የተያያዘ የአንድነት ባህሪ አለው። የዚህ ዓይነቱ ቅርስ ጥሩው ክፍል 1258 በሞንጎሎች ወድሟል። ከዚህ አደጋ የተረፈ ፍርስራሽ በስፔን በተለይም በአልሀምብራና ኮርዶቫ መስጂዶች ቀርቷል።
የሙስሊሙ ሥነ-ህንፃ እና የእጅ ፅሁፍ ጥበብ ተፅዕኖ እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ በፑይ የሚገኘው ካቴድራል አንዱ በር በአረብኛ /ማሻአላህ/ በሚል ፅሁፍ ያጌጠ ነው። በርግጥም ሞሳይክ የሚባለው ኢስላማዊ የአፃፃፍ ስታይል /ዘዴ/ ፈረንሳይ አውቬርጅ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አገልግሎት ላይ ውሏል። በብሪታኒያ በሚገኘው ሙዝየም ውስጥ በ9ኛው ክፍለ ዘመን የተሠራ የአይሪሽ መስቀል ሲኖር ይህም መስቀል በመሀሉ ቢስሚላህ /በአላህ ስም/ በሚል የዓረበኛ ፅሁፍ ተውቧል።[7]
12. ሌሎች የትምህርት ዘርፎች
ከላይ ከተጠቀሱት የትምህርት ዘርፎች የሙስሊሞች አስተዋፅኦ አለባቸው። በተጨማሪ ሌሎች እኩል ጠቀሜታ ያላቸው የትምህርት ዘርፎች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ የፖለቲካ ሳይንስ እና sociology (ሶሺዎሎጂን)[8] እንደ ምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። በ 10ኛው ክፍለ ዘመን አልፋራቢ ስለ አርአያ ከተማ /Model city/ እንዲህ በማለት ፅፏል። “በሚገባ የተቀናጀ ግዛት ማለት ለዜጎቹ ትክክለኛ አገዛዝና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ደስታን ያጐናፀፈው ነው።”
የአል-መዊርዲ “አል-አህካም አልሱልጣኒያህ” /የሥልጣን አገዛዝ/ መጽሐፍ የተሻለ ተግባራዊ ሥራ ተደርጐ ይወሰዳል። ይህም በ 10ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻና በ 11ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ እንደፃፈ ይነገራል።
ታዋቂው የሙስሊም ሶሺዎሉጂስት ኢብን-ኸልዱን /1332-1406/ የሁሉም ጊዜ ታላቅ ሶሺዎሎጂስት ተደርጎ ይወሰዳል። የታሪክን ፍልስፍና በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ ሰፋ አድርጎ የፃፈ የመጀመሪያው ሰው ነው።
ዘመናዊ ሶሺዎሎጂ ከመጀመሩ እጅግ ቀድሞ ኢብን ኸልዱን የማህበረሰብን ሥነ-ተፈጥሮ ዝግመተ ለውጥ በማጥናት፣ በዚህ ጥናት ላይ በመመስረት ስለታሪክ ሂደት ገለፃ ሰጥቷል። “አልሙቀዲማ” በሚለው መፅሀፉ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታሪክን ነፀብራቅ፣ የተለያዩ የስልጣኔ አይነቶችን፣ ማህበሰባዊ ተቋማትን ማየት ይችላል።
13. የጠፋ ወይም የተንኳሰሰ ቅርስ
አለመታደል ሆኖ አብዛኞቹ የበለፀጉና ግዙፍ የሙስሊም ምሁራን ስራዎች ጠፍተዋል፤ አልያም በሙስሊሙ አለም ላይ በተደረጉ ድንገተኛ ጥቃቶች ፈራርሰዋል። ሞንጐሎች የቲግሪስ ወንዝን በመፅሀፍቶች በመደልደል ድልድይ ሰርተውባቸዋል። ይህም የወንዙን ቀለም ለረዥም ጊዜ ቀይሮት ቆይቷል።
የመስቀል ጦረኞች ሶሪያን በያዙት ወቅት ወደ 3 ሚሎዮን መፅሀፍትን አጥፍተዋል። ሙስሊሞች በስፔን /ግራናዳ/ በተሸነፋበት ወቅት ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ መፅሀፍት እንዲቃጠሉ ተደርገዋል። ይህም የሆነው በአጥባቂ ሀይማኖተኞች መሪነት በአንደ ቀን ውስጥ ነው። የሲሲሊው ካርዲናል ዚሞንስ /15ኛው ክፍለ ዘመን/ ከ50,000 በላይ በአረብኛ የተፉ መፅሀፈትን በፍራንዳ ከተማ ዋና አደባባይ ላይ እንዲቃጠሉ አድርጓል።[9]
ሆን ብለው ሙስሊሙ ያደረገውን አስተዋፅኦ ለመደበቅ ጥረት ለሚያደርጉ የታሪክ አጥኚዎች ምንም አይነት ይቅርታ አይገባቸውም። አንዳንድ ጊዜም እነዚህን የሙስሊሙ አስተዋፅኦት የአውሮፓዊያን ሳይንቲስቶች ከብዙ ክፍለ ዘመን በኋላ የተወለደ እንደሆነ አድርጐ ሲያቀርቡት ቆይተዋል። ነገር ግን ፍትሀዊ የሆኑ አውሮፖዊያን ፀሀፍትም አይጠፉም።
ከነሡም መካከል ጆን ድራፐር አንዱ ሲሆን እንዲህ ሲል ተናግሯል። “የአውሮፖ ፀሃፍቶች ሳይንሳዊ ሀላፊነታችንን ወደ ኋላ ብለን መሀመዳዊያን ለሳይንስ ያደረጉትን አስተዋፅኦ ከእይታ ለማውጣት የምናደርገውን ጥረት በተመለከተ የተሰማኝን ቅሬታ ልገልፅ እፈልጋለሁ። በርግጥ እነዚህ ስራዎች ብዙም ሊደበቁ አይችሉም። በሀይማኖት ጥላቻና ብሄራዊ /ዜጋን/ በማታለል ላይ የተመሰረተ ኢ-ፍትሀዊነት እድሜልክ የሚቆይ አይደለም።”[10]
ማጠቃለያ
ከዚህ ጥልቅ ጥናት በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃና በተግባራዊ ደረጃ ሁለት ድምዳሜዎች ላይ መድረስ እንችላለን። በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ እስልምና ሁሉን አቀፍና የተሟላ ከፈጣሪ የሆነ የሕይወት መመሪያ ነው። በሐይማኖትና በቁሳዊ (ዓለማዊ) ሕይወት መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት አይፈጥርም። አስተምህሮውም የሰው ልጅ መንፈሳዊ ስጋዊና አእምሮ ያለው ማሰብና ማስተንተን የሚችል (intellectual) በመሆኑም በዚሁ ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል። እስልምና በነዚህ ሦስት ክፍሎች መሀከል መሰረታዊ የሆነ መጋጨትና አለመስማማት አለ ብሎ አያምንም።
ይህ ሰፊ አቀራረብ እስልምና በትምህርት በሳይንስና በሚዛናዊ የሰው ልጅ እድገት (progress) ላይ ባለው አመለካከት ይንጸባረቃል:: ቁርአን ሰዎችን በተደጋጋሚ አላህ ለሰዎች የፈጠራቸውን ፀጋዎች እንዲያስተነትኑ እንዲማሩ እንዲመለከቱ እንዲመራመሩ እንዲያስሱ ይጋብዛል። ምክንያቱም እነዚህ አላህ የሰው ልጅ በምድር ላይ የተቀበለው የተተኪነት (ኸሊፋነት) ኃላፊነት ከግብ እንዲያደርስ ስለሚረዱት ነው።
በታሪካዊና ተግባራዊ ደረጃ እየበለፀገ የመጣው ስልጣኔ የዓለምን ሳይንስና ትምህርት ለ600 ዓመታት ያህል ተቆጣጥሮ በቆየው ኢስላማዊ አስተምህሮ ተንፀባርቋል። ይህም ለአውሮፓውያን ማንሰራራት (renaissance) መንገዱን ጠርጓል። ይህ ወሳኝ አስተዋጽኦ ባይኖር ኖሮ ዘመናዊው የሳይንስና የቴክኖሎጂ እድገት አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ አሁን በደረሰበት ፍጥነት ባልደረሰ ነበር።
ይህ በቁርአን የተቀሰቀሰው ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎት የሚገጥመው በመቻቻል ብቻ ሲሆን ይህም መቻቻል እውቅና የሚሰጠውና የሚያበረታታው ሙስሊም ምሁሮችን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ጭምር የዘር ግንድን ወይም ሐይማኖትን ሳይመርጥ ነው። ዓለም እንዲህ ዓይነቱን ሁሉንም ለመጥቀም የተነሳ አንፀባራቂ የመቻቻል የለውጥ ትብብር ምሳሌ አይቶ አያውቅም።
በሰዎች ላይ በስህተት መገኘታቸው (ሊገኙ መቻላቸው) እና የሰዎች ጎዶሎነት መጠቆሙ እርግጥ ነው። ይህም በመላዕክቶች ዓለም ብዙም አይጠብቅም። ነገር ግን ዋናው ጥያቄ ምንጊዜም ቢሆን የሚከተለው ነው።
በመብረቅ ብልጭታ ፍጥነት ለማድረግ የቻለውና የውስጥ ችግርና የውጭ ወረራ ሳይበግረው የኢስላማዊ ስልጣኔ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ ያስቻለው ተአምራዊ ኃይል ምንድን ነው? መልሱም ቁርአን ነው። ነገር ግን አንድ ጥያቄ ሳይመለስ ይቀራል። እሱም የኢስላም አስተምህሮ ይህ ከሆነ እና እነዚህም አስተምሮዎች ለብዙ ክፍለ ዘመናት ተግባር ላይ ሲውሉ ከነበረ ለምንድነው ታዲያ ይህ የሙስሊሙ ስልጣኔ አውሮፓዎች ከጨለማው ዘመን (Dark Age) ሲነቁ እየደከመ የመጣው? ለምንድነው የዛሬ ሙስሊሞች ከሌሎች ወደኋላ የቀሩት ታዲያ ይህ የድክመት መገለጫ አይሆንምን?
እርግጥ ነው ይህ የድክመት መገለጫ ነው:: ነገር ግን ይህ ድክመት የሙስሊሙ እንጂ የኢስላም (የአላህ ቀጥተኛ መንገድ) አይደለም። ምንም እንኳን ውጫዊ ችግሮችና ወረራዎች ለዚህ መከሰት እንደምክንያት ቢገለፅም ለሙስሊሙ መውደቅ ዋናው መንስኤ ግን የሙስሊሙ የውስጥ ችግርና በእምነቱ ላይ የነበራቸው ቆራጥነት መድከሙ ነው።
የተዋጣለት ስልጣኔ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች (ባህሪያት) ያስፈልጉታል።
- መለኮታዊ መመሪያ፡- ይህም መለኮታዊ መመሪያ ጠንካራ መሰረትን የሚሰጠው የሚያበረታና አውታር የሚሆነው ለእድገቱ አቅጣጫ የሚያስይዘው እንዲሁም በስነ-ምግባር ዙሪያ አስፈላጊውን ሁሉ የሚያሟላለት ነው።
- በሁለተኛ ደረጃ ምናባዊ (የተዋጣለት) ስልጣኔ የሚያስፈልገው ጠንካራ የስራ ፈጠራና ታታሪነት (የህልምን እንጀራ ባለፈ ድል መኮፈስ ሳይሆን) ናቸው።
መለኮታዊ መመሪያ የሌለው ስልጣኔ በጠንካራ ሥራ ምክንያት ሊበለፅግ ይችላል። ቢሆንም የእምነት ስነ-ምግባር ጠንካራ መሠረት አለመኖሩ የአእምሮ መረበሽንና በሂደትም ውድቀትን ያስከትላል። በጨረቃ ላይ ዘለን እንድንወጣ ሊያደርገን ይችላል። ነገር ግን በምድር ላይ እያነከስን መሄዳችንን ለመተው አይረዳንም። በተመሳሳይ ሁኔታ በመሠረታዊ እሳቤዎች ላይ በአፍ እየደለለ ኃላፊነትን ለመተግበር ያልቻለ ስልጣኔ በህግጋቶች ድክመት ሳይንስ ህግጋቶቹን መተግበር ባለመቻል ሊወድቅ ይችላል።
ሙስሊሞች ከሌሎች ጋር በመጣመር ወደ ማያልቀው የጥንካሬ ምንጭ ወደፊት መጓዝ ቢችሉ ታሪክ እራሱን በመድገም ሁሉንም የሚጠቅም የተሻለ ዓለም መገንባት ይቻላል። “ጨረቃ ላይ ዘለን እንደወጣን ምድር ላይም ለመዝለል እንችል ይሆናል”
– ተፈፀመ –