የቁርዓን ክፍፍሎች

0
5823

“አያ” እና “ሱራ”

አያ (በብዙ ቁጥር አያት) ጥሬ ትርጉሙ ተዓምር ማለት ሲሆን በቁርዓን አጠቃቀም የቁርዓን አጭሩ ክፍልን ማለትም አረፍተ ነገር ወይም ሀረግ ይገልፃል።

የቁርኣን ራዕይ ከአምላክ ለሰው ልጆች የተላከ መመሪያ በመሆኑ ይህ ትንሹ ክፍል አያ ወይንም ተዓምራዊ (መመሪያ) መባሉ የሚያስገርም አይደለም። ቁርኣን ግጥም ባለመሆኑ ይህን ክፍል ለመግለፅ “verse” ወይም በአማርኛ አንቀፅ የሚለውን ቃል መጠቀሙ አግባብነት አይኖረውም።

“ሱራ” (ብዙ ቁጥር ሲሆን ሱዎር) የቃል በቃል ትርጉሙ መስመር፣ አጥር ወዘተ እንደማለት ሲሆን በቁርኣን አጠቃቀም ከኋላው እና ከፊቱ ለፊቱ ካሉት ምንባቦች የተለየ የቁርዓን ክፍል ማለትም ምዕራፍ ማለት ነው።

በቁርኣን ውስጥ 114 ሱራዎች ሲገኙ፣ አጭሩ ሱራ 4 አያዎች ሲኖረው ረጅሙ ደግሞ 286 አያዎችን አቅፏል፡፡

ከምዕራፍ 9 ውጭ ያሉት የቁርዓን ምዕራፎች በሙሉ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም (በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው) ብለው የሚጀምሩ ሲሆን ይህም ኋላ ላይ የተጨመረ ሳይሆን ነብዩ ሙሃምደ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይ ሳይሆኑ ጭምር ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነው። (ለበለጠ መረጃ ምዕራፍ 27፣30 ን ይመልከቱ)

ሁሉም የቁርዓን ምዕራፎች እንደ ርዕስ የሚያገለግሏቸው ስሞች አሏቸው፡፡ ስያሜዎቹ በአብዛኛው ምዕራፉ ውሰጥ ካሉ በጣም አስፈላጊ ወይም ልዩ የሆነ ቃላት (ምሳሌ አል-በቀራ አል-አንፋል) የተወሰዱ ሲሆን አልፎ አልፎ ምዕራፉ ከሚጀምርባቸው የመጀመሪያ ጥቂት ቃላት መካከል በአንዱ ሊሰየሙ ይችላሉ (ለምሳሌ ሱረቱ ጦሀ፣ አል-ፉርቃን)፡፡

ቅደም ተከተል እና አወቃቀር

በአንድ ምዕራፍ ውስጥ ያሉት አያዎች ሆነ የሱራዎች ቅደም ተከተል የተወሰነው መላዕኩ ጅብሪል ቁርዓንን ሁለት ጊዜ ከነብዩ ጋር በተናበበት እና ነብዩ በሞቱበት አመት በመላዕኩ ጅብሪል መሪነት በራሳቸው በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አማካኝነት ነው።

የሙስሊም ሙሁራን የቁርዓን ሱራዎችን በአራት አይነትም ከፍለዋቸዋል።

  • አጥ-ጢዋል         (ረጃጅሞች)፡ 2-10 (ከአል-በቀራ እስከ ዩኑስ)
  • አል-ሚያዑን        (መቶ ያክል አያዎች ያሏቸው)፡ 10-35
  • አል-መሳኒ          (ከመቶ ያነሱ አያዎች ያሏቸው)፡ 36-49
  • አል-ሙፋሰል       (ከ ቃፍ ምዕራፍ ጀምሮ ያለው የመጨረሻው ቁርዓን ክፍል)፡ 50-114

ሌሎች የቁርዓን ክፍሎች

ጁዝዕ፡- ጁዝዕ (ብዙ ሲሆን አጅዛእ) የቃል በቃል ትርጉሙ ክፍል፣ ድርሻ እንደማለት ነው። በየወሩ በተለይ ደግሞ በረመዷን ወር በየሌሊቱ አንዳንድ ጁዝዕ ለማንበብ ይመች ዘንድ ቁርዓን ከሞላ ጎደል እኩል ርዝማኔ ባላቸው 30 ክፍሎች (ጁዝኦች) የተከፈለ ነው። ጁዝዖች ሁልጊዜ ጁዝዕ በሚለው ቃል እና በተሰጣቸው ቁጥር ይገለፃሉ። ለምሳሌ 30ኛው ጁዝዕ የሚጀምረው በሱራ 78 (አን-ነባእ) ነው፡፡

ሩኩዕ፡- አንዳንድ የቁርዓን ቅጅዎች ሱራዎችን ሩኩዕ ወደሚባሉ አንቀፆች ይክፍሏቸዋል። አንቀፆቹ እነሱን በሚወክል ምልክት እና ከምልክቱ ጋር አብሮ በሚፃፉ አረበኛ ቁጥሮች ይገለፃሉ። ለምሳሌ 2፡13፡2

  • የመጨረሻው ቁጥር (2) በተጠቀሰው ምዕራፍ (በአሁኑ ምሳሌ አል-በቀራ) ሁለተኛው ሩኩዕ መሆኑን ያመለክታል
  • መካከል ላይ ያለው ቁጥር (13) የተጠናቀቀው ሩኩዕ 13 አያዎች እንዳሉት ያመለክታል
  • መጀመሪያ ላይ ያለው ቁጥር(2) በተጠቀሰው ጁዝዕ (በዚህ ምሳሌ የመጀመሪያው ጁዝዕ) ሁለኛው ሩኩዕ መሆኑን ያሳያል።

ሂዝብ፡- በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የታተሙ የቁርዓን ቅጅዎች እያንዳንዱን ጁዝዕ በምልክት ወደሚገለፁ አራት “ሂዝብ” ይክፍሉታል። ለምሳሌ 2፡74 በ2 ቁጥር የተመለከተው የሁለተኛው የቁርዓን ሂዝብ መጀመሪያ ነው።

እያንዳንዱ ሂዝብ እንደገና ከዚህ በታች በተመለከተው ሁኔታ ወደ አራት ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል፡፡

  • የሂዝቡ የመጀመሪያው ¼ ክፍል XXX
  • የሂዝቡ ግማሽ ½ ክፍል XXX
  • የሂዝቡ ሶስተኛው ¾ ክፍል XXX

መንዚል፡- ቁርኣን በየሰባት ቀን ለመቅራት ያመች ዘንድ መንዚል ወደሚባሉ ሰባት ከሞላ ጎደል እኩል የሆኑ ክፍሎች ይከፈላል። በአንዳንድ የቁርኣን ቅጅዎች ላይ መንዚል በሚለው ቃል እና ክፍሉን በሚወክሉ ቁጥሮች ይገለፃሉ። ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ ቁርኣን ወደ ጁዝዕ እና መንዚል እንዴት እነደተከፈለ ያሳያል።

መንዚል

ጁዝዕ

ሱራ

1

1

1፤1

2

2፤142

3

2፤253

4

3፤92 ወይም 93

5

4፤24

6

4፤148

2

6

5፤1

7

5፤82 ወይም 83

8

6፤111

9

7፤88

9

7፤286

10

8፤41

11

9፤93 ወይም 94

3

11

10፤1

12

11፤6

13

12፤53

13

13፤15

14

15፤1 ወይም 2

14

16፤50

4

15

17፤1

15

17፤109

16

18፤75

16

19፤58

17

21፤1

17

22፤18

17

22፤77

18

23፤1

19

25፤21

19

25፤60

5

19

27፤1

19

27፤26

20

27፤56 ወይም 60

21

29፤45 ወይም 46

21

32፤15

22

33፤31

6

22

35፤1

23

36፤22 ወይም 28

23

38፤24 ወይም 25

24

39፤32

24

41፤38

25

41፤47

26

46፤1

7

26

50፤1

27

51፤31

27

53፤62

28

58፤1

29

67፤1

30

78፤1

30

84፤21

30

96፤19

በቀታዳ አገላለፅ የተለያዩ መንዚሎች መጨረሻቸው 4፤76, 8፤36, 15፤49, 23፤118, 34፤54, 49፤18 እና 114፤6 ናቸው። [ኢብን አቢ ዳውድ ገፅ 118]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here