ሙስሊም መሆን፡ ሙስሊም ከባለቤቱ ጋር (ክፍል 2)

2
9651

ስኬታማ ባል

እናም ሙስሊም ባል በቤተሰብ ሕይወቱ ከየትኛውም አባወራ የበለጠስኬታማ ነው። ራሳቸውን ለሚጠብቁ ደግ ሴቶችም ይበልጥ ተወዳጅነው። ሚስቱን እንዴት መያዝ፣ እንዴት ማዝናናት፣ እንዴት ማስደሰትእንዳለበት ያውቃል። ኢስላም ወደሚሻው ሕይወት በብስለትና በጥንቃቄይመራታል።

ዝንባሌዋን ያውቃል። ፍላጎቷን ይረዳል። ባህሪዋን ጠልቆ ይገነዘባል። ስነልቦናዊ አወቃቀሯን ለአፍታ እንኳ ሳይዘነጋ ይህን ሁሉ ይፈጽማል።

ብልህና ጥንቁቅ

ሙስሊም ከባለቤቱ ፊት ምንጊዜም ብልህና ጥንቁቅ ነው። ዘመዶቿን በክፉ አይነካም። ዘሯን አያነውርም። ወገኖቿንአይሰድብም። ስሜቷን ይጠብቃል። ውስጧን የሚያቆስል ቃል ስለነርሱ አይናገርም።

እርሷም እንዲሁ የርሱን ስሜት ትጠብቃለች። ዘመዶቹን በክፉ አታነሳም። ውስጡን በቃላት አታቆስልም።

የነገረችውን ሚስጥር አደባባይ አይበትንም። በእንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ቸልተኛ መሆን በባልና በሚስት መካከልየውዝግብ ጎመራ ያስነሳል። የፍቅር ነበልባልንም ያጠፋል። ጥንቁቅና ብልህ አባወራ ከዚህ ሁሉ ራሱን ይጠብቃል።በኢስላማዊው አደብ ራሱን እስከጠበቀና እስከመራ ድረስ ከእንዲህ ዓይነት ችግር ውስጥ አይወድቅም።

ጉድለቷን ይሞላል

ጥንቁቅና ብልህ ሙስሊም ባል የሚስቱን ጉድለት ይሞላል። የእውቀት ወይም የስነ ምግባር ጉድለት ካየባት በስልትናበጥንቃቄ ያስተካክላታል። በመሐሉ የአፈንጋጭነትና የአመጽ ችግር ቢገጥመው እንኳ በዘዴ ይመልሳታል።

ከሰው ፊት አይተቻትም። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን። ሴትን ልጅ ክፉኛ ከሚጎዱ ነገሮች አንዱ ነውሯን ሌሎችእንዲሰሙ ማድረግ ነው። ብልህ ሙስሊም ከእንዲህ ዓይነቱ ነገር ራሱን ይጠብቃል።

እናት እና ሚስት

ብልህ ሙስሊም አባወራ የእናቱንና የሚስቱን ፍላጎት እንዴት ማጣጣም እንደሚችል ያውቅበታል። እናም ሁለቱንምበብልሐት ያስተናግዳል። ግዴታዎቹን በብስለት ይወጣል። ሚስቱን ለማስደሰት እናቱን አያስቀይምም። የእናቱን መብትለመጠበቅ ሚስቱን አያስቀይምም።

የእናቱን መብቶችና ወሰኖችን ያውቃል። እርሱን እስከመጨረሻው ይወጣል። የሚስቱን መብትና ገደቡን ያውቃል። በዚህበኩልም ስኬታማ ክንዉን ያደርጋል። ለሌላ  ሰው ተቃራኒ መስለው የሚታዩ ነገሮች እነሱን አይከብዱትም። የተውባስንቅ፣ የኢስላማዊ ስነ ምግባር ስንቅ እስካለው ድረስ፣ ባህሪውን በኢስላም መንገድ እስከገራ ድረስ ይህን ማከናወንአይገደውም። ለሁሉም የየድርሻቸውን ይሰጣል። ሁሉንም በትክክለኛ ቦታቸው ያስቀምጣል።

መምራትና ማስተዳደር

ሙስሊም አባወራ ከላይ በሰፈረው የመጠቀ ባህሪና ስነ ምግባር የሚስቱን ቀልብ ይቆጣጠራል። እናም ትእዛዙንአትጥስም። ለዚህም ነው ቤቱን የመምራት ሐላፊነት ለርሱ የተሰጠው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا أَنفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ

“ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው። አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው።” (አል ኒሣእ፤ 34)

ይህን ሐላፊነት አለመወጣት የሚያስከትለው ነገር አለ። ተጠያቂነትም አለበት። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-

ሁላችሁም ኃላፊነት አለባችሁ። በሐላፊነታችሁም ትጠየቃላችሁ። መሪ ሐላፊነት አለበት። በሐላፊነቱም ይጠየቅበታል። አባወራ በቤተሰቡ ላይ ሐላፊነት አለበት። በሐላፊነቱም ይጠየቅበታል። ሴትም በባሏ ቤት ሐላፊነት አለባት። በሐላፊነቷም ትጠየቅበታለች። አገልጋይ በጌታው ገንዘብ ሐላፊነት አለበት። በሐላፊነቱም ይጠየቅበታል። ሁላችሁም ሐላፊነት አለባችሁ። በሐላፊነታችሁም ትጠየቁበታላችሁ።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

በእያንዳንዱ ሙስሊም ትከሻ ላይ ያለ ኃላፊነት። ሁሉም ሐላፊነትን፣ ይጋራል። ከዚህ ነጻ ሆኖ የምታገኘው ግለሰብየለም። ምክንያቱም በኢስላም እይታ ሕይወት ቁም ነገር ናት። ተግባር እና እነጻ ናት። ቀልድና ጨዋታ አይደለችም።

ኢስላም ለሴት ልጅ የላቀ ደረጃ እነደሰጣት ሁሉ በሕይወት ውስጥ ሚናዋን እንድትረዳም አድርጓታል። ተልእኮዋንበትክክል ትወጣ ዘንድ ሸሪዓው ያሰመረላትን ወሰን መጠበቅ ይኖርባታል። በሸሪዓዊ መርሆዎች ስትመራ ለወንድ ልጅአጋር፣ የጥሩ ትውልድ መፍለቂያ ትሆናለች። ቤቷንም የሐሴት ምንጭ ታደርጋለች።

ወንድን ሚስቱን እንዲንከባከብ ያዘዘው ኢስላም እርሷንም በተፈቀደ ነገር እስካዘዛት ድረስ እንድትታዘዘው ግድአድርጎባታል። በዚህ ረገድ ጥብቅ ትእዛዛት ተላልፈዋል። የሚከተለው የአላህ መልእክተኛ ቃል ክብደቱን ያሳያል፡-

“አንድ ሰው ለሌላው እንዲሰግድ የማዝ ብሆን ኖሮ ሴት ልጅ ለባሏ እንድትሰግድ ባዘዝኳት ነበር።”

የባልን መደሰት ጀነት ለመግባት መስፈርት አድርጎላታል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህብለዋል፡-

“ባሏ በርሷ የተደሰተ ሆኖ የሞተች ሴት ጀነት ገባች።” (ኢብን ማጃህ)

ከባሏ ትእዛዝ ያመጸችን ሴት ደግሞ ከአመጽዋ እስክትመለስ ድረስ መላኢካ እንደሚረግማት መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አስጠንቅቀዋል፡-

“አንዲት ሴት የባሏን ፍራሽ ተለይታ  ደረች እስኪነጋ ድረስ መላኢኮች ይረግሟታል። (ቡኻሪና ሙስሊም)

ኢስላም የባልን መሪነት እና ሐላፊነት ለማጽናት ካለው ፍላጎት የተነሳ ሴት ልጅ ከረመዷን ወር ውጭ ባሉት ጊዜያትያለርሱ ፈቃድ እንዳትጾም ግድ አድርጓል። እንግዳንም ያለ ፈቃዱ እንዳትቀበል ግድ አድርጓል።

“አንዲት ሴት ባሏ በአገር እያለ ያለ ፈቃዱ ልትጾም አይፈቀድላትም። ያለ ፈቃዱም ከቤቱ ውስጥ ለማንም አትፍቀድ።”

ባል ቤተሰቡን ወደ ሰላም መስክ ይመራ ዘንድ ኢስላም የሐላፊነትን ቦታ ሰጥቶታል። ወንዶች በእንስት ውበት ተታለውወኔያቸው እንዳይላሽቅ፣ ውስጣቸው እንዳይዳከም፣ እንዳይልፈሰፈሱም አስጠንቅቋል። ሴት ልጅ መንገድ ስትስት ፍቅሯአማሎት ከማስተካከል መልፈስፈስ የለበትም። እንዲህ ዓይነቱን ባህሪ የሚያሳዩ ወንዶች የመሪነት  ልጓሙን ከእጃቸውያፈተልካል። ከዚያ በኋላ የሚስትን አመጽና መንገድ መሳት የሚመልሱበት ብልሐትና ጉልበት አይኖራቸውም። የአላህመልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህን ሁኔታ በተከታዮቻቸው ላይ ከሚደርሱ ፈተናዎች ሁሉ የከፋው ማድረጋቸውእውነት ብለዋል፡-

“ከኔ ሕልፈት በኋላ ለወንዶች ከሴት ልጅ የበለጠ ፈተና አልተውኩም።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ሙስሊም ወንድ በሴት ልጅ ውበት ማሎ ሚዛን አይስትም። የቱም ያህል ቢማርከውና ቢያማልለውም። የአላህ ፍቅርከርሷ ፍቅር እንደሚበልጥበት በትህትና ይነግራታል፤ በለዘብታ ያስረዳታል እንጅ። ባል ለሚስቱ የሚኖረው ፍቅር የቱንያህል ቢገዝፍና ቢመጥቅ ከአላህ ፍቅር በታች ነው።

قُلْ إِن كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ وَجِهَادٍ فِي سَبِيلِهِ فَتَرَبَّصُوا حَتَّىٰ يَأْتِيَ اللَّهُ بِأَمْرِهِ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ

“«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ» በላቸው። አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አይመራም።” (አል ተውባ፤ 24)

እናም ሙስሊሞች ነን በሚሉ በርካታ ሰዎች ቤቶች ውስጥ የምናየው የእንስቶች አፈንጋጭነት በትክክለኛ ሙስሊምቤት ውስጥ ፈጽሞ አይስተዋልም።

ሚስቱ፣ እንስት ልጆቹ፣ እህቶቹ እና ቤተሰቦቹ መንገድ ላይ ተራቁተውና ለብሰው ግን እርቃናቸውን ሆነው እያየ በዝምታየሚያልፍ፣ ይህን ሁኔታ ለመቀየር ምንም ዓይነት ጥረት የማያደርግ ሙስሊም በእርግጥም የወንድነት ወኔውን አጥቷል።እስልምናውን ከስሯል። የአላህን ቁጣ ሸምቷል። ከዚህ ውድቀት ሊታደገው የሚችለው ሕሊናውን የሚያነቃ፣ የወንድነትስሜቱን የሚቀሰቅስና ወደቀጥተኛው ጎዳና የሚመራ ንጹህና ትክክለኛ ተውባ ብቻ ነው።

ኢስላም ለሴት ልጅ አደብ አድርጎላታል። የተለየ አለባበስ ደንግጎላታል። ከባእድ ወንድ ፊት እንዴትና በምን ሁኔታእንደምትለብስ ስርዓት አብጅቶላታል። ይህ ስርዓት ኢስላማዊ የሴቶች አለባበስ (ሒጃብ) ስርዓት በመባል ይታወቃል።

ከኢስላም የጠራ ምንጭ እየተጎነጨች፣ ወተቱን እየተመገበች፣ አየሩን እየተነፈሰች ያደገች ሙስሊም እንስት ሒጃብንበደስታ ነው የምትቀበለው። ምክንያቱም የአላህ ዲን፣ የአላህ ትእዛዝ እንጅ አንዳንድ ከንቱዎች እንደሚሉት ወንዶችበትምክህተኝነት በርሷ ላይ የጫኑት ሸክም ወይም የነርሱ የንቀትና የጭቆና መገለጫ ወይም የኋላቀርነት ተምሳሌትአይደለም። ቡኻሪ አኢሻን ጠቅሰው እንዲህ ማለቷን ዘግበዋል፡-

“የሙሐጅር እንስቶችን አላህ ይዘንላቸው። “ጉፍታወቻቸውን ከደረቶቻቸው ላይ ያጣፉ።” የሚለው የቁርአን አንቀጽበወረደ ጊዜ መቀነቶቻቸውን እየቀደዱ በርሱ ተከናነቡ።”

በሌላ የቡኻሪ ዘገባ እንደተመለከተው “ሽርጦቻቸውን እየቀደዱ በርሱ ጉፍታ አደረጉ።” ብላለች።

ሶፍያ ባስተላለፈችው ሌላ ዘገባ እንዲህ ብላለች፡-

ከአኢሻ ጋር እያለን የቁረይሽ እንስቶችንና ልቅናቸውን አወሳን። አኢሻ እንዲህ አለች፡- የቁረይሽ እንስቶች ልቅና አላቸው።ግና በአላህ እምላለሁ፣ እንደ አንሷሮች ጥልቅ እምነት እና ልቅና ያለው አላየሁም። “ጉፍቶቻቸውን ከደረቶቻቸው ላይያጣፉ።” የሚለው የቁርአን አንቀጽ በወረደ ጊዜ ወንዶች ወደየቤቶቻቸው እየሄዱ አላህ ስለነርሱ ያወረደውን መልእክትነገሯቸው። ለእያንዳንዱ የቤተሰባቸው አባል የአንቀጹን መልእክት አነበቡ። እናም እንስቶች በአላህ መጽሐፍ ውስጥየሰፈረውን መልእክት በማመን እና በመተግበር መቀነታቸውን እያወጡ በርሱ ተጠቀለሉ። ጠዋት ከአላህ መልእክተኛሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጀርባ ሲሰግዱ ሁሉም ተመሳስለው ልክ ከአናቶቻቸው ላይ ቁራ የሰፈረባቸው ይመስሉ ነበር።

የአንሷር ሴቶች በእርግጥም አላህ ይዘንላቸው። እምነታቸው ጠንካራ ነበር። እስልምናቸው እውነተኛ ነበር። የአላህንየነብዩን ትእዛዝ ወዲያውኑ የመተግበር ፍጥነታቸው ድንቅ ነበር። እያንዳንዷ ሙስሊም እንስት የአንሷሮችን አርአያነትልትከተል ይገባታል። የኢስላምን የተለየ አለባበስም ልትይዝ ይገባታል። በዙሪያዋ ያለው መራቆት ደንታ ሳይሰጣት ይህንታድርግ።

አንዲት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ አስታወስኩ። በእምነቷና በዲኗ ያላት መተማመን የአንሷር ሴቶችን ጥንካሬ ያስታውሰኛል።ዩኒቨርሲቲውን የጎበኘ አንድ ጋዜጠኛ ስለ ሒጃቧና በበጋ የጸሐይ ወራት ስለሚያስከትልባት ሙቀት ጠየቃት። “የጀሃነምእሣት ይበልጥ አቃጣይ ነው።” አለችው።

በእንዲህ ዓይነት ንጹህና ብጹእ ሙስሊም እንስቶች ቤቶች ይደምቃሉ። ትውልድ ይታነጻል። ሕብረተሰቡም ገንቢ በሆኑጀግኖች ልጆች ያሸበርቃል። አሁን አሁን እንዲህ ዓይነት እንስቶች እየበዙ መጥተዋል። አላህ የተመሰገነ ይሁን።

እውነተኛ ሙስሊም ቤተሰቡን አይዘነጋም። እንስቶቹን እውነተኛ ኢስላማዊ ስነ ስርዓት ያስይዛቸዋል። አደቡን እንዲከተሉያደርጋቸዋል። ሚስቱ፣ ልጆቹ እህቶቹ። የሙስሊም እንስት መለያ የሆነውን ኢስላማዊ ሂጃብ ይለብሳሉ። ሚስት ይህንንስርዓት ለመከተል ስታምጽ፣ አይሆንም ብላ ስታሸንፈው፣ እርሱም ሊጫናት ጉልበት ሲያንሰው፣ ያኔ የርሱ ሐይማኖትጉዳይ ገደል ገባ። ዲናዊ ስብእናው አከተመለት።

ባል በሚስቱ ላይ ያለበት ሐላፊነት ውጫዊ ገጽታዋን በማስተካከል ብቻ የሚወሰን አይደለም። አምልኮም ሌላየሕይወት ክፍሏን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።

ኢባዳ ላይ ስትሰንፍ ወይም የአላህን ትእዛዝ ስትጥስ እና ወንጀል ስትሰራ ካያት ሊያቅባት ሐላፊነት አለበት። ስነ ምግባሯእንዲስተካከል፣ ባህሪዋ እንዲገራ፣ ሐላፊነቶቿን በአግባቡ እንድትወጣ የማድረግ ሐላፊነት አለበት። በዚህ ረገድየሚያሳየው መሳነፍ የባልነትና የወንድነት ወኔውን የሚያሟሽሽ ይሆናል። እስልምናውን ያጎድላል። ከአላህ ዘንድ ያለውንልቅና ይቀንሳል። ይህም የሆነው አላህ ሴትን ልጅ ከወንድ ልጅ አደራ ስር ስላስቀመጣት ነው። እንስት የባሏን ሐይማኖትነው በአብዛኛው የምትከተለው።

እናም አንድም ወደ ጀነት ይመራታል። ወይም ጀሃነም ይዟት ይወርዳል። ለዚህም ሲባል አላህ ሴቶችንም ወንዶችንምራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከእሣት እንዲጠብቁም ጾታ ሳይለይ አዟቸዋል። ከዚህ ተግባር ከተዘናጉ የሚጠብቃቸውንአስደንጋጭ ቅጣት ልቦናን በሚያርገፈግፍ መልኩ ገልጾላቸዋል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ። በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ። አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም። የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።” (አተ ተህሪም፤ 6)

የወንድ ሐላፊነት (ቀዋማ) እና አስተዳዳሪነት ሊረጋገጥ የሚችለው ወንዱ ቤተሰቡን መምራት ሲችል ብቻ ነው።

ወንድ ልጅ ወንድ የሚሰኘው፣ በጭካኔውና በደረቅነቱ፣ ተሣዳቢና ተከራካሪ ወይም ጉልበተኛ በመሆኑ አይደለም። ይህየድንቁርና ዘመን ወንድነት ነው። በኢስላም ወንድነት ሌላ ትርጉም አለው። ጀግንነት ሌላ ይዘት አለው።

ወንድነት በኢስላም ጠንካራና የሚስብ ሰብእና፣ የላቀና የመጠቀ ባህሪ ባለቤት መሆን ነው። ጥቃቅን ጥፋቶችን ይቅርማለት፣ ከአላህ ወሰኖች ላይ ሳያወላውሉ መቆም፣ ሸሪዓውን ያለ ማመንታት በጽናት በቤተሰብ ላይ ማስፈጸም፣በብስለትና በብልሐት ቤተሰብን ወደ ኸይር መምራት፣ ሳያባክኑ መጽዋች መሆን፣ በዚህችም ሆነ በመጭው ዓለምሐላፊነትንና ተጠያቂነትን በጥልቀት በመረዳት ኢስላማዊ ቤተሰብ ሊታነጽበት የሚችለውን ናሙናዊ መስፈርት ማሟላትነው።

ይህ፣ ኢስላም ከተከታዮቹ የሚፈልገው ባህሪና ስብእና ተምሳሌት ነው።

2 COMMENTS

  1. All are very important points and consist of strong messages. May Allah(s.w) bestow the road to good deeds on you all here in Adunya and reward you all in Jenetel firdaws in the hereafter.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here