ሙስሊም መሆን፡ ሙስሊም ከባለቤቱ ጋር (ክፍል 1)

0
9120

ኢስላም ለሴቶችና ለጋብቻ ያለው እይታ

ጋብቻ በኢስላም እይታ የነፍስ ማረፊያ፣ የቀልብ መርጊያና መርኪያ፣የሕሊና መረጋጊያ ነው። ሁለቱ ጾታዎች በፍቅር፣ በመተዛዘን እናበመተባበር፣ በመቻቻልና በመመካከር የሚኖሩበት ተቋም ነው። በእንዲህዓይነቱ ሰላማዊና የተረጋጋ ተቋም ኢስላማዊ ቤተሰብ ይመሠረታል።ደስተኛና ጤነኛ ልጆች ይፈልቃሉ። ቁርአን የሁለቱን ጾታዎች ዘልዓለማዊናተፈጥሯዊ ግንኙነት አንጸባራቂ በሆነ አኳኋን ገልጾታል።

የፍቅርና የመረጋጋት፣ የመተዛዘን፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ድባብ ሊያሰፍንበሚችል መልኩ አብራርቶታል።

وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።” (አል ሩም፤ 21)

ጋብቻ የነፍስ ለነፍስ ትስስር ነው። ጠንካራ የግንኙነት ገመድ ነው። አላህ ሁለቱን ነፍሶች እንዲረጋጉ እና እንዲሰክኑ፣በፍቅር በተሞላ ቤት ውስጥ በጋራ እንዲኖሩ አስተሳስሯቸዋል። ለአንድ ሙስሊም ጥሩ ሚስት በሕይወት ውስጥ ዋነኛመደሰቻው፣ መርኪያውና መርጊያው፣ አላህ ከሰጠው ጸጋዎች ሁሉ በላጯ ናት።

ከሕይወት ውጣ ውረድ ወደርሷ አረፍ ይላል። ከየትኛውም ነገር በላይ ከርሷ ዘንድ መረጋጋትን፣ ፍቅርንና እዝነትንያገኛል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

“ይህች ዓለም መጠቀሚያ ናት። ትልቁ መጠቀሚያና መደሰቻ ግን መልካም ሚስት ናት።” (ሙስሊም)

ኢስላም ለጋብቻ ያለው እይታ እንዲህ አንጸባራቂ ነው። ለሴቶች ያለው እይታም እንዲህ የመጠቀ ነው።

ሙስሊም የሚፈልጋት የትዳር ጓደኛ

ሙስሊም ስለ ጋብቻ ያለው እይታ ይህ በመሆኑ አንዳንድ የዘመናችን እንስቶች የተሸፈኑበት የውበት ልባጭውስጣቸውን ከመፈተሽ አያቅበውም። የተሟላ ኢስላማዊ ስብእና ያላትን እንስት ይፈልጋል። እናም በጥንቃቄ ያጠናል።በጥንቃቄ ይመርጣል። የተረጋጋና ሰላማዊ ጎጆ መመስረት የምትችለውን እንስት ተግቶ ይሻል።

በርካታ ወንዶች የሚሹትንና የሚታለሉበትን የሚያማልል ውበት ብቻ አያነፈንፍም። ከርሱ ጎን ለጎን ዲን፣ ስብእና፣ ብልህአእምሮና ግሩም ባህሪን ይከጅላል። ተከታዩ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቃል መመሪያው ነው፡-

“ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ትገባለች። ለገንዘቧ፣ ለዘር ክብሯ፣ ለውበቷና ለዲኗ። የዲን ባለቤት የሆነችውን ምረጥ። (ይህን  ላደረግክ) እጅህ አመድ አፋሽ ትሁን።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዲን ያላትን መምረጥን ማበረታታታቸው የውበትን ጉዳይ ችላ በሉትማለታቸው አይደለም። አንድ ሰው ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት የሚያገባትን ልጅ እንዲያይ መክረዋል። ሲያያትየማታስደስተውን እና የማትስበውን ሚስት አግብቶ እንዳይቸገር።

ሙጊረት ቢን ሸእባህ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና  እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘመን አንዲት ሴት አጨሁ። የአላህ መልእክተኛም፡- “አየሐትን?” አሉኝ። “አላሐኋትም።” አልኳቸው። “እንግዲያውስ ተመልከታት። ጋብቻችሁ ዘለቄታ የሚኖረው እንዲያ ሲሆን ነው።” አሉ። (ነሣኢ)

አንድ ሰው መጣና አንዲትን የአንሷር ሰው ማጨቱን ለነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ነገራቸው። “አይተሐታልን?” አሉት። “አላየኋትም  አላቸው። እንዲያያት አዘዙት። (ነሣኢ)

ውበት አንድ ሙስሊም ወንድ ሊያገባት የሚፈልጋት ሴት አይነተኛ ባህሪ እንዲሆን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በአጽንኦት በብዙ ቦታዎች ገልጸዋል። ከሌሎች ውስጣዊ ባህሪያት ጎን ለጎን መገኘት ያለበት ነገር እንደሆነአሳስበዋል።

በአንድ ወቅት ለኢብን አባስ እንዲህ ብለውታል፡-

“ከአንድ ሰው ሐብቶች ውስጥ ይበልጥ ውድ የትኛው እንደሆነ ልንገርህን? ሲያያት የምታስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ ሲርቅ የምትጠብቀው ጥሩ ሚስት ናት።” (ሐኪም)

አቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም“ከሴቶች ሁሉ በላጯ የትኛዋ ናት?” ተብለው ተጠይቀው “ሲያያት የምታስደስት፣ ሲያዛት የምትታዘዝ፣ በነፍሷም በገንዘቡም እርሱ የማይፈልገውን የማትፈጽም” ሲሉ መለሱ።

ለወንድ ልጅ ደስታንና እርካታን፣ የሰላም እና የደስታ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆችን ማፍራት የምትችል፣ ልጆችን በጥሩስነ ምግባር የማሣደግ ችሎታ ያላት ስለሆነች እንስት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያላቸው እይታ ይህንይመስላል።

ጋብቻ በቀላል ጥሎችና አለመግባባቶች መሠረቱ የማይናጋ ጠንካራና ጽኑ ይሆን ዘንድ የአእምሮን፣ የመንፈስን እናየነፍስን ፍላጎት ሊያሟላ በሚችልበት መልኩ እንዲታነጽ የመልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍላጎት ነው። እናምየአላህን ሸሪዓ መመሪያው ያደረገ ሙስሊም በውበት ልጣጭ የተለበጠችን እኩይ ሴት በማግባት ሕይወቱን ከማናጋትበእጅጉ ጥንቃቄ ያደርጋል።

በጋብቻ ሕይወቱ የኢስላምን መመሪያ ያከብራል

ትክክለኛ ሙስሊም ከሚስቱ ጋር ባለው ግንኙነት እጅግ ድንቅና ውብ የሆኑ የኢስላም ትምህርቶችንና መመሪያዎችንያከብራል። እንስትን ስለ ማክበርና ከርሷ ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለመመስረት፣ እንዲሁም ስለመንከባከብ ኢስላምያስተላለፋቸውን መመሪያዎች ስናይ በግርምት እንደመማለን።

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህን አጀንዳ ከፍተኛ ቦታ ሰጥተውታል። እውነቱን ለመናገር እንዲህዓይነቱን ድንቅ መመሪያ ከየትኛውም ሐይማኖት አናገኝም። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወንዶችንእንዲህ ሲሉ ይመክራሉ፡-

“ሴትን ልጅ በእንክብካቤ ያዙ። አደራችሁን። ሴት ልጅ የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነው። ከጎን አጥንት ውስጥ ደግሞ እጥፋቱ የሚበዛው የላይኛው ነው። እርሱን ለማቃናት ከሞከርክ ትሰብረዋለህ። እንዲሁ ከተውከው ደግሞ እንደታጠፈ ይኖራል። ስለዚህም በሴቶች ጉዳይ አደራችሁን።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

“ሴት ልጅ እንደ ጎን አጥንት ናት። አቃናታለሁ ካልክ ትሰብራታለህ። በርሷ መጠቀም ከፈለግክ ባለችበት ሁኔታ መታጠፏ እንዳለ ሆኖ  ነው።”

በሌላ የሙስሊም ዘገባ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

“ሴት ልጅ ከጎን አጥንት ተፈጥራለች። በአንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ አትሆንም። ከርሷ መኗኗር ከፈለግክ እጥፋቷ ባለበት ሁኔታ ተኗኗራት። አቀናታለሁ ካልክ ትሰብራታለህ። መስበር ማለት ደግሞ መፍታት ማለት ነው።”

ይህ የመልእክተኛው ገለጻ የእንስትን ባህሪ ድንቅ በሆነ ሁኔታ የገለጸ ነው። ባል እንደሚፈልገው በአንድ ዓይነት ባህሪውስጥ አትሆንም። ባል ይህን ሊረዳ ይገባል። እርሱ ትክክል ነው ብሎ በሚያስበው ቆፍጣናነት ወይም ሌላ ስነ ልቦናዊባህሪ ላይ እንድትጸና ለማድረግ መሞከር የለበትም። እንስታዊ ባህሪዋን መዘንጋት የለበትም። አላህ እንደፈጠራትይቀበላት። እርሱ ከሚፈልገው ባህሪ አንጻር የታጠፈ የሚመስል ባህሪ አላት። እርሱ በሚፈልገው የባህሪ መስመርሊያስኬዳት ካሰበ ይሰብራታል። ይህም ማለት አብረው መኖር አይችሉም ማለት ነው። እጣ ፈንታቸው ፍች ይሆናል።

ሙስሊም ይህን ነብያዊ ትምህርት ከተረዳ፣ ስነ ልቦናዊና ተፈጥሯዊ ባህሪዋን ከተገነዘበ ብዙ ግድፈቶቿን ይቅር ይላል።እናም ቤታቸው የተረጋጋና የሰከነ ይሆናል። ጭቅጭቅና ጥል አይበዛበትም።

ይህን ሐዲስ በጥሞና አስተውል። ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሐዲሱን የጀመሩት፡- “የሴትን ልጅ ነገር አደራችሁን።”በማለት ነው። ለሴት ልጅ የሰጡትን ትኩረትና ስነ ልቦናዋን ምን ያህል ጠልቀው እንደተረዱ ያመለክታል። ሙስሊም ባልበዚህ ነብያዊ መመሪያ በእያንዳንዱ ቅጽበት ከመመራት ያመነታልን?

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመሰናበቻ ሐጃቸው ላይ ባደረጉት ንግግር እንኳ የሴትን ልጅ ጉዳይአልዘነጉም። ይህ ንግግር የሕይወታቸው ፍጻሜ መቃረቡን ያወቁበት ነው። ለሙስሊሞች እጅግ አንገብጋቢ አጀንዳዎችንመናገር እንዳለባቸው ግልጽ ነው። በዚህች ቅጽበት እንኳ የሴቶችን ጉዳይ አንስተው እነርሱን ስለመንከባከብ መመሪያአስተላልፈዋል። እንዲህ አሉ፡-

“አዋጅ፣ የሴቶችን ጉዳይ አደራ እላችኋለሁ። መልካም ዋሉላቸው። ከናንተ ዘንድ የተቀመጡ አደራዎች ናቸው። መጥፎ ነገር ካልፈጸሙ በቀር። እንዲያ ሲሆን ግን በምኝታ ከነርሱ ተገለሉ። ይህም ካላስተካከላቸው ለስሙ ያህል ቸብ አድርጓቸው። ከታዘዟችሁ አታንገላቷቸው። አዋጅ፣ በሴቶቻችሁ ላይ መብት አላችሁ። እነርሱም በናንተ ላይ መብት አላቸው። እናንተ በነርሱ ላይ ያላችሁ መብት የምትጠሉት ሰው ከፍራሻችሁ እንዳይደርስና ቤታችሁን ላልፈለጋችሁት ሰው እንዳይፈቅዱ ነው። እነርሱ በናንተ ላይ ያላቸው መብት ደግሞ በልብስም በጌጥም የሚያስፈልጋቸውን የኑሮ ሁኔታ ልታሟሉላቸው ነው።” (ቲርሚዚ)

እያንዳንዱ ሙስሊም ሊሰማውና ሊያስተውለው የሚገባ ኑዛዜ ነው። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ንግግራቸው የተጋቢዎችን መብቶች ወስነዋል። ሴትን ለመበደል ማሰብ በማያስችል ሁኔታ ለነርሱ መሥራትና መንከባከብ ተገቢ መሆኑን አስምረውበታል።

ስለ ሴት ልጅ ያስተላለፏቸው ኑዛዜዎች ወደ ከፍተኛ የምጥቀት ደረጃ አሻቅበው ለሴቶች ደግ የሆነን ወንድ ምርጥ የኡምማው አባል እስከማድረግ ደርሰዋል። እንዲህ ብለዋል፡-

“ከአማኞች መካከል እምነቱ ይበልጥ ሙሉ የሆነው ስነ ምግባሩ ጥሩ የሆነው ነው። ከናንተ ውስጥ በላጬ ለሴቶች በጎ የሆነው ነው።” (ቲርሚዚ)

ሴቶች ባሎቻቸውን ለመክሰስ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ ቀረቡ። መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ወንዶችን ወቀሱ፡-

“ሴቶች ባሎቻቸውን ለመክሰስ ከመሐመድ ቤቶች ድረስ መጥተዋል። ሴቶችን የሚበድሉ ወንዶች በጎዎች አይደሉም።” (አቡ ዳውድና ነሣኢ)

ኢስላም ሴትን የማላቅና ለርሷ እንክብካቤ የመጨነቅ ደረጃን ይበልጥ ከፍ በማድረግ ባል ቢጠላት እንኳእንዲንከባከባት ያዘዋል። ይህ፣ ሴት ልጅ በዚህ ሐይማኖት ካልሆነ በቀር በየትኛውም የታሪክ ወቅትና አስተሳሰብአግኝታው የማታውቀው ጸጋ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَيَجْعَلَ اللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا

“በመልካምም ተኗኗሩዋቸው። ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)። አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና።”  (ኒሣእ፤ 19)

ይህ ቁርአናዊ መልእክት የወንዱን ሕሊና በመንካት ቁጣውን ያበርዳል። ለሚስቱ ያለውን ጥላቻ ይቀንሳል።

ኢስላም በእንዲህ ዓይነት መመሪያዎች ጋብቻ በቀላሉ እንዳይናጋ፣ ስሜቶች በተለዋወጡ ቁጥር ለአደጋ እንዳይጋለጥይጠብቀዋል።

ዑመር ቢን አል ኸጣብ ሚስቱን ስላልወደዳት ሊፈታት ላሰበ ሰው የሰጡት ምክር ድንቅ ነው። እንዲህ አሉት፡-

“ወዮልህ፣ ቤት የሚገነባው በፍቅር ላይ ብቻ ነውን? እንክብካቤና ስነ ምግባር የት ጠፋ?”

በኢስላም የጋብቻ ትስስር ከጊዜያዊ ስሜቶችና ከእንስሳዊ ዝንባሌዎች በላይ ነው። ሆደ ሰፊ፣ ታጋሽ፣ ለሌሎች ሕይወትአሳቢ የሆነ ሙስሊም ከሚጠላት ሚስቱ ጋር ያለው ግንኙነት ከእንስሳዊ ስሜት፣ እንዲሁም ከትርፍና ከኪሣራ በላይየሆነ ስሜት ነው።

ምንጊዜም ቢሆን የአምላክን ቃል ያከብራል። ሚስቱን ይንከባከባል። ቢጠላት እንኳ። ምን አልባትም አላህ በጋብቻቸውውስጥ በርካታ በጎ ነገሮችን አድርጎ ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው አንድን ነገር ሊጠላ ይችላል። ግና ምን አልባትም አላህበዚያ ነገር ውስጥ በጎ ሁኔታን አኑሮለት ይሆናል። እናም ሙስሊም ሲወድም ሲጠላም በልክ ነው። ሲወድ  ፍቅር እውርነው ብሎ እውር አይሆንም። የአእምሮውን ልጓም አይስትም። በጭፍኑ አይጎተትም። ሲጠላም እንደዚሁ ሚዛንአይስትም። በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጥ ፍጹም ሚዛናዊ ይሆናል።

ሴት ልጅ ባሏ የቱን ያህል ቢጠላትም ከበጎ ባህሪዎች የነጠፈች እንደማትሆን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይናገራሉ። ይህን በጎ ጎኗን ትቶ የሚጠላውን ጎኗን ማጉላት አግባብ አይደለም።

ሙእሚን ወንድ ሙእሚን ሴትን አይጥላ። አንድ ባህሪዋን ባይወደው ሌላውን ይወደዋል።” (ሙስሊም)

ተምሳሌታዊ ባል

እነዚህ ሸሪዓዊ መመሪያዎች የሰረጹት ሙስሊም ተምሳሌታዊ ባል ከመሆን ውጭ ሌላ ምርጫ የለውም። ባለቤቱንይንከባከባል። ልቧን በደስታ ይሞላል። ለስሜቷ ይጠነቀቃል። ትዳራቸው እድሜው ቢረዝምም አይወይብም።  ቀቱናድምቀቱ እንደተጠበቀ ይኖራል።

ወደቤቱ ሲገባ ሚስቱንና ልጆቹን የደስታ ስሜት በሚያሰርጽ የደመቀ ፈገግታ፣ በብሩህ ገጽታ ያገኛቸዋል። የተባረከችውንኢስላማዊ ሰላምታ ያቀርብላቸዋል። አላህ ይህችን ሰላምታ አዟል፡-

فَإِذَا دَخَلْتُم بُيُوتًا فَسَلِّمُوا عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِّنْ عِندِ اللَّهِ مُبَارَكَةً طَيِّبَةً ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ። እንደዚሁ አላህ አንቀጾችን ለእናንተ ያብራራል። ልታውቁ ይከጀላልና።” (አል ኑር፤ 61)

የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አነስን እንዲህ ሲሉ መክረወል፡-

“ልጄ ሆይ፣ ወደቤተሰቦችህ ስትገባ ሰላምታ አቅርብላቸው። ላንተም ለቤተሰቦችህም በረከት ይሰፍንላችኋል።”(ቲርሚዚ)

በእርግጥም በረከት ነው። ትልቅ በረከት። ወደ ቤቱ ሲገባ ሰላምታ ያቀርባል። በብሩህ ገጽታ ቤተሰቦቹን ይገናኛል።ሕይወታቸውን በደስታ በሚያደምቅ አቀባበል ያደርጋል። እዝነትና ርህራሄ ያሳያቸዋል። ሚስቱ የምትፈልገውን እገዛያደርግላታል። ድካም ወይም ሕመም ሲሰማት በጥሩ ቃላት ያጽናናታል። ሐዘኗን ያስወግድላታል። ጠንካራና መልካምበሆነ ጥላ ከለላ ስር መሆኗ እንዲሰማት ያደርጋታል። በቻለው ልክ የሚያስፈልጋትን ነገሮች ያደርግላታል። እንስታዊባህሪዋ የሚጠይቃትን የመዋብ ሁኔታ እንድትፈጽም ይፈቅድላታል። ጊዜውን እና ትኩረቱን ይሰጣታል። ጊዜውን በሙሉበንባብ ወይም በስራ ተወጥሮ እርሷን አይረሳም። መብቶቿን አይዘነጋም።

ኢስላም ለሚስት በባሏ የመጠቀምና የመደሰት መብት ሰጥቷታል። እንደ እንስት ማግኘት ያለባትን ሁሉ እንድታገኝደንግጎላታል። በሌላ ስራ ይቅርና በኢባዳ እንኳ ተውጦ ሚስቱን የራቀ ተወቅሷል። የአላህ መልእክተኛ ለአንድ ባልደረባቸው የሰጡትን ትምህርት እናስተውል፡-

“ቀን እንደምትጾም፣ ሌሊት እንደምትቆም፣ አልተነገረኝምን?” አሉት። “አዎ” አላቸው። እንዲህ አሉ፡- “እንዲህስ አታድርግ። ጹም፣ አፍጥር። ተኛ፣ ስገድ። አካልህ ባንተ ላይ መብት አለው። ዓይንህ ባንተ ላይ መብት አለው። ባለቤትህ ባንተ ላይ መብት አላት። እንግዶችህ ባንተ ላይ መብት አላቸው።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

የዑስማን ቢን መዝዑን ባለቤት ከነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባለቤቶች ዘንድ ገባች። ጥሩ ያልሆነ ገጽታና አለባበስይታይበታል። ምን አገኘሽ? አሏት። ባሏን በማስመልከት እንዲህ አለች፡-

“ሌሊት ይቆማል። ቀን ይጾማል።”

ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህ አባባሏ ተነገራቸው። ዑስማን ቢን መዝዑንን አገኙትና ወቀሱት። “የኔን አርአያነት አትከተልምን?”ሉት።  እከተላለሁ።” አላቸው።

በሌላ ጊዜ ገጽታዋ አምሮና አለባበሷ ተውባ፣ ሽቶ ተቀብታና ተቆነጃጅታ መጣች።

በሌላ ዘገባ እንደተወሳው ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለዑስማን እንዲህ ነበር ያሉት፡-

“ዑስማን ሆይ፣ ምንኩስና ግድ አልተደረገብንም። የኔን አርአያነት አትከተልምን? በአላህ እምላለሁ፣ ሁላችሁም አላህን እኔ ይበልጥ እፈራለሁ። ወሰኖችንም እጠነቀቃለሁ።”

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህን መመሪያቸውን ለባልደረቦቻቸው ያስተላልፉ ነበር። እጆቻቸውንምይዘው ወደ ሚዛናዊነት ይመሯቸው ነበር። በሁሉም የሕይወታቸው መስክ ኢስላም ሚዛናዊነትን አስተማራቸው።በአምልኳዊም ከባለቤቶቻቸው ጋር ባላቸውም ግንኙነት ሚዛናዊነት ባህሪያቸው ሆነ። እርስ በርስ በዚህ ባህሪይመካከራሉ። ይተራረማሉ። በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ መግባት ከፈለጉም  የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያማክራሉ።

ቡኻሪ አቡ ጁሃይናህን ዋቢ በማድረግ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስልማንና አቡ ደርዳእን በወንድማማችነት አስተሳሰሩ። ሰልማን አቡደርዳእን ሊጠይቀው በሄደ ጊዜ ኡም ደርዳእ ራሷን ጥላ አገኛት። “ምን ሆነሽ ነው?” አላት። “ወንድምህ አቡ ደርዳእ ለዚህች ዓለም ሕይወት ደንታ ቢስ ሆኗል  አለችው። ወደ አቡ ደርዳእ ዘንድ ሄደና ምግብ አዘጋጅቶ “ብላ” አለው። “ጾመኛነኝ አለ።” ካልበላህ አልበላም  አለው። በላ። ሌሊት ላይ አቡ ደርዳእ ሊሰግድ ተነሳ። ሰልማንም “ተኛ” አለው። ተኛ። ደግሞ ሊነሳ ሲልም “ተኛ” አለው። የሌሊት መጨረሻ ሲደርስ “አሁን ተነስና ስገድ” አለው። ከዚያም እንዲህ ሲልመከረው፡-

“ጌታህ ባንተ ላይ መብት አለው። ነፍስህም ባንተ ላይ መብት አላት። ቤተሰቦችህም ባንተ ላይ መብት አላቸው።ለሁሉም የየመብታቸውን ስጣቸው።”

ከነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና የሆነውን ነገራቸው። ነቢዩም፡- ሰልማን እውነቱን ነው። አሉ።

ሙስሊም ሚስቱን ማዝናናትንም አይዘነጋም። በቀልድና በጫዋታ ዘና እንድትል ያደርጋታል። በዚህም አርአያው የአላህመልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ናቸው። በሁሉም የሕይወት መስክ አርአያ ነበሩ። የሕይወት ውጣ ውረድ፣ያለባቸው ከባድ ሐላፊነት፣ ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ለማነጽ፣ ዲኑን ለማጠናከር የሚያደርጉት ሩጫ፣ የጦር መሪ ሆነውሰራዊት ማዝመታቸው፣ የሕብረተሰቡ መሪ በመሆን ስለ ሐገር ማሰባቸው እና ሌሎችም ተግባራት ከባለቤቶቻቸው ጋርባላቸው ግንኙነት መብታቸውን እንዳይጠብቁ አላደረጓቸውም። ጥሩ ባል ነበሩ። ሚስቶቻቸውን ይንከባከባሉ። ያዝናናሉ።ያጫውታሉ። በደስታ እንዲፈነድቁ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ይፈጽማሉ።

አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ያስተላለፉት አንድ ሐዲስ ይጠቀሳል። እንዲህ ብለዋል፡-

ለነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያዘጋጀሁትን አጥሚት ይዥ መጣሁ። ሰውዳእን አገኘኋት። በኔና በነቢዩ መካከልቆማለች። “ብይ” አልኳት። “አልበላም” አለች። “ብይ? ካልሆነ ፊትሽን እለቀልቀዋለሁ” አልኳት። አሻፈረኝ አለች። እጄንበአጥሚቱ አስነካሁና ፊቷን ለቀለቅኳት። ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይስቁ ጀመር። እርሷንም ብድርሽን መልሽ።አንችም ለቅልቂያት አሏት።

በሌላ ዘገባ እንደተወሳው እርሷም ብድሯን መለሰች። ፊቴን ለቀለቀች። የአላህ መልእክተኛ ይስቁ ነበር። (አል ሐይሰሚ)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሴቶችን እንዴት ዘና ያደርጉና ያጫውቱ እንደነበር አስተዋልክን?

አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በአንድ ጉዞ ላይ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጋርነበረች። ሩጫ ከርሳቸው ጋር ተሽቀዳደመች። አሸነፈቻቸው። ውፍረት በጨመረች ጊዜ እንደገና ተሽቀዳደ ና አሸነፏት። ብድሬን መለስኩ።  አሉም። (አህመድና አ  ዳውድ)

መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሚስታቸውን ለማስደሰት ከዚህም በላይ ያደርጋሉ። እንድትደሰት በመሻት ንጹህየሆነን ዜማና ጨዋታ እንድትመለከት ይፈቅዱላታል። ያዝናኗታል። አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውናእንዲህ ሲሉ ከነዚህ ክስተቶች አንዱን አውስተዋል፡-

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ተቀምጠው ነበር። የሕጻናት ጨዋታና የወጣቶችን ጫጫታ ሰሙ። ሐበሾችበመዝፈንና በመጨፈር ላይ ነበሩ። “አኢሻ፣ ነይ ተመልከች” አሉኝ። አገጨን ከትከሻቸው ላይ አድርጌ ማየት ጀመርኩ።ጥቂት ቆይተው “ጠገብሽን?” አሉኝ።  አልጠገብኩም” አልኳቸው- ከርሳቸው ዘንድ ያለኝን ደረጃ (ምን ያህልእንደሚያፈቅሩኝ) ለማወቅ። እያስተራረፉ በመቆም እስኪበቃኝ ድረስ እንድመለከት አደረጉ። (ነሣኢ)

በሌላ ዘገባ አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

“በአላህ እምላለሁ፣ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከቤቴ በር ላይ ቆመው ነበር። ሐበሾች መስጊድውስጥ በአንካሴ ይጫወቱ ነበር። የአላህ መልእክተኛ እኔን በኩታቸው ከልለው ጫዋታውን እንድመለከት አደረጉኝ።በትከሻቸው እና በጆሯቸው መካከል አጮልቄ እመለከት ነበር። ለኔ ሲሉም (ይታየኝ ዘንድ) ቆሙልኝ። እስክጠግብ ድረስአሳዩኝ። ገና ጨዋታ ያልጠገብኩ ልጅ ነበርኩ።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከባለቤቶቻቸው ጋር የነበራቸውን በእንክብካቤና በፍቅር የተሞላ ግንኙነትስንመለከት ሙስሊም ምንጊዜም ከባለቤቱ ጋር መዝናናት፣ መጫወት የተቀላቀለበት ልዝብና ልስልስ ግንኙነት ሊኖረውእንደሚገባ እንረዳለን። የሐላልን መስክ የጣሰ እስካልሆነ ድረስ የሚስትን ልቦና በሐሴት ማድመቅ ተገቢ ነው።

ያልወደዱት ምግብ ሲቀርብ፣ ማእድ ከተወሰነለት ሰአት ሲዘገይ ወይም በሌላ ጥቃቅን ምክንያት ምድርን ቀውጢየሚያደርጉ ባሎች አሉ። በአልባሌ ሰበብ ቁጣቸው ጣሪያ ይነካል። ከሚስቶቻቸው ጋር ይጣላሉ። ትክክለኛ ሙስሊምእንዲህ ዓይነት ባህሪ ካላቸው ባሎች አይሆንም። ልዝብና ልስልስ፣ ገራገርና ተጫዋች የሚያደርገውን ባህሪ ይከተላል።

መልእክተኛው ምግብን አጣጥለው አያውቁም። ካልወደዱት እንኳ ይተውታል እንጅ ክፉ አይናገሩም። (ቡኻሪና ሙስሊም)

አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ባለቤታቸውን መረቅ ጠየቁ። ኸል እንጅ የለንም አሏቸው። እርሱ እንዲመጣላቸውፈቀዱ። እንዲህም “ኸል ጥሩ ምግብ ነው። ኸል ጥሩ ምግብ ነው።” (ሙስሊም)

ባለቤታቸው ምግብ በጊዜ ስላላቀረበች፣ ጥቂት ነገር ስላጠፋች ወይም ስላጓደለች አይናቸው የሚቀላና ቡጢየሚሰነዝሩ አባወራዎች ይህን የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ምክር ያድምጡ። ባህሪያቸውን ያስተውሉ።ይህን ያደረገችው ወዳ ላይሆን ይችላል። ምን አልባትም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ገጥሟት ሊሆን ይችላል።አባወራው ግን ምክንያቱን ሳያውቅ ይቆጣል። ችግሩን ሳይጠይቅና ሳይረዳ ይበሳጫል። ለምን አይቆጣ? አባወራአይደል!

ትክክለኛ ሙስሊም ውለታው በሚስቱ ብቻ አይወሰንም። የርሷን ጓደኞችም ያከብራል። ለነርሱ ውለታ ይውላል።የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አርአያነት በመከተል ይህን ያደርጋል። አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

“አንዲት አዛውንት ከነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ ትመጣ ነበር። እርሳቸውም ያከብሯታል። ይንከባከቧታል።አጥብቀውም ስለደህንነቷ ይጠይቋታል። እርሷም ትመልሳለች። “ይህችን አዛውንት ከሌሎች በበለጠ ሁኔታየሚንከባከቧት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኳቸው።  ኸዲጃ በሕይወት በነበረች ጊዜ ትመጣ ነበር። የፍቅረኛንወዳጅ መንከባከብ የእምነት አካል መሆኑን አላወቅሽምን?” አሉኝ። (ሐኪም)

ሚስት በአንዳች ምክንያት ልትቆጣና ልትበሳጭ ትችላለች። በዚህ ጊዜ ሙስሊም ባል ሆደ ሰፊ ሊሆን ይገባል።ይታገሳት። እንስታዊ ባህሪዋን ይረዳላት። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባለቤቶቻቸው ሲቆዩና ሲያኮርፉያደርጉት እንደነበረው ታጋሽና ሩህሩህ ይሁንላት።

ዑመር ቢን አልኸጣብ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

“ቁረይሾች ሴትን የምንጫን ሰዎች ነበርን። መዲና ስንገባ ሴቶች የሚጫኗቸውን ወንዶች አገኘን። ሴቶቻችን ከነርሱሴቶች መማር ጀመሩ። ቤቴ ከበኒ ኡመያ ቢን ዘይድ ቤት አጠገብ ነበር። አንድ ቀን ሚስቴ ተቆጣችብኝ። ስናገራት መለሰችልኝ። እንድትመልስልኝ አልፈልግም ነበር። ተቃወምኳት። “መቃወም አይገባህም። የአላህ መልእክተኛም ሚስቶችም ይመልሱላቸዋል።” አለች። “አንድ ቀን ከነሌሊቱም ያኮርፏቸዋል።” ስትልም አከለች። ከሐፍሷ ዘንድ ገባሁ።“የአላህን መልእክተኛ ትመልሱላቸዋላችሁን?” አልኳት። “አዎ” አለችኝ። “አንድ ቀን ከነሌሊቱ ታኮርፏቸዋላችሁን?”አልኳት። “አዎ” አለችኝ። “ይህን ያደረገች ሴት ከሰረች። የአላህ መልእክተኛ ሲቆጡ አላህም ይቆጣል ብላችሁ አትሰጉምን? እንጠፋለን ብላችሁ አትፈሩምን? የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አትመልሺላቸው። ምንምነገርም አትጠይቂያቸው። እኔን ጠይቂኝ።  አልኳት።”

ዑመር ከነቢዩ ዘንድ መጣና ከሐፍሷ ጋር የተነጋገሩትን አወሱላቸው። መልእክተኛው ፈገግ አሉ።

ሙስሊም በዚህ ባህሪ መዋብ ይገባዋል። በስራው ሁሉ የነቢዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አርአያነት ይከተል ዘንድ።ይህ ሲሆን ኢስላም የመጠቀ የማሕበራዊ ሕይወት ሐይማኖት ነው፤ ሙስሊሞች ያገኛቸው ችግርና ሁከት ምክንያቱሰዎች ከዚህ ሐይማኖት በመራቃቸው ወይም ይህን የመጠቀ እሴት ስላለወቁት የተፈጠረ ነው ለሚለው አባባል ጥሩመረጃ ይሆናል። ኢስላም የላቁ ማሕበራዊ እሴቶች እንዳሉት እና ተጋቢዎች በኢስላማዊ የቤተሰብ ስርዓት ከተመሩሕይወታቸው ሐሴት እና ጽድቅ የነገሰበት እንደሚሆን ቋሚ ምስክር ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here