ሙስሊም መሆን፡ ሙስሊም ከራሱ ጋር (ክፍል 1)

0
3515

መግቢያ

ሙስሊሞች ከሰዎች መሐል በሁ ም ነገራቸው ለየትና ጎላ ብለውእንዲታዩ ኢስላም ይሻል፡፡ በአነጋገራቸው፣ በእንቅስቃሴያቸውናተግባራቸው የሌሎች አርአያ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ የታላቅ ተልእኮባለቤት የሆነ ስብእና ጎላና ደመቅ ብሎ መታየት አለበትና፡፡

ኢብን ሐንዞላ ባስተላለፉት አንድ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ከወንድሞቻቸው ጋር ለመገናኘትበሚያደርጉት አንድ ጉዞ ላይ እንዲህ ብለዋቸዋል፡-

“ወንድሞቻችሁን ልትገናኙ ነው፡፡ እናም ከሰዎች መካከል ጎላና ደመቅ ብላችሁ ትታዩ ዘንድ መጓጓዣችሁን አበጃጁ፡፡ ልብሶቻችሁንም አሳምሩ፡፡ አላህ መዝረክረክን አይወድምና፡፡” (ኡቡ ዳውድና ሐኪም)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በአለባበስና በውጫዊ ገጽታ መዝረክረክን “አተፈሁሽ” ሲሉ ጠርተውታል፡፡የቃል አጠቃቀማቸው ኢስላም ለነገሩ ያለውን የከበደ ጥላቻ ያመለክታል፡፡

እውነተኛ ሙስሊም ራሱን አይዘነጋም፡፡ በሕይወት ውስጥ ታላቅ ሐላፊነት ቢኖርበትም አካሉን አይዘነጋም፡፡ ውጫዊገጽታ የውስጥን ማንነት እንደሚያሳይ ይረዳልና፡፡ ጥሩ ውጫዊ ገጽታ ለጥሩ ውስጣዊ ማንነት ተገቢ ነው፡፡ ወደ አላህጥሪ የሚያደርግ ሙስሊም ስብእናውን የሚገነባው ከዚህ ሁሉ ኢባዳ ነው፡፡

ንቁና ጥንቁቅ ሙስሊም አካሉን፣ አእምሮውንና መንፈሱን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ይንከባከባል፡፡ ለሁሉም የየድርሻቸውንይሰጣል፡፡ ለአንዱ አድልቶ ሌላውን አይጎዳውም፡፡ በአብደላህ ቢን አምር ቢን አል አስ የተላለፈውን የሚከተለውን የነቢዩሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

በኢባዳ ላይ ወሰን ማለፍን የተረዱት ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም፡-

“ቀን እንደምትጾም እና ሌሊት እንደምትሰግድ አልደረሰኝምን?  ሲ” ጠየቁት፡፡ “አዎ ልክ ነው፡፡” አላቸው፡፡ “ይህን አታደርግ፡፡ ጹም፣ አፍጥር፡፡ ተኛ፣ ስገድ፡፡ ምክንያቱም አካልህ በአንተ ላይ መብት አለው፡፡ አይኖችህም መብት አላቸው፡፡ ባለቤትህም መብት አላት፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ሙስሊም በአካሉ፣ በአእምሮውና በመንፈሱ መካከል ይህን ሚዛናዊነት እንዴት ሊያረጋግጥ ይችላል?

ሀ) አካሉ

በአመጋገቡ ሚዛናዊ

ሙስሊም ምንጊዜም ጠንካራና ጤነኛ አካል እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ እናም በአመጋገቡ ሚዛናዊ ነው፡፡ ምግብ ላይጉጉና ስግብግብ አይደለም፡፡ ለሰውነቱ የሚጠቅመውን ያህል ብቻ ይመገባል፡፡ ጤንነቱን የሚጠብቅለትንና አካላዊጥንካሬውን የሚለግሰውን ሚዛናዊ የአመጋገብ ስልት ይከተላል፡፡ በዚህ ረገድ የሚከተለው የአላህ ቃል መመሪያውነው፡-

يَا بَنِي آدَمَ خُذُوا زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا وَلَا تُسْرِفُوا ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْرِفِينَ

“የአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡ ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና፡፡”  (አል አእራፍ፤ 31)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አመጋገብን በተመለከተ የሚከተለውን መመሪያ አስተላልፈዋል፡-

“የአደም ልጅ ከሆዱ የበለጠ መጥፎ እቃን አልሞላም፡፡ ሰውየው መመገብ ካለበት አንድ ሦስተኛውን ለምግብ፣ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጥና አንድ ሦስተኛውን ለአየር ይተወው፡፡” (አህመድና ቲርሚዚ)

ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

“አለቅጥ መመገብንና መጠጣትን ተጠንቀቁ፡፡ ምክንያቱም እርሱ አካልን ያበላሻል፡፡ በሽታን ያወርሳል፡፡ ከሶላት ያሰንፋል፡፡ እናም ሚዛናዊ ሁኑ፡፡ ለአካልም ጥሩ ነው፡፡ ከአባካኝነትም የራቀ ነው፡፡ አላህ ውፍረትን ይጠላል፡፡ ከሐይማኖቱ አካላዊ ስሜቱን ያስበለጠ ሰው ይጠፋል።”

ሙስሊም አስካሪ መጠጦችን ይቅርና ሰውነትን የሚያነቃቁ ወይም የሚያደንዝ ነገሮችን ሁሉ ይጠነቀቃል፡፡ በጊዜይተኛል፡፡ በጊዜም ይነሳል፡፡  ልታመመ በቀር መድሐኒት አይወስድም፡፡ የአመጋገብ እና የአኗኗር ስርዓቱ ጤንነትንናንቃትን ይለግሰዋል፡፡

ጠንካራ ሙስሊም ከደካማ ሙስሊም የተሻለ መሆኑን ሙስሊም ይረዳል፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምእንደነገሩን፡፡ እናም ለጤንነት የሚረዳ አኗኗርን በመከተል ጤንነቱን ይንከባከባል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ሙስሊም በአብዛኛው ጎጂ ከሆኑ ምግቦችና አመጋገቦች፣ አካልን ከሚጎዱ አጓጉል ልምዶች የራቀ በመሆኑ አካላዊጤንነቱ የተጠበቀ ቢሆንም ይበልጥ ብርታትን እና መነቃቃትን ለማግኘት ይጥራል፡፡ ለራሱ በመረጠው ጤንነታዊ አኗኗርብቻ አይብቃቃም፡፡ እድሜውን፣ አካሉንና ማሕበራዊ ሁኔታውን የሚስማማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ያከናውናል፡፡ለዚህም የማይዛባ ኘሮግራም አለው፡፡

ዘወትርና በኘሮግራም የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ አካልን ለማጎልበትና ጤንነታዊፋይዳንም በተሟላ መልኩ ለማግኘት ይረዳል፡፡ ሙስሊም በዚህም ረገድ ባህሪው የሆነውን ሚዛናዊነትን ይከተላል፡፡

የአካልና የልብስ ንጽህና

በሰዎች መካከል ጎላና ደመቅ ብሎ እንዲታይ ኢስላም የሚፈልገው ሙስሊም በአካሉ ንጹህ ነው፡፡ ዘወትር ይታጠባል፡፡የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ተከታዮቻቸውን ዘወትር እንዲታጠቡና ሽቶ እንዲቀቡ መመሪያአስተላልፈዋል፡፡ በተለይም በጁሙዓ ቀን፡፡ እንዲህ ብለዋል፡-

“ጁሙዓ ቀን ራሳችሁን ጨምሮ ታጠቡ፡፡ ጀናብተኛ ባትሆኑም እንኳ፡፡ ሽቶም አርከፍክፉ፡፡” (ቡኻሪ)

ነቢዩ መታጠብን አጥብቀው ከማዘዛቸው የተነሳ አንዳንድ የፊቅህ ጠበብት በጁሙዓ ቀን መታጠብ ግዴታ መሆኑንእስከመናገር ደርሰዋል፡፡

አቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምእንዲህ ብለዋል፡-

“እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ መታጠብ አለበት፡፡ አካሉንና ራሱን ይታጠብ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ሙስሊም ልብሱም ካልሲውም ንጹህ ነው፡፡ ልብሱንና ካልሲውን ሁሌም ይቆጣጠራል፡፡ ንጽህናቸውን ይጠብቃል፡፡ከልብስ ወይም ከካልሲ መጥፎ ጠረን እንዲወጣ ፈጽሞ አይፈቅድም፡፡ ጠረኑን ለማሣመር ሽቶ ይጠቀማል፡፡ ዑመርአላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ማለታቸው ተወስቷል፡-

“የንብረቱን አንድ ሦስተኛ ለሽቶ ያዋለ አባካኝ አይደለም፡፡”

የአፉንም ንጽህና አጥብቆ ይከታተላል፡፡ በአፉ ሽታ ሰውን ማወክ አይሻም፡፡ እናም በየቀኑ መፋቂያ በመጠቀም የጥርሱንንጽህና ይጠብቃል፡፡ የጥርሱን ጤንነት በየጊዜው ይከታተላል፡፡ የጥርስ ሐኪም ያማክራል፡፡ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜየአፉን ጤንነት ሐኪም ዘንድ በመሄድ ይከታተላል፡፡ በዚህ ሁኔታ አፉ ምንጊዜም ንጹህና ማራኪ ሆኖ ይኖራል፡፡

አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዳስተላለፉት በአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በቀንወይም በሌሊት ከእንቅልፍ ሲነቁ መጀመሪያ የሚፈጽሙት ተግባር መፋቂያ መጠቀም ነው፡፡ ውዱእ ሳያደርጉ በፊትጥርሳቸውን ይፍቃሉ፡፡ (አህመድ እና አቡ ዳውድ)

ለጥርስ ንጽህና ከፍተኛ ጉጉት ስለነበራቸው እንዲህ በማለት እስከመናገር ደርሰዋል፡፡

“በተከታዮቼ ላይ ችግር የማያስከትል ቢሆን ኖሮ በየሶላት ወቅቱ መፋቂያ እንዲጠቀሙ ባዘዝኳቸው ነበር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ ወደ ቤታቸው ሲገቡ የሚሰሩት የመጀመሪያ ስራ ምን እንደሆነ አኢሻ ተጠይቀው “ጥርሳቸውን ይፍቁነበር፡፡” ብለዋል፡፡ (ሙስሊም)

አንዳንድ ሙስሊሞች አፋቸው ገምቶና ሰውን ከሩቅ የሚገፈትር አስቀያሚ ሽታ ተሸክመው ማየት ያሳዝናል፡፡ የአፍንጽህናን መጠበቅ ከኢስላም አብይ ክንውኖች መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

የአፍ፣ የአካል እና የልብስ ንጽህና ሳያስጨንቃቸው በየመስጊዶችና የኢልም ቦታዎች በከረፋ ሽታ አማኙን ማጨናነቅኢስላማዊ አይደለም፡፡ ወንድሞቻቸውን በመጥፎ ሽታ ያውኩ፡፡ መላኢኮችን ከቦታው ያባርራሉ፡፡

የሚገርመውሽንኩርት የበላ ሰው መላኢኮችን እንዳያውክ ወደ መስጊድ አፉን ሳያጸዳ አይሂድ የሚለውን ነብያዊ ሐዲስ ዘወትር የሚሰሙ እና የሸመደዱት መሆናቸው ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህብለዋል፡-

“ነጭ ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ መስጊዳችንን አይቅረብ፡፡ በአፉ ጠረን መላኢኮችን እንዳይረብሻቸው፡፡” (ሙስሊም)

መጥፎ የአፍ ጠረን የሚያመጣ ነገር የተመገቡ ሰዎችን በአፋቸው ሽታ መላኢኮችን እና ሰዎችን እንዳይረብሹ በማለትመስጊድ እንዳይገቡ ነብዩ ከልክለዋቸዋል፡፡ በእርግጥም የነጭና የቀይ ሽንኩርት ሽታዎች ለንጽህናቸው ግድ ከሌላቸውዝርክርኮች አካል ከሚመነጨው የአፍ ፣የልብስና የካልሲ ሽታ ጋር የሚወዳደሩ አይደሉም፡፡ ቀለል ይላሉ፡፡ ቢሆንም ነቢዩሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከልክለዋቸዋል፡፡

ኢማም አህመድና ነሣኢ ባሰፈሩት ዘገባ እንደተወሳው ጃቢር እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከኛ ዘንደ መጡ፡፡ ሊጠይቁን ነው አመጣጣቸው፡፡ ልብሱ የቆሸሸ አንድ ሰውተመለከቱ፡፡ “ይህ ሰው ልብሱን የሚያጥብበት ነገር የለውምን?” ፡፡

ሰውየው ልብሱን ማጠብና ማጽዳት እየቻለ ከነቆሻሻው ከሰዎች ፊት መቅረቡን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አልወደዱለትም፡፡ ይህ የመልእክተኛው ስሜት ሙስሊም ሁሌም ንጹህና ማራኪ እንዲሆን ካላቸው ፍላጎትየመነጨ ነው፡፡ እንዲህ ይሉ ነበር፡-

“ከናንተ አንዳችሁ ለጁሙዓ ቀን ከስራ ልብሱ የተለየ ሌላ ልብስ ቢኖረው መልካም ነበር፡፡” (አቡ ዳውድና ኢብኑ ማጃህ)

ኢስላም በበርካታ ድንጋጌዎች ልጆቹን በንጽህና ያዛል፡፡ ሁሌም ንጹህና ማራኪ እንዲሆኑ ይሻል፡፡ አካላቸውን ታጥበውናአጽድተው፣ ልብሳቸውን አጥበው ንጽህናቸውን ጠብቀው፣ ሽቶ አርከፍክፈው ማራኪ ሽታ ከነርሱ እንዲመነጭያስተምራቸዋል፡፡

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በባህሪያቸው እንዲህ ነበሩ፤ ሁሌም ንጹህና ማራኪ ሽታ ነበራቸው፡፡ሙስሊም እንደዘገቡት ማሊክ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

ከአላህ መልእክተኛ ይበልጥ የሚያውድ ሽታ ያለው ሚስክ ወይም ሽቶ አሽትቼ አላውቅም፡፡ (አቡ ዳውድ)

የነቢዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የአካልና የልብስ ንጽህና የሚያወሱ፣ ሽታቸውና ላበታቸው እጅግ ይማርኩ እንደነበርየሚገልጹ ዘገባዎች በርካታ ናቸው፡፡

አንድን ሰው በመዳፋቸው ከጨበጡት ያ ሰው ከእጁ ላይ የሚቀረውን ሽታ ቀኑን ሙሉ እያጣጣመ ይውላል፡፡ እጃቸውንከአንድ ልጅ ራስ ላይ ሲያስቀምጡ ያ ልጅ ከሌሎች ልጆች መሐል በማራኪ ሽታው ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ቡኻሪ ጃቢርንበመጥቀስ እንደዘገቡት ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በአንድ መንገድ ሲያልፉ ጠረናቸውን መከተል ይቻል ነበር፡፡

አንድ ቀን ከአነስ ቤት ተኙ፡፡ ላበት ወጣቸው፡፡ የአነስ እናት እቃ አመጣችና ላበታቸውን እየጠረገች ከእቃ ውስጥ ታደርግጀመር፡፡ ለምን እንዲህ እንደምታደርግ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጠየቋት፡፡ “ከሽቶ ጋር ልቀላቅለው ነው፡፡የርስዎ ላበት ከየትኛውም ሽቶ የበለጠ ይጣፍጣል፡፡” አለች፡፡ (ሙስሊም)

ሙስሊሞች ከዚህ የአላህ መልእክተኛ ባህሪና ተሞክሮ እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ይቀስማሉ፡፡

መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ረገድ ካስተላለፏቸው መመሪያዎች መካከል ተከታዮቻቸው ጸጉራቸውንእንዲያስተካክሉ፣ እንዲያበጥሩ፣ በአግባቡ እንዲይዙ ማዘዛቸው ይጠቀሳል፡፡ አቡ ዳውድ አቡ ሀረይራን ጠቅሰውበዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

“ጸጉር ያለው ሰው ይንከባከበው፡፡”

ጸጉርን መንከባከብ ማለት ማበጠር፣ ንጽህናውን መጠበቅ፣ ሽቶ መቀባትና ማበጃጀት ማለት ነው፡፡ ሰውየው ጸጉሩንእንዲሁ ልቅ አድርጎ ንጽህናውንና ውበቱን ሳይጠብቅ መተውን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሰይጣንመስለውታል፡፡ ኢማሙ ማሊክ አጧእ ቢን የሳርን በመጥቀስ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምመስጊድ ውስጥ ነበሩ፡፡ አንድ ሰው ጸጉሩ እና ጺሙ እንደተንጨባረረ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት፡፡ ጸጉሩንና ጺሙንእንዲያበጃጅ በምልክት ነገሩት፡፡ አበጃጀቶ ተመለሰ፡፡ ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡-

“ከናንተ አንዳችሁ ጸጉሩን ልክ እንደሰይጣን አንጨባርሮ ከሚመጣ ይህ የተሻለ አይደለምን?”

የአላህ መልእክተኛ ጸጉሩ የተንጨባረረውን ሰው በሰይጣን መመሰላቸው ኢስላም ለነገሩ ያለውን ከፍተኛ ጥላቻአመላካች ነው፡፡ ኢስላም ለላያዊ ገጽታ ውበት የሚሰጠውን ትኩረትም ያሳያል፡፡

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባልደረቦቻቸውን ስለ ውበት ምንጊዜም ከማስታወስ ተቆጥበውአያውቁም፡፡ የተዝረከረከ የሰውነት ይዞታ ሲመለከቱ ይነቅፋሉ፡፡

አህመድና ነሣኢ ጃቢርን በመጥቀስ ተከታዩን ዘግበዋል፡-

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከኛ ዘንድ ሊጠይቁን መጡ፡፡ ጸጉሩ የተንጨባረረ ሰውም ተመለከቱ፡፡ይህሰው ጸጉሩን የሚያበጃጅበት ነገር የለውምን?” ሲሉ ነቀፉት፡፡

ያማረ ገጽታ

ትክክለኛ ሙስሊም ለአለባበሱና ለአካላዊ ገጽታው ትኩረት ይሰጣል፡፡ እናም ማራኪ ገጽታ ያለው ሆኖ ይታያል፡፡የሰዎችን አይን ይማርካል፡፡ ተዝረክርኮና ተንዘላዝሎ ከሰው ፊት አይቀርብም፡፡ ከሰዎች ጋር ከመገናኘቱ በፊት ራሱን ያበጃጃል፡፡ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ይዋባል፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከቤተሰቦቻቸው አልፎለባልደረቦቻቸው ይዋቡላቸው ነበር፡፡

በኢማም ቁርጡቢ የቁርአን ማብራሪያ ላይ፡-

“ለባሮቹ ያወጣቸውን ጌጦችና ከሲሳይም በጎዎችን እርም ያደረገ ማን ነው?” ለሚለው የቁርአን አንቀጽ ቁርጡቢበሰጡት ማብራሪያ እንዳመለከቱት አኢሻ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡-

“የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባልደረቦቻቸው በር ላይ ይጠብቋቸው ነበር፡፡ ወደነርሱ አቀኑ፡፡ በር ላይውሃ የያዘ ገበታ ነበር፡፡ በውሃው ውስጥ ራሳቸውን እያዩ መበጃጀት ጀመሩ፡፡ ጸጉራቸውንና ጺማቸውን ያስተካክሉ ጀመር፡፡

“እርስዎም እንዲህ ያደርጋሉን (ለውበት ይጨነቃሉን)?” አልኳቸው፡፡ “አዎ፣ ሰውየው ወደ ወንድሞቹ በሚሄድ ጊዜ ራሱን ማበጃጀት አለበት፡፡ አላህ ውብ ነው፡፡ ውበትን ይወዳል፡፡” አሉ፡፡

ሙስሊም ይህን ሁሉ ሲያደርግ የኢስላምን የሚዛናዊነት መርህ በተከተለ መልኩ ነው፡፡ አላህ ምጽዋትን በማስመልከትየአማኞችን ባህሪ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡-

وَالَّذِينَ إِذَا أَنفَقُوا لَمْ يُسْرِفُوا وَلَمْ يَقْتُرُوا وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا

“እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው፡፡” (አል ፉርቃን፤ 67)

ይህ መርህ በሁሉም ቦታዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ሙስሊሞች አይኖች ሊያዩአቸው የሚጠየፏቸው አስቀያሚዎችሳይሆን ለአይን የሚማርኩ ደማቅና ጉልህ በመሆን በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲታዩ ኢስላም ይፈልጋል፡፡

ለዚህች ዓለም ግዴለሽ መሆን (ዛሂድ) በሚል እና ራስን በማስተናንሰ (በትህትና) ሰበብ ሰውየው ራሱን መርሳት እናመዝረክረክ የለበትም፡፡ የዛሂዶችና የትሁቶች ፈርጥ የሆኑት የአላህ መልእክተኛ የተዋቡ ልብሶችን ይለብሱ ነበር፡፡ለቤተሰቦቻቸው ይዋቡ ነበር፡፡ መዋብንና መበጃጀትንም የአላህን ጸጋ ይፋ ከማድረግ ቆጥረውታል፡፡ እንዲህ ብለዋል፡-

“አላህ የጸጋው ፋና ከባሪያው ላይ እንዲታይ ይፈልጋል፡፡” (ቲርሚዚ)

ጦበቃት ቢን ሰእድ ውስጥ እንደተዘገበው ጀንደብ ቢን መኪስ የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡-

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አንድ ልዑክ ከርሳቸው ዘንድ በመጣ ጊዜ ያማሩ አልባሳትን ይጎናጸፋሉ፡፡ሶሐቦቻቸውም ይህንኑ እንዲያደርጉ ያዛሉ፡፡

አንድ ቀን አንድ ልዑክ መጣ፡፡ ከኪንዳህ የመጣ ነው፡፡ መልእክተኛው ከየመን የመጣች ጥሩ ልብስ ነበረቻቸውና እርሷንተጎናጸፉ፡፡ አቡበክርም እንደዚሁ አደረጉ፡፡

ኢብን ሙባረክ፣ ጦበራኒ፣ ሐኪም፣ በይሐቂና ሌሎችም ዑመርን አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ዋቢበማድረግ እንደዘገቡት፡-

የአላህ መልእክተኛ አንድ ቀን ቆንጆ ልብስ ለበሱና እንዲህ አሉ፡-

“ሐፍረተ ገላዬን የምሸፍንበትን እና የምዋብበትን ልብስ የሰጠኝ አላህ የተመሰገነ ይሁን፡፡”

አብዱረህማን ቢን አውፍ አምስት መቶ ወይም አራት መቶ የሚያወጣ (ውድ) ልብስ ይለብሱ ነበር፡፡ ኢብን አባስ በአንድሺህ ዲርሃም ልብስ ገዝተው ለብሰዋል፡፡ መዋብ አለቅጥ ወሰን የማለፍ ደረጃ ላይ ካልደረሰ አላህ የፈቀደው እናያበረታታው መልካም ጌጥ ነው፡፡

قُلْ مَنْ حَرَّمَ زِينَةَ اللَّهِ الَّتِي أَخْرَجَ لِعِبَادِهِ وَالطَّيِّبَاتِ مِنَ الرِّزْقِ ۚ قُلْ هِيَ لِلَّذِينَ آمَنُوا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا خَالِصَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

“«የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው፡፡ «እርሷ በትንሣኤ ቀን ለእነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት ተገቢያቸው ናት» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ «ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡” (አል አእራፍ፤ 32-33)

ኢብን መስዑድን በመጥቀስ ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ፡- “ከልቦናው ውስጥ ቅንጣት ታክል ኩራትያለበት ሰው ጀነት አይገባም፡፡” በማለት ተናገሩ፡፡ “ሰውየው ልብሱ እና ጫማው ጥሩ እንዲሆንለት መሻቱ ከኩራትይቆጠራልን?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡-

“አላህ ውብ ነው፡፡ ውበትን ይወዳል፡፡ ኩራት ማለት ሐቅን አለመቀበልና ሰዎችን ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው፡፡”

ሶሐቦችና የነርሱን ፈለግ የተከተሉ ሁሉ ይህን ግንዛቤ አጽድቀዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ኢማም አቡ ሐኒፋ ምንጊዜምገጽታቸውን የሚጠብቁ፣ በመልካም ሽታ የሚያውዱ ነበሩ፡፡ ሁሌም ውበታቸውን ይጠብቃሉ፡፡ በአለባበስ ይከሸናሉ፡፡ለዚህ አጀንዳ ከፍተኛ ትኩረት ከመስጠታቸው የተነሳ ሰዎችን ለዚህ ተግባር ያነሳሱ ነበር፡፡

አንድ ቀን ከአጠገባቸው ከተቀመጡ ሰዎች መካከል አንዱ ቆሻሻ ልብስ ለብሶ አዩትና ለብቻው ጠርተው አዲስ ልብስይገዛበት ዘንደ አንድ ሺህ ዲርሃም ሰጡት፡፡ ሰውየውም፡- “እኔ እኮ ገንዘብ ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ ባለጸጋ ነኝ፡፡ ገንዘብ ከርስዎ የምፈልግ አይደለሁም፡፡” አላቸው፡፡ አቡ ሐኒፋም እንዲህ ሲሉ ወቀሱት፡-

“አላህ ጸጋው ከባሮቹ ላይ እንዲታይ ይፈልጋል፣ የሚለው ሐዲስ አልደረሰህምን? ራስህን ለውጥ፡፡ ወዳጅህእንዳያዝንብህ፡፡”

በተለይም ወደ አላህ ዲን ጥሪ የሚያደርጉ ሰዎች ላያዊ ገጽታቸው ያማረ ይሆን ዘንድ ጥንቃቄና ጥረት ሊያደርጉእንደሚገባ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ሰዎችን በበለጠ ለመሳብና ወደውስጣቸው ዘልቀው ለመግባት ያስችላቸዋል፡፡

በዚህ ረገድ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ አካላቸውን፣ ጸጉራቸውን፣ የአፋቸውን ጽዳት ሊጠብቁ ይገባል፡፡ብቻቸውን በሆኑበት ሰአት እንኳ ቢሆን፡ ለተፈጥሯዊ ጥሪያቸው ምላሽ መስጠት አለባቸው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

“አምስት ነገሮች የተፈጥሮ አካሎች ናቸው፡፡ ግርዛት፣ የብልትን ዙሪያ መላጨት፣ የብብትን ጸጉር መንጨት፣ ጥፍርን መቁረጥና ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

እናም ውጫዊ ገጽታን መጠበቅና አምሮና ተውቦ መገኘት የሰው ልጅ ተፈጥሮና ጤነኛ ስሜት የሚደግፉት፣ ዲንምያጸደቀው ተግባር ነው፡፡

ይህ ማለት ግን ሙስሊም የተጋነነ የውበት ግንዛቤ ይኖረዋል ማለት አይደለም፡፡ ሚዛን እስኪስት ድረስ ለአካላዊገጽታው ሲጨነቅ እና ሲጠበብ ይራኖራል ማለት አይደለም፡፡ ሙስሊም በማንኛውም ጉዳይ ምንጊዜም ሚዛናዊ ነው፡፡ሸሪዓው ያስተማረውን ሚዛናዊነት መቼም ቢሆን ይጠብቃል፡፡ አንድ የሕይወቱ ገጽታ ገዝፎና ገኖ ሌሎችን አይጋፋበትምወይም አይጨፈልቅበትም፡፡

መዋብንና ላያዊ ገጽታን ማሣመርን ያስተማረው ኢስላም በዚህ ረገድም ቢሆን ሚዛን መሳትን እንደከለከለው ሙስሊምአይዘነጋም፡፡ የአላህ መልእክተኛ የውበት፣ የፋሽንና የገንዘብ ባሪያ መሆንን እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡-

“የገንዘብ ባሪያ ጠፋ፡፡ የፋሽን ባሪያ ጠፋ፡፡ ሲያገኝ ደስ የሚለው፣ ሲከለከል የሚከፋው (ሰው ከሰረ)፡፡” (ቡኻሪ)

ወደ አላህ ጥሪ የሚያደርጉ ሰዎች ከእንዲህ ዓይነቱ ሚዛን መሳት ላይ ይወድቃሉ ተብሎም አይታሰብም፡፡ የዲኑአስተምህሮ እጃቸውን ይዞ ወደ ሚዛናዊነት ይመራቸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here