በአላህ መመካት

1
4124

አላህ!!! ከደቃቃዎቹ የሰውነታችን ህዋሳት ጀምሮ የምናውቃቸውንና የማናውቃቸውን ፍጥረታት ዘንድ የዘለቀው ጥንቃቄ እውቀቱ፣ ቃላቶች በማይገልፁት እርሱ በፈለገው መልኩ የሚገልፅበት ድንቅ ጥበቡ፣ ርህራሄውና እዝነቱ ምንኛ ሠፊ ነው?! ታዲያ በዚህ ፈጣሪ መመካት ለኛ ደካማ ፍጥረቶቹ አይገባንም ትላላችሁ?! በደስታም ይሁን በሀዘን፣ በስኬትም ሆነ በውድቀት፣ በሁሉም የህይወታችን መስክ መመኪያችን አላህና አላህ ብቻ ሊሆን ይገባል።

ከመመካት በኩልም ከርሱ ሌላ ማንም እንደማያስፈልገን ልናምን ይገባል።

سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ﴿﴾ لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴿﴾ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ ﴿﴾ هُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِي الْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ السَّمَاءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ ﴿﴾ لَّهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ ﴿﴾ يُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَيُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ وَهُوَ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ ﴿﴾

“በሰማየትና በምድር ያለው ሁሉ አላህ አሞገሰ፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው። የሰማያትና የምድር ንግስና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ይገድላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ ግልጽም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው። እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የሚገባውን ከርሷም የሚወጣውን ከሰማይም የሚወርደውን በርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፤ እርሱም የትም ብትሆኑ ከናንተ ጋር ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው። የሰማያትና የምድር ንግስና የርሱ ብቻ ነው፤ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ። ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፤ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን አዋቂ ነው።” (አል-ሀዲድ 57፡1-6)

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴿﴾ وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ ﴿﴾

“በዚያም ቀን ከርሱ ላይ ቅጣት የሚመለስለት ሠው (አላህ) በርግጥ አዘነለት፤ ይህም ግልጽ ማግኘት ነው። አላህም በጉዳት ቢነካህ ለርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ ሌላ አስወጋጅ የለም፤ በበጎም ነገር ቢነካህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።” (አል-አንዓም 6፡17-18)

እስቲ ለደቂቃዎች በዚህ ሀዲስ ውስጥ የተወሳውን ድንቅ መልዕክት እናስተውል። ኢማም ቲርሚዚ ከኢብን አባስ የተወራውን ሀዲስ እንዲህ ዘገቡት:-

ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ወቅት ከነቢዩ ጋር ነበርኩኝ እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ:- ልጄ ሆይ! ጥቂት ቃላትን አስተምርሀለሁ! አላህን አስታውስ እርሱ ይጠብቅሀል፤ አላህን አስታውስ ቅርብህ ሆኖ ታገኘዋለህ፤ መጠየቅህ የፈለግክ ጊዜ አላህን ብቻ ጠይቅ፤ እርዳታን ስትሻ ከአላህ ብቻ እርዳታን ፈልግ፤ ጠንቅቀህ እመን፣ አላህ ይጠቅምህ ዘንድ የወሰነው እንጂ ፍጥረታት ሁሉ ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አይጠቅሙህ፤ እንዲሁም ፍጥረታት ሁሉ ሊጎዱህ ቢሰባሰቡ በአንዳች አይጎዱህም በእርግጥ አላህ ሊጎዱህ ቢወስነው እንጂ።” (አል-ቲርሚዚ ሀዲስ ቁጥር 2442)

በአላህ ብቻ መመካት የእምነታችን አንድ ክፍል ነው። እኛ የተውሂድ ህዝቦች ነን። ተውሂድ (አላህን ብቻ መገዛት) የስብዕናችን፣ የባህሪያችንና የህይወታችን መሰረት ነው። በአላህ ላይ በመመካት ላይ የተገነባ ተውሂድ የሚከተሉትን ፍሬዎች ያፈራል፡-

  1. በራስ መተማመን፡- የተውሂድ ሰው ኃይልና ችሎታ ሁሉ ለአላህ ብቻ የተገባ መሆኑን ያምናል። ማንም ከአላህ ውጪ በምንም ሁኔታ ኢምንት ሊለግስም ሆነ ሊነሳ እንደማይችል ይገነዘባል። ይህም ልቡን በከፍተኛ ራስ መተማመን ይሞላዋል። የተውሂድ ሰው፣ ለሰው በማጎብደድና ለፍጥረታት በመስገድ ራሱን አያዋርድም። በሰዎች ስኬትም ቅጥ ባጣ ሁኔታ አይገረምም። ክብሩ መጠን አለው። ተውሂዱ ልቡን በቁርጠኝነት፣ በትዕግስትና በፅናት ሞልቶታል። በየትኛውም ችግር አይንቀጠቀጥም፤ እጁን ለዱንያ ፈፅሞ አያስገዛም። ፈፅሞ!! እምነቱ በአላህ ላይ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ለፈጣሪው እጁ በመስጠቱ፣ ተውሂድን ወደ መቀበሉ የለገሰው ድንቅ ስጦታ ነው።
  2. መተናነስና ቁጥብነት፡- የተውሂድ ሰው ለህይወቱ የህሊና ልጓም ያበጃል። የልቅና ባለቤት፣ የስጦታዎች ለጋሽ፣ የሰጠውንም የሚነሳ አላህ ብቻ እንደሆነም ያውቃል። ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ ይጥቀምም ይጉዳ፣ ይጨምርም ይቀንስ፣ ሞትም ይሁን ህይወት፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት፣ ጤናም ሆነ ህመም፣ ሀብትም ይሁን ድህነት፣ የዚህች ዓለም ክስተት ሁሉ በፈጣሪው ፍቃድ እንደሚከወኑ ጠንቅቆ ይረዳል። ስለዚህ፤ አይኮራም። ስላዚህ፤ ማናለብኝነት ልቡን አያሳብጠውም። የተውሂድ ሰው ሁሌም አመስጋኝ፣ ሁሌም የጌታውን ፀጋ አዋቂ፣ ሁሌም ለአላህ የሚተናነስ ነው።
  3. መልካም ስብዕና፣ ትዕግስተኝነትና ብሩህ አዕምሮ፡- አንድን ፈጣሪ ብቻ መገዛት መልካም ስብዕና ለመያዝ እጅግ ያስፈልጋል። የተውሂድ ሰው በአንድ ፈጣሪ ህግ ብቻ ይዳኛል። ለማንም ሰው አድሏዊ ውሳኔ አይሰጥም። ማንንም አይበድልም፣ በማንም ላይ ወሰን አያልፍም። ፍጥረታት ሁሉ የአላህ ብቻ እንደሆኑ ይገነዘባል። ይህም የብሩህ አእምሮ ባለቤት ያደርገዋል። ችግሮችን በትዕግስት ያልፍ ዘንድ ይረዳዋል። ምክንያቱም፤ ይሄ የዚህኛው ፈጣሪ ያኛው ደግሞ የሌላኛው የሚለው ንብረት የለውም። አዕምሮው ሰላም አለው። የመረበሽ ህይወት በውስጡ የለም።
  4. ፍፁም ሰላምና መረጋጋት፡- የተውሂድ ሰው ጥላቻን አይወድም፣ ለምቀኝነትና ፀብም ቦታ አይሰጥም። መሠረቱ ሰላም ነው። ለራሱ ስኬት የሌሎችን ቀብር አይቆፍርም። የራሱን ቪላ ለመገንባት የሰዎችን ድንኳን አያፈርስም፤ ፀጥታን አያደፈርስም። ይልቁንስ፤ ከአላህ ዘንድ በተሰጠው ሰላም ይኖራል። ፍፁም እርካታ ያገኛል። እምነቱ ሁሌም እንዲለፋ፣ ጥሩን እንዲሰራና በአላህ እንዲተማመን ያግዘዋል። ድንቅ እምነት! ኢስላም!

1 COMMENT

  1. Could you please check the translation for Sura Al-Hadid discussing about the Creation of Heavens & Earth.

    You do not provided the full translation.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here