ሜክሲኮ አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ጓደኛዬን እየጠበቅኩ ነው፡፡ ከተቀጣጠርን ሳፊ አንድ ሰዓት ሆኗል፡፡ ወዳጄ ግንእስካሁን ብቅ አላለም፡፡ ያዘዝኩት ሻይ ቀዝቅዞ የድመት አፍንጫ ሆኗል፡፡ አንድ ሻይ አዝዤ ይህን ሁሉ ሰዓት መቀመጤያበሳጫቸው አስተናጋጆች ደግሞ በዓይናቸው እያነሱ ይጥሉኛል፡፡ እኔን እያዩ ከርቀት ሲንሾካሸኩ እንደ ዕድር ዳኛ ወንበርይወዳል የሚሉኝ ይመስለኛል፡፡ ሰዎች ይገባሉ – ይወጣሉ … ሙዚቃው ጆሮን ይበጥሳል፡፡
መቼም ወዳጄ ኔትዎርክ ተመችቶታል፡፡ ደጋግሜ ብደውልም ስልኩ አይነሳም፡፡ መንገዱ ተዘጋግቶ፣ ታክሲ አጥቼ፣ ስልኬን ረስቼ፣የቤት ወጪ ሳልሰጣት ወጥቼ፤ ….. የማያልቁ መቶ ምክንያቶቹን እያሰብኩ ፈገግ አልኩ፡፡ መቀመጡ ሲሰለቸኝ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ያአላህ .. የሀኪም ቤት ቀጠሮዬ ደርሷል፡፡ አስተናጋጆቹ ሳያዩኝ ተነስቼ ሹልክ አልኩ፡፡ የታክሲው ወረፋ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ቢሆንምምርጫ የለኝም፡፡ እየተንፏቀቀ የሚሄደው ሰልፍ ላይ ከኋላ ተሸጎጥኩ፡፡ ወጪ ወራጁን እየታዘብኩ ከሃያ ደቂቃ በኋላ ታክሲ ውስጥገባሁ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡
እድሌ ሆኖ ጋቢና ደርሶኝ አያውቅም፡፡ አራተኛው ወንበር ላይ ተኮራምቼ ቁጢጥ አልኩ፡፡ አዲስ አበባ ዕድሳት ላይ ናት፡፡የትናንት መንገዶቿ ሁሉ ወደ ሰው ሰራሽ ገደልነት ተቀይረዋል፡፡ መኪኖቿም ቢሆን ሬሳ የጫኑ ይመስል እየተንፏቀቁ ነውየሚሄዱት፡፡ ከሰለሳ ሶስት ደቂቃዎች በኋላ ከታክሲ ወረድኩ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡
ቤት ገብቼ ብርድልብሴ ውስጥ እስክሸሸግ ቸኩያለሁ፡፡ ህሊናዬ ግን አላረፈም፡፡ ውሉዬን ደጋግሞ ያስታውሰኛል፡፡ያለአንዳች ፋይዳ የባከኑብኝ ሰዓቶች ነገ በአላህ ፊት እንደሚያስጠይቁኝ ሹክ እያለ ጭንቀቴን ያብሰው ጀመር፡
ያአላህ.. ሆስፒታሉ ተጨናንቋል፡፡ ካርድ ሳስወጣ ሰራተኛዋ ሳይገርማት አይቀርም፡፡ “ነገ ጠዋት ይሻልሃል” ብትለኝም”እጠብቃለሁ” ብያት ሞባይሌን አውጥቼ ጌም እየተጫወትኩ መጠበቅ ጀመርኩ ሰላቴን እንደነገሩ ወጋ ወጋ አድርጌቦታዬ ተመለስኩ፡፡ ሰዓቱ እየሮጠ ነው፡፡ ወረፋው ግን ንቅንቅ አላለም፡፡ ሞባይሌ ባትሪ ጨርሷል፡፡ አንዲት ጀማሪ ነርስምንም ሳይመስላት ዶክተሩ እንደወጣና ተረኛ ሌላ ዶክተር ሊያየን እንደሚችል አሳስባን ሄደች፡፡ ያአላህ.. አንድም የረባቁምነገር ሳላከናውን ፀሀይ ወጥታ ጠለቀች…!
ቤት ገብቼ ብርድልብሴ ውስጥ እስክሸሸግ ቸኩያለሁ፡፡ ህሊናዬ ግን አላረፈም፡፡ ውሉዬን ደጋግሞ ያስታውሰኛል፡፡ያለአንዳች ፋይዳ የባከኑብኝ ሰዓቶች ነገ በአላህ ፊት እንደሚያስጠይቁኝ ሹክ እያለ ጭንቀቴን ያብሰው ጀመር፡፡ ውዱዕአድርጌ ሁለት ረከዓ ሰገድኩና መስገጃዬ ላይ ተደፍቼ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ አዛኝ የሆነውን አምላኬን ማረኝ እያልኩእስቲግፋር ሳደርግ ረጅም ሰዓታት ቆየሁ፡፡
ቀልቤ ሲረጋጋ ውሎዬን ተመልሼ ቃኘሁት፡፡ ጓደኛዬን ስጠብቅ ከአባከንኩት ሰዓት ጀምሬ እስካሁን ያለውን ደቂቃ በሙሉአሰላሁት፡፡ በትንሹ በጉዞና በጥበቃ ከስምንት ሰዓታት በላይ አባክኛለሁ፡፡
ያአላህ በነዚህ ሰዓታት ስንት ጁዝ ቁርአን መቅራት እችል ነበር? በቀላሉ ዚክር ባደርግ እንኳ ስንት ዛፍ ጀነት ውስጥእተክል ነበር?
ሃዘኔን ውጬ ራሴን ማረጋጋት ጀመርኩ፡፡ ከተውበት ሸርጦች አንዱ መጸጸት መሆኑ ታወሰኝ፡፡ ልክ ነኝ.. ጸጸትተሰምቶኛል፡፡ ሌላኛው ሸርጡ ደግሞ ትዝ አለኝ… ድርጊቱን ዳግም አለመፈጸም ጥሩ ከነገ ጀምሮ እያንዳንዱን ደቂቃበዚክርና በቂርዓት ብሎም ለሎች መልካም ስራዎችን በመስራት ለማሳለፍ በቻልኩት ሁሉ ጥረት ለማድረግ ነየትኩ፡፡
ዛሬ አዲስ ቀን ነው፡፡ ብሩህ ዕለት፡፡ ማለዳ ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ጥበቃ ስቆም ተወዳጄን ዚክር .. “ሱብሃነላህወቢሃምዲሂ.. ሱብሃነላል-ዓዚም” ከመቶ ጊዜ በላይ ማለት ችዬ ነበር፡፡ አልሃምዱላሊህ! ታክሲ ውስጥ ሆኜ በዛ ያለእስቲግፋር ለማድረግ ታድዬ ነበር፡፡ ዛሬ የመንገድ መዘጋጋትም ሆነ ወረፋው ትዝ እንኳን አላለኝም፡፡ ሆስፒታል ቁጭ ብዬሞባይሌን ያወጣሁት እንደትላንቱ ጌም ለመጫወት ሳይሆን ቁርአን ለመቅራት ነበር፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ በአላህ ፈቃድከእንግዲህ የሚባከኑ ቀናት አይኖሩኝም፡፡
እናንተም ይህንን መንገድ በቀላሉ ልትሞክሩት ትችላላችሁ፡፡ እስቲ ከዚህ ጀምሩ
- ሞባይላችሁ ላይ ቁርዓን አስጭኑበት፣ በማንኛውም ሁኔታ ለመቅራት ይረዳችኋል፡፡
- ቦርሳችሁ ውስጥ ለዚክር የሚረዳችሁ ሙስበሃ ወይም ሌላ የመቁጠሪያ መሳሪያ አይጥፋ፡፡
- በመጠናቸው አነስ ብለው የተዘጋጁ ሁስኑል ሙስሊም ወይም ሌላ የአዝካርና የዱዓ መጽሃፍትንየመታወቂያችሁን ያህል ዋሌታችሁ ወይም ቦርሳችሁ ውስጥ ቦታ ያዙላቸው፡፡
- ዚክሮች ላይ ጎበዝ የሆኑ ወዳጆችን በመግባባት ባህሪያቸውን ለመውረስ ጣሩ፡፡
- እጅግ በርካታ ጥቅሞች ምንጭ የሆነውን ሰለዋት በየቀኑ ከሰላሳ ያላነሰ ለማለት ሞክሩ፡፡
I found the articles very helpful. thank you and keep up your nice work.