የኢስላማዊ አካባቢ ጥቅም

0
2405

አካባቢ ምንድን ነው?

“አካባቢ ማለት በዙሪያችን የከበበን ሁሉንም ሁኔታዎች፣ ክስተቶች እንዲሁም ጫናዎችን ያጠቃለለ፤ በአካባቢው በሚኖር አንድ ፍጡርም ሆነ የፍጡራን ስብስብ ላይ በጥሩም ይሁን በመጥፎ ተጽእኖ ማሳደር የሚችል ነገር ነው።”

ማንኛውም ነገር አካባቢ ያስፈልገዋል። አንድ ነገር ትክክለኛ (የሚያስፈልገውን) አካባቢ ካገኘ ያድጋል፣ ይበለፅጋል ካልሆነ ደግሞ እድገት አይኖረውም፤ ቢያድግም ትክክለኛ እድገት አይዝም።

የተለያዩ የአካባቢ አይነቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ተፈጥሮአዊ አካባቢና ማህበራዊ አካባቢ ይገኙበታል። ተፈጥሮአዊ አካባቢ የምንለው ንፁህ አየር፣ ንፁህ ውሀ፣ ጥሩ ምግብ ሲኾን፤ ማኅበራዊ አካባቢ የምነለው ደግሞ ጥሩ ቤተሠብ፣ ጥሩ ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታ፣ ጥሩ ፖለቲካዊ አየር፣ ጥሩ ትምህርት፣ ጥሩ ጓደኞች እንዲሁም ጥሩ ጎረቤቶች ናቸው።

በቁርዓንና በሐዲስ ውስጥ መልካም ሠው ስለመሆን ብዙ ትንታኔ ተሠጥቷል። ይህም ብቻ አይደለም አንድ ሠው ምንግዜም ከጥሩ ሠዎች ጋር ለመዋልና አካባቢውን ጥሩ ለማድረግ መልፋት እንዳለበት ተነግሯል። ይህንን ከሚዳስሱ የቁርኣንና የሐዲስ አናቅጾች ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል፡-

وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَارْكَعُوا مَعَ الرَّاكِعِينَ

“ሶላትንም፣ ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም (ግዴታ ምፅዋትን) ስጡ፤ (ለጌታችሁ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ” (አል-በቀራ 2፤43)

يَا مَرْيَمُ اقْنُتِي لِرَبِّكِ وَاسْجُدِي وَارْكَعِي مَعَ الرَّاكِعِينَ

“መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፤ ስገጂም፤ ከአጎንባሾች ጋር አጎንብሺ።” (ኣሊ-ዒምራን 3፤43)

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞችም ጋር ሁኑ።” (አት-ተውባህ 9፤119)

وَاصْبِرْ نَفْسَكَ مَعَ الَّذِينَ يَدْعُونَ رَبَّهُم بِالْغَدَاةِ وَالْعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجْهَهُ وَلَا تَعْدُ عَيْنَاكَ عَنْهُمْ تُرِيدُ زِينَةَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُ عَن ذِكْرِنَا وَاتَّبَعَ هَوَاهُ وَكَانَ أَمْرُهُ فُرُطًا

“ነፍስህንም ከነዚያ ጌታቸውን ውዴታውን የሚሹ ሆነው በጧትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ፤ የቅርቢቱንም ሕይወት ሽልማት የምትሻ ኾነህ አይኖችህ ከነሱ (ወደ ሌላ) አይለፉ። ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሠን ማለፍ የኾነውን ሠው አትታዘዝ።” (አል-ከህፍ 18 ፤28)

አላህ (ሱ.ወ) የዒሳን (ዐ.ሰ) የአምልኮ ስርዓት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል።

فَلَمَّا أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ الْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِي إِلَى اللَّهِ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ اللَّهِ آمَنَّا بِاللَّهِ وَاشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ رَبَّنَا آمَنَّا بِمَا أَنزَلْتَ وَاتَّبَعْنَا الرَّسُولَ فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

“ዒሳ ከነርሡ ክህደት በተሠማውም ጊዜ ወደ አላህ (ተጨምረው) ረዳቶቼ እነማን ናቸው? አለ። ሐዋሪያቱም፡- እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህ አምነናል እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር አሉ። ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አመንን፤ መልዕክተኛውንም ተከተልን ከመስካሪዎችም ጋር መዘገብን (አሉ)።” (ኣሊ-ዒምራን 3፤52-53)

በቅዱስ ቁርኣንም ውስጥ ጥሩ ወዳጆች እንድናፈራና መልካም አካባቢን እንድንፈጥር ነግሮናል።

وَإِذَا رَأَيْتَ الَّذِينَ يَخُوضُونَ فِي آيَاتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ الشَّيْطَانُ فَلَا تَقْعُدْ بَعْدَ الذِّكْرَىٰ مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

“እነዚያንም በአንቀፆቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከርሱ ሌላ በሆነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፤ ሰይጣንም (መከልከልህን) ቢያስረሳህ ከትዝታ በኋላ ከበደለኞች ህዝቦች ጋር አትቀመጥ” (አል-አንዓም 6፣ 68)

وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَارُهُمْ تِلْقَاءَ أَصْحَابِ النَّارِ قَالُوا رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

“ዓይኖቻቸውም ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ፡- ‘ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን’ ይላሉ።” (አል-አዕራፍ 7፤47)

وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ

“እርሷም እንደ ተራራዎች በኾነ ማዕከል ውስጥ በነርሡ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትኾን (በአላህ ስም ተቀመጡበት)። ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ፡- ልጄ ሆይ ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሀዲዎችም አትሁን ሲል ጠራው።” (ሁድ 11፤42)

የአላህ መልክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ምንግዜም ከመልካም ሠዎች ጋር መሆንና ጥሩ ጓደኛ ማፍራትን ይመክሩ ነበር። የጥሩ ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ሻጭና እንደ እንጥረኛ ነው። ከሽቶ ሻጭ ጋር ከዋልን ጥሩ ሽቶ እንገዛለን ወይም ጥሩ ሽታ ያውደናል። ነገር ግን ከአንጥረኛ ጋር ስንውል ልብሳችን ይቃጠላል አልያም መጥፎ ሽታ ይደርሠናል። (ቡኻሪ)

“ማንኛውም ሠው ጓደኛውን ይከተላል እንዲሁም ይመስላል እና ጓደኛ አድርገን የምንይዘውን በአፅንኦት እንመልከት” (ሙስነድ አህመድ)

የዚህ ሀዲስ ዘጋቢ እንዲህ ሲሉ ማብራሪያ ይሠጣሉ፡- “የሠው ልጅ ባህሪ ተለዋዋጭ ነው። አካባቢው ወደ መልካምም ሆነ ወደ መጥፎ ሊያስጠጋው ይችላል።”

ኢማም አል-ገዛሊ “ከስግብግብ ሠው ጋር የሚደረግ ወዳጅነትም ሆነ መቀማመጥ የስግብግብነትን ባህሪን ያመጣብናል። እንዲሁም መብቃቃትን ባህሪው ካደረገ ሠው ጋር መዋልና መቀማመጥ የመብቃቃት ባህሪን ያላብሠናል። ለዱንያ መስገብገብን ያጠፋልናል። ምክንያቱም የሠው ልጅ ተፈጥሮ መከተልንና መመሳሰልን ያበዛልና።” ሲሉ ተናግረዋል።

ኢስላማዊ አካባቢን እንዴት እንፍጠር?

  1. በየመኖሪያ ቤታችን ኢስላማዊ አኗኗር መፍጠር በየግድግዳዎች ላይ መልካም የሆኑ ጌጣጌጥና ቁርአናዊ ጥቅሶችን መጠቀም ጥሩ መፅፎችን ማንበብ መልካም የሆኑ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን መከታተል
  2. ሐላል የሆነ ገቢ እንዲኖረን ማድረግና ሐላል መመገብ፣ ሐላል የሆነ ገቢና ምግብ ሠውነትንም ሆነ ነፍስን ያበለፅጋል።
  3. ከሁሉም ሠዎች ጋር ወዳጃዊ የሆነ አቀራረብ እንዲኖረን ማድረግ፣ ግን ደግሞ የልብ ጓደኛ የምናረጋቸው ሠዎችን ሥነ-ምግባራቸው መልካም የሆነ እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም ለመልካምነት ለእርዳታና ለመሣሰሉት በጎ ምግባሮች የቆሙ ማህበሮችን መቀላቀል
  4. ሌሎችን በመልካም ባህሪያችንና ደግነታችን መማረክ በሌሎች ተጽዕኖ ሥር አለመውደቅ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here