የኢስላም ልዩ ባህሪያት (ክፍል 4) – መካከለኛነት (አል-ወሰጢያ)

0
3451

ኢስላም በነገሮች ሁሉ ላይ መካከኛ አቋም የሚይዝ ሲሆን ጠርዘኛነትንና አክራሪነትን (ጉሉው/ extremism)፣ በአንጻሩም ችልተኛነትን (ተቅሲር/ laxity) ያወግዘል። በኢስላም አንድን ነገር በጣም ማጥበቅ (ድንበር ማለፍ)ም ይሁን ነገሩን በአግባበቡ አለመፈጸም (ችላ ማለት) የተጠሉ ጉዳዮች ናቸው።

ኢስላም መካከለኛነት በተለያዩ ነገሮች ሊገለጽ ይችላል፡-

1. ኢሰላማዊ ህግ ግደታዎችን ሲደነግግና መብቶችን ሲሰጥ መካከለኛና ፍትሃዊ ስለመሆኑ

ነበያችን (ሶ.ዐ.ወ) ይህን ኢስላመዊ መርህ በተግባር የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ሰጥተውናል። እንዲህ ይላሉ፡-

إنما أهلك الذين قبلكم أنهم كانوا إذا سرق فيهم الشريف تركوه، وإذا سرق فيهم الضعيف أقاموا عليه الحد. وايم الله لو أن فاطمة بنت محمد سرقت لقطعت يدها

“ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ያጠፋቸው ከነሱ መካከል ሃይል ያለው ሰው የስርቆት ወንጅል ሲፈጽም ቅጣት ሳይፈጸምበት ያልፉታል። ደካማ ሰው በሰረቀ ጊዜ ግን ቅጣት ይፈጽሙበታል። በአላህ እምላለሁ (ልጄ) ፋጡማ ቢንት ሙሃመድ ሰርቃ ብትገኝ እጇን እቆርጣት ነበር!” (ቡኻሪና ሙስሊም)

የመሰናበቻ ሐጅ እየተባለ በሚታወቀው ሐጅ ላይ ባደረጉት እውቁ ንግግራቸውም እንድህ ብለዋል፡-

…وربا الجاهلية موضوع، وأول ربا أضع ربا عباس بن عبد المطلب فإنه موضوع كله

“…በጃሂልያ የወለድ ገንዘብ ለመክፈል የገባችሁት ቃል ውድቅ ነው፤ መጀመሪያ ውድቅ የማደርገውም (የአጎቴን) አባስ ቢን አብዱልሙጦብ ወለድ ነው።” (ሙስሊም)

2. ኢስላም ያልተበረዘና ያልተጣመመ ቀጥተኛ መንገድ ከመሆኑ አኳያ

ኢስላም ባለማውቅ እንደጠመሙት የነሳራዎች መንገድ ወይም እያወቁ እንደጠፉትና አላህ እንድተቆጣባቸው የአይሁድ መንገድ የተጣመመ ሳይሆን ቀጥ ያለና ትክክለኛው አለህ (ሰ.ወ) የመረጠው መንገድ ነው፤ አላህ ሱ.ወ እንድህ ይላል፡-

اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
 

“ቀጥተኛውን መንገድ ምራን። የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)።” (አል-ፋቲሃ 1፤6-7)

3. በኢስላም ሁሉም ህግጋቶቹና ሥርዓቶቹ እውነትንና ተአማኝነትን መሠረት ከማድረጋቸው አኳያ

ኢሰላማዊ ሸሪዓ (ህግ) የመልካም ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَاكُمْ أُمَّةً وَسَطًا لِّتَكُونُوا شُهَدَاءَ عَلَى النَّاسِ وَيَكُونَ الرَّسُولُ عَلَيْكُمْ شَهِيدًا
 

“እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልክተኛውም በናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ ምርጥ ሕዝቦች አደረግናችሁ።” (አል-በቀራ 2፤143)

كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ

“ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ታዛላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ።” (ኣሊ-ዒምራን 3፤110)

4. ኢስላም በእምነትና አምልኮት ጉዳዮች ሳይቀር መካከለኛ አቋም አለው

በኢስላም ማናቸውም ጥሩና ጠቃሚ ነገሮች አልተከለከሉም፤ በአንጻሩ ግን ለሰው ልጅ ጎጅና አፀያፊ የሆኑ ነገሮችን ኢስላም ከልክሏል።

ኢስላም አንድ ፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) መኖሩንና አምልኮም ለርሱ ብቻ የሚገባ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-

أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

“ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው። የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ።. ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት። እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።” (አል-አዕራፍ 7፤54-55)

ይህ በኢስላም ያለው አንድን ሐያል ፈጣሪ ብቻ የማመንና ማምለክ አቋም፤ ሐይማኖት የለሾቹ (ሙልሂድ/ atheist) ከሚያራምዱት በምንም አለማመንና እንዲሁም ከፈጣሪ ጋር ብዙ አማልክትን አድርገው ከሚገዙት (ሙሽሪኮች/ polytheists) ድንበር አላፊዎች መካከል ሆኖ እናገኘዋለን።

በኢስላም ነቢያትና መልክተኞች የተከበሩና አላህ (ሱ.ወ) ከሰው ልጆች የመረጣቸው መሆናቸው ይታመናል። ከዚህም በላይ እነሱን መከተልና ትእዛዛቸውን መፈጸም በማንኛውም ሙስሊም ላይ ግደታ ነው። ነገር ግነ ነሳራዎች ድንበር አልፈው እንደሚያደርጉት አምልኮት አይገባቸውም፤ በሌላም በኩል አይሁዶች እንደፈጸሙት ነብያቶች አይሰደቡም፤ አይካዱም። ስለዚህ ኢስላም በነብያት ጉደይም መካከለኛ አቋም አለው ማለት ነው።

ኢስላም የፈጣሪን ባህሪያትን በተመለከተም መካከለኛ አቋም ይዞ እናገኘዋለን። እርግጥ ነው አላህ (ሱ.ወ) ለታላቅነቱ የሚስማሙ ያማሩ ስሞችና ከፍ ያሉ ባህሪያት አሉት፤ ነግር ግን በዛቱም ይሁን በባህሪያቱ ፍጡራኑን አይመስልም፤ ብጤም የለውም፤ እርሱ ከሁሉም የተለየ ነው፤ በማለት ኢስላም ያስተምራል። አላህ (ሱ.ወ) እንደህ ይላል፡-

وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
 

“ለአላህም መልካም ስሞች አሉት። (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት። እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው። ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ።” (አል-አዕራፍ 7፤180)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here