መልካም የሆነ ሀላል የተቀባይነት መስፊርት ነው (አስረኛው ሀዲስ)

0
227

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَال: قَال رَسُول اللهِ صلى الله عليه وسلم “إنَّ اللهَ طَيِّبٌ لا يَقْبَل إلا طَيِّبًا، وَإِنَّ اللهَ أَمَرَ المُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ المُرْسَلينَ فَقَال تَعَالى: “يَا أَيُّهَا الرُّسُل كُلوا مِنْ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلوا صَالحًا”، وَقَال تَعَالى: “يَا أَيُّهَا الذِينَ آمَنُوا كُلوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ” ثُمَّ ذَكَرَ الرَّجُل يُطِيل السَّفَرَ أَشْعَثَ أَغْبَرَ يَمُدُّ يَدَيْهِ إلى السَّمَاءِ: يَا رَبِّ! يَا رَبِّ! وَمَطْعَمُهُ حَرَامٌ، وَمَشْرَبُهُ حَرَامٌ، وَمَلبَسُهُ حَرَامٌ، وَغُذِّيَ بِالحَرَامِ، فَأَنَّى يُسْتَجَابُ لهُ؟”.

رَوَاهُ مُسْلمٌ

አቡ ሁረይራ እንዲህ አሉ፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሚከተለውን ብለዋል፦ “አላህ መልካም ነው መልካምን እንጂ አይቀበልም አላህ መልእክተኞችን ባዘዘበት ጉዳይ ምእመናንም አዝዋል። አላህ እንዲህ አለ፦

﴿يا أَيُّها الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيَّباتِ واعمَلُوا صالحاً﴾ [المؤمنون: 51]

እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ሥራንም ሥሩ። እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ።

አላህም እንዲህ አለ

﴿يا أَيُّها الَّذِينَ آمَنُوا كلُوا مِنْ طَيِّباتِ ما رَزَقْناكُم﴾ [البقرة: 172]

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮች ብሉ። ለአላህም እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ አመስግኑ።”
ከዚያም ስለ አንድ ሰው አነሱ። (ኃይማኖታዊ) መንገድ ያረዝማል (ያበዛል)። ፀጉሩ ጨበሪያም፣ አቧራም ነው። እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ጌታዬ! ጌታዬ! እያለ ይጣራል። (ይህ ሰው) የሚበላው ሀራም፤ የሚጠጣው ሀራም፤ የተገነባው በሀራም ነው። እንዴት ተቀባይነት ያገኛል” ሙስሊም ዘግቦታል።

የሀዲሱ አሳሳቢነት

ይህ ሀዲስ የኢስላም መሠረቶች የሆኑት ህግጋት ከሚመሠረቱባቸው ሀዲሶች መሀከል የሚቆጠር ሀዲስ ነው። ሀላልን ለመያዝና ሀራምን ለመራቅ ፍቱን መንገድ ያስተምራል። ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ የሚወድ እንዲሁም ለራሱ የሚጠላውን ለወንድሙ የሚጠላ ግለሰብ  ያለበትን ማህበረሰብ ለማስገኘት ታላላቅ ፋይዳዎችና ሰፊ ጥቅሞችን ያካተተ ሀዲስ ነው። የሸሪአ ድንበር ላይ በረካ ባለው ሀላል ተብቃቅተው የሚቆሙ በደስታና በእርጋታ የሚኖሩ ሰዎች የሚፈጥሩበትን መንገድም ይጠቁማል።

የቃላትና ሀረጎች ፍቺዎች

  • ‹‹አላህ መልካም ነው››፦ ከጉድለት የጠራ ቅዱስ ነው።
  • ‹‹መልካምን አንጂ አይቀበልም››፦ ከገንዘብም ሆነ ከስራ ከብክለት የጠራና ሀላል የሆነ እንጂ አይቀበልም። ‹‹መልእክተኞችን ባዘዘበት ጉዳይ››፦ ሀላልን መብላት እንዳለባቸው ሁለቱንም ጭፍራዎች በተመሳሳይ ሁኔታ አዟል፤
  • ‹‹ጨበሪያም››፦ ባለመሞሸጡ ምክንያት ፀጉሩ የተበታተነ ወይም የተጠቀለለ
  • ‹‹አቧራም››፦ ጂሀድና ሀጅን ለመሰሉ አምልኮዎች በሚያደርገው ጉዞ ምክንያት የፀጉሩን ቀለም አቧራ ለውሶታል።‹‹እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ››፦ ዱአ ለማድረግና ለመማጸን እጆቹን ከፍ የደርጋል።
  • ‹‹እንዴት ተቀባይነት ያገኛል››፦ ባህሪው እንደተጠቀሰው ሆኖ ሳለ ጥያቄው እንዴት ተቀባይነት ያገኛል። አያገኝም!

ጥቅል ትርጓሜው

  1. ተቀባይነት ያለው መልካም ነገር

ይህ በአካል የሚፈፀሙ ተግባራትን፣ በገንዘብ የሚተገበሩ ስራዎችን፣ንግግሮችንና እምነትን ይጨምራል። አላህ (ሱ.ወ) መልካምና ንፁህ የሆነን፤ ከታይታ እና ከይስሙልኝ የጸዳን ስራ እንጂ አይቀበልም። ሀላል የሆነና ከሀራም የጠራን ገንዘብን እንጂ በፍፁም አይቀበልም። ከንግግር መልካም የሆነው እንጂ ወደርሱ አይወጣም። አላህ እንዲህ አለ፦

﴿إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ﴾ [فاطر: 10]

ሙእሚን ሁለመናው መልካም ነው። ልቡ ላይ ያለው ኢማን የጸዳ ነው፤ ምላሱ ላይ በሰፈረው ዚክርና አካሉ ላይ በሚነበበው መልካም ስራም የተዋበ ነው፤ ይህም የኢማን ፍሬ ነው።

  1. ስራ እንዴት መልካምና ተቀባይነት ያለው ሊሆን ይችላል?

ሙእሚንን ስራውን መልካም ከሚያደርጉትና ተቀባይነት ከሚያስገኙለት ተግባሮች ውስጥ የሚመገባቸው ምግቦች መልካምና ሀላል መሆናቸው ነው። በዚህ ሀዲስ ውስጥም ሀላልን በመብላት እንጂ ስራ ተቀባይነት እንደማይኖረው መረጃ አለ። ሀራም ስራን ያከስማል፤ ተቀባይነትም ያሳጣል። አላህ መልእክተኞችን ባዘዘበት ጉዳይ ሙእሚኖችንም አዟል። አላህ እንዲህ አለ፦


﴿يا أيها الرسل كلوا من الطيبات واعملوا صالحاً﴾
وقال الله تعالى:
﴿يا أيها الذين آمنوا كلوا من طيبات ما رزقناكم﴾

“እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ሥራንም ሥሩ። እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ።”

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮች ብሉ። ለአላህም እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ አመስግኑ።”

የዚህ ትርጓሜ መልእክተኞችና ህዝቦቻቸውን ከመልካም በመመገብ ወይም ሀላልን በመጠቀም እና መልካምን በመሰራት ታዘዋል። “መልካምን እንጂ አይቀበልም” የሚለው ንግግር ትርጓሜው፤ ስራዎች ደሞዝና መልካም ምንዳ ለማስገኘት የሚበቁት የተጠቀሰው መስፈርት ሲሟላ ብቻ ነው። ግዴታን ለመወጣት እና ፈርድን ለመስራት ያህል ብቻ ከሆነ ግን ተቀባይነቱም ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

  1. የዱዓን ተቀባይነት የሚያስገኙ ምክንያቶች

    • መንገድን ማስረዘም

ሀይማኖታዊ ጉዞ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል። አቡዳውድ ኢብኑ ማጃህ እና ቲርሚዝይ እንደዘገቡት የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ “ያለ ምንም ጥርጥር ሶስት ዱዓዎች (ጥሪዎች) ተቀባይነት አላቸው፤ የተበዳይ ዱዓ፣ የመንገደኛ ዱዓና የወላጅ ዱዓ ለልጅ።” መንገድ መቆረጥና መላን ማጣት ዱዓን ተቀባይነት ከሚያስሰጡ ምክንያቶች ዋነኛዎቹ ናቸው።

    • እጆችን ወደ ሰማይ መዘርጋት

ይህ ከዱዓ ስነስርኣቶች አንዱ ነው። ኢማም አህመድ እንደዘገቡት የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ “ አላህ እጅግ ለጋስና ሐያእ የሚያደርግ አምላክ ነው፤ አንድ ሰው እጆቹን ወደ እርሱ በዘረጋ ጊዜ ባዶ፣ ፍሬ አልባ ሆነው ሊመልሳቸው ያፍራል።”

በልመናህ አላህ ላይ ሙጥኝ ማለት፦ይህ የአሏህን (ሱ.ወ) ጌትነትና ለጋስነት ደጋግሞ በማውሳት ይፈጸማል።

    • የዱዓን ተቀባይነት ከሚከለክሉ ጉዳዮች መራቅ

የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲሱ ላይ እንዳመላከቱን በምግብ፣ መጠጥና ልብስ እንዲሁም ራስን በመገንባት ላይ በሀራም መጠቀም ዱዓን ተቀባይነት ያሳጣሉ።

ከሀዲሱ የምንቀስማቸው ትምህርቶች

  • ሀዲሱ በሀላል ብቻ መጠቀምንና ከእርሱ ውጪ ያሉ መንገዶችን መከልከልን አበክሮ ያስረዳል።
  • ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ የፈለገ ሰው ምግቡን መጠጡንና የመሳሰሉትን ከሀላል ብቻ ሊያደርግ ይገባል።
  • አሏህ (ሱ.ወ) ከሙእሚኖች መልካም ልግስናን ሁሉ ይቀበላል፤ ያሳድጋታል፤ ይባርካታልም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here