ኢኽላስን ለማዳበር የሚያስፈልጉ ወሳኝ ነጥቦች

0
1370

ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡት ነጥቦች እውነተኛውን ኢኽላስ ለማምጣት የሚያግዙ ሐሳቦች ናቸው፡፡

  1. አንድ ሰው በምንም ሁኔታው ውስጥ ሳለ በስራው ላይ ፈጣሪን እንጂ ፍጡርን መመልከት የለበትም፤ ሰዎች ከአላህ በላይ በአንዲትም ነገር አያብቃቁለትምና፡፡

 ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል፡ ‹‹ ለሰዎች ብሎ መስራት በአላህ ላይ ማጋራት (ሽርክ)  ነው፡፡ ለሰዎች ብሎ መስራትን መተው ታይታ (ሪያእ) ነው፡፡ ከሁለቱ መዳን ደግሞ ኢኽላስ ነው፡፡››

2. አንድ ሰው ውስጡና ውጪው አንድ አይነት መሆን አለበት፣ በግልጽ የሚያወራውና በድብቅ የሚያስበውም ተመሳሳይ መሆን አለበት፣ በውጪው አሳማሪ በውስጡ ደግሞ አበላሽ፣ በግልጽ ሲሆን ማር በድብቅ ደግሞ ጎምዛዛ ሊሆን አይገባም፡፡

ሰረ ሰቅጢ እንዲህ ይላሉ፡ ‹‹ በሌለው ነገር ላይ ለሰዎች ብሎ የተዋበ ሰው በአላህ ዘንድ ይወድቃል፡፡››

3. ከሰዎች ዘንድ የሚያገኘው ውዳሴም ሆነ ወቀሳ እኩል መሆን አለበት እንዲህ ተብሏል፡ ‹‹አላህ ዘንድ ምስጋና አግኝተህ ሰዎች ዘንድ አትወቀስም፡፡ አላህ ዘንድ ተወቅሰህ ደግሞ ሰዎች ዘንድ አትመሰገንም፡፡››
4. የራሱን ታማኝነት እያየ በነፍሱ መገረም የለበትም፤ በራስ መገረሙ ያጠፋዋልና፡፡ አዋቂዎች ለዚህ ነው ስራቸውን ተመልሶ ከመመልከት የሚታቀቡት አቡ ያዕቁብ ሱስዩ እንዲህ ይላሉ፡ ‹‹ ለኢኽላሳቸው መስተካከል ለራሳቸው ከመሰከሩ …ኢኽላሳቸው ራሱ ኢኽላስ ይፈልጋል፡፡ ››

አቡበክር አዲቃቅ እንዲህ ይላል፡ ‹‹የራሱን ኢኽላስ የሚመለከት ሁሉ ጎዶሎ ነው፤ አላህ ኢኽላሱን እንዲያጠራለት የሚፈልግ ሰው የራሱን ስራ (ኢኽላሱን) ከመመልከት ይቆጠብ፤ ያን ጊዜ ለአላህ ቅን (ሙኽሊስ) ይሆናል፡፡››

አቡ ዑስማን አልመግሪቢ እንዲህ ይላሉ፡ ‹‹ ኢኽላስ ማለት ለራስ  ድርሻዋን አለመፈለግ ነው፡፡ ይህ ጥቅሉ ኢኽላስ ሲሆን፤ ልዩ የሆነው ኢኽላስ ደግሞ ስራው በእነርሱ ላይ ያልፋል እንጂ በእነርሱ ውስጥ አያልፍም፡፡ እነርሱ ከጉዳዩ ውጭ ናቸው ከስራው ጋር ጥገኛ አይደሉም፡፡ ይህ ነው ልዩ ኢኽላስ ማለት›› የዚህ ንግግር ትርጉሙ፡ ‹‹ እነዚህ (ሙኽሊሶች) ከነፍሶቻቸው፣ ከስራቸው፣ ከኢኽላሳቸው ይጠፋሉ፡፡ ለእምነቱ ያጠራቸውን አላህን እንጂ ማንንም አይመለከቱም፤  እነርሱም እምነታቸውንም ለርሱ አጠሩ፡፡››

5. ማንኛውም ስራ በመጪው ዓለም ምንዳ እንደሚሰጠው መዘንጋት፤ አንድ ሰው ከስራው ለነፍሱ ድርሻ መፈለግ ላይ ወይም በውስጡ እንዲህ አይነት የተደበቀ ስሜት መኖሩን ልክ አይደለም አላህም ዘንድ ይህ ተቀባይነት የለውም አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል፡

إنما يتقبل الله من المتقين

‹‹አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው አለ፡፡›› አልማኢዳህ፤27

ስራዎች ምንም ያክል ቢገዝፉ አላህ ለባሪያው ካስቀመጠው ትንሹ ጸጋ ጋር አይመጣጠኑም፡፡ ለስራ ገጠመኝ ማግኘት ማግኘት ከአላህ ነው፤ እርሱ አላህ የመጀመሪያም የመጨረሻም የችሮታ ባለቤት ነው፡፡ አንድ ሙኽሊስ ስራን ሽልማት ከማግኘት ጋር (ለራስ መፈለግ) አቆራኝቶ አይመለከተውም፤ ስራን የሚመለከተው ከአላህ የሚገውን ምንዳ ነው፡፡ መልእክተኛው ሙሐመድ(ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ ‹‹ ማንም ሰው በስራው ጀነት አይገባም፡፡››  እንዲህ ተባሉ፡ ‹‹ አንተም ብትሆን?›› እንዲህ አሉ፡ ‹‹ እኔም ብሆን! አላህ በእዝነቱ እስካልሸፈነልኝ ድረስ፡፡››

6. ሪያእን (ታይታን) እና ዝንባሌን መከተል ወደ ውስጥ እንዳይሰራጭ መፍራት

ይህ ስሜት በቀላሉ አይታወቅም ሰውየውም አይሰማውም፣ ሰይጣን በውስጡ ይደብቀዋል ያጣምመዋል፡፡ ወደ ነፍሱ ይገባል፡፡ አንድ አማኝ ግልጽ ካደረገው ወንጀሉ ለመንቃት ተስፋ ያስቆርጠዋል፤ በውስጥ ለሚሰራው ወንጀል ዘወትር አብሮት ነው፡፡ በዚህም ለአላህና ለመጪው ዓለም ብሎ የሚያደርገውን አምልኮውንና ስራውን ያባክንበታል፡፡ ለዚህም ሰህል እንዲህ አለ፡ ‹‹ ሪያእ ምን እንደሆነ ሙኽሊስ የሆነ ሰው እንጂ ማንም ሰው አያውቅም፡፡ ምክንያቱም እርሱን ስለሚፈራ… ስለሚቆጣጠረው…ስለሚከታተለው ጥልቀቱንና መግቢያውን ያውቃል፤ ለነፍሱ አይዋሽም፣ መጥፎ ስራውን ለነፍሱ ያስጌጣል፤ ስለዚህ መልካም ሆኖ ታየዋለህ፡፡››

በዚህ ከባድ ኢኽላስ ምክንያት ሙኽሊሶች ጥቂት ሆኑ ሰህል በድጋ እንዲህ ይላል፡ ‹‹ የ “ላ ኢላሀ ኢለላህ” ባለቤቶች ብዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ ውስጥ ሙኽሊስ የሆኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡››

እነዚህ ከላይ የተጠቀስናቸው ነገሮች ኢኽላስ ሙሉ እንዲሆን የሚያግዙ አስፈላጊ ነጥቦች ናቸው፡፡ እድለኛና ደስተኛ የሆነ ሰው ሁሉንም ሲያገኝ ጥቂቶቹንም የሚያገኝ አለ፡፡ እንዳለው ኢኽላስና እድል መጠን ከዚህ ያገኛል፡፡


‹‹ኒያና ኢኽላስ›› ከተሰኘው መጽሐፍ በዶክተር ዩሱፍ አልቀርዳዊ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here