በሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅ

0
1232

በሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅ ሸሪዓዊ መሰረቱ ምን ይመስላል?

ኢስላም ከቆመባቸውመሠረቶች መካከልስለሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅአንዱ ነው።ይህን አስመልክተውነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ጦበራኒ በዘገቡት ሐዲስ “የሙስሊሞች ጉዳይ የማያስጨንቀው ሰው ከነርሱ አይደለም” ብለዋል።አንዳንድቀደምት አበዎች ይህ ሐዲስ ‹የእምነት 1/4ኛነው› ሲሉ ተሰምተዋል። ሙስሊም በዘገቡት ሌላም ሐዲሥነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.)እንዲህ አሉ፡-“ዲን (ኢስላም) ማለት ታማኝነትና መመካከር ነው” አሉ። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለማን?” በማለት ጠየቅናቸው።ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) “ለአላህ፤ ለመልዕክተኛው ለሙስሊም መሪዎችና ለጠቅላላውማኅበረሰብ ነው፤ ለአላህ፣ለመልዕክተኛው፣ ለሙስሊም መሪዎች ብሎም ለማኅበረሰቡ ታማኝነት ሳያሳይና መካሪ ሳይሆን ቀንና ለሊት የተፈራረቀበት ከነሱ አይደለም” አሉ።

አቡሁረይራ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ አሉ ብለዋል:- “አትመቀኛኙ፣ አትጨራረቱ፤ አትጠላሉ፣ጀርባ አትሰጣጡ፣ የአላህ ባሮችወንድማማቾች ሁኑ።ሙስሊም ለሙስሊም ወንድም ነው፤ አይበድለውም፤ አሳልፎም አይሰጠውም፤ አያዋርደውም፤ አይዋሸውም፤ አይንቀውም።ተቅዋ (የአላህ ፍራቻ) እዚህ ነው በማለት ወደ ደረታቸው አመለከቱ።አንድ ሙስሊም ወንድሙን መናቁለወንጀል በቂ ነው፤ ሁሉም ሙስሊም የሌላውን መስሊም ደም፤ ገንዘብን ክብር መንካት ክልክል ነው።”(ሙስሊም ዘግበውታል)

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) “አንዳችሁምአላመናችሁም ለራሳችሁ የምትወዱትን ለወንድማችሁእስካልወደዳችሁ ድረስ።” በሌላም ሐዲሳቸው፡- “በወንድሙ ጉዳይ ላይ ለሆነ አላህበርሱ ጉዳይ ላይ ይሆንለታል።ከአንድ ሙስሊም ላይ አንዲትን የዚህ ዓለምን ጭንቅ ያስወገደ አላህ ከትንሳኤቀን ጭንቅ አንዲትን ጭንቅ ያስወግድለታል፤ የወንድሙንነውሩን በዚህች ዓለም የሸፈነ አላህ የትንሳዔ ቀንነውሩን ይሸፍንለታል”ብለዋል።(ሙስሊም ዘግበውታል)

ጦበራኒ እንደዘገቡት ደግሞነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) “አንድ ሰው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስከዘወተረ ድረስ አላህ ባሪያውን በመርዳት ላይ ይዘወትራል” ብለዋል።ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ አልገዛሊ ይህንን ትርጉም ሲያጸኑ እንዲህ ይላሉ፡-“ኢስላም የተወሰኑ አሊያምብዙ ሰዎችን የሚያሰባስብማስተሳሰሪያ ብቻ አይደለም።ነገርግንበሰዎች እና በፈጣሪያቸው፣ አሊያም በሰውና በሰውትክክለኛ ትስስርን የሚፈጥር እውነታ ነው።ስለሆነም የእስልምና ተሸካሚ ባለቤቶች አላህ (ሱ.ወ) ያብራራውንና በሥሩ እንዲሰባሰቡ ያደረገውን የዐቂዳን ታላቅነት በትክክል ሊረዱ ይገባል።በሷ ላይምመተዋወቅና ለሷ ከጥበቃ አንፃር ለሷ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።ይህ ሲሆን ይህ የአላህ ብቻ የሆነው ሃይማኖት የጥብቅ ወንድማማችነት መሠረት ሆኖ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ዳርቻ የሚገኙ ተከታዮቹን ልብ አንድ ሊያደርግ የሚችለው።ይህ ሲሆን ብቻ ነው ምንም እንኳን በቦታ እና ዘመን ቢራራቁም የትኛውም ኃይል ግንኙነታቸውን ሊገፋና ሊያፈርስ በማይችል መልኩ ጽኑ ትስስር የሚኖራቸው።

ወንድማማችነት የኢማን አስኳል ነው፤ አንድ ሙስሊም በነርሱና ለነርሱ የሚኖር በሚመስል መልኩ ለሌሎች ወንድሞቹ የሚሠጠው የጥልቅ ስሜቶች ልብ ነው።እነርሱ ከአንድ ግንድ የበቀሉ ቅርንጫፎች አሊያም በተለያየ ሰውነት ውስጥ እንደሚገኙ አንድ ሩሕ ናቸው።

ስለሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅ ያለው አስፈላጊነት

እኔነትና ስለራስ ብቻ ማሰብአጥፊ የሰው ልጆች በሽታና የመልካምነቱንምየሚገድልነው።በአንድ ግለሰብ የሕይወት ክፍል ላይ የገባ እንደሆነ በጎነቱን ያጠፋል፣ መጥፎነቱን ያጎላል፣ ራሱን ብቻ በሚያውቅበት የጠባብ ዓለም ሕይወት ውስጥ ብቻም እንዲኖር ያደርገዋል።መጥፎ አለያም ደስ የሚያሰኝ ነገር ካልገጠመው በስተቀር ደስታም ሆነ ሐዘን ደንታ የለውም።ሰፊዋ ዓለምንም ሆነ እልፍ አእላፍ የሰው ልጆችን የሚያውቀው አንድን ነገር ለማሳካት አሊያም የሚያስፈራውን ነገር ለማስወገድሲንቀሳቀስ በአጋጣሚ መንገዱ ላይ ያገኛቸው እንደሆነ ብቻ ነው።

የወንድምህን መጎዳት መጥላት እና የጎዳው ነገር ካለምለማስወገድ መንቀሳቀስና በማዘንም ሆነ በሌላ ከሱ ጋር ተጨባጩን መጋራት ወንድምህ ባንተ ላይ ካለውመብቶች መካከል አንዱ ነው።ጉዳቱ ካንተ እይታ ውጭ የሆነ ነገር ነውና በመጎዳቱ ምንም አያገባኝም ብለህ የማታዝንና ምንም ስሜት የማይሰማህ ከሆንክ ይህ በርግጥም አሳፋሪ አቋም ነው።በሙስሊሞች ነፍስ ውስጥ ያለችውሁሉን አካላይየወንድማማችነት ትስስር ስሜት አንድን ሰው በወንድሙ ላይ በሚደርሰው ችግር ምክንያት እንዲሰማው ልታደርግ ይገባል።የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) ይህንኑ በሚያረጋግጠው ንግግራቸው “አማኞች በመካከላቸው ያለው መዋደድ፤ መራራትና መተዛዘንምሳሌ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ነው።አንድ የሰውነት ክፍሉ ሲጎዳ ሌላኛው የሰውነት ክፍል በህመምና እንቅልፍ በማጣት ህመሙን እንደሚጋረው ሁሉ።”ብለዋል።(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

እውነተኛ የመታመም ስሜት ደግሞ የወንድምህን ጭንቀት እንድታስወግድ ያነሳሳሃል።ጭንቀቱ እስኪነሳለትና ጨለማውም እስኪወገድለት ድረስ መረጋጋት አይኖርህም።በዚህም የተሳካልህ እንደሆነ ፊትህ ይበራል፣ ውስጥህም ደስ ይሠኛል።

የዚህች ዓለም ችግሮች እጅግ ከባድ ናቸው።መከራዎች ዝናብ ለምና ደረቁም መሬት ላይ እንደሚዘንቡት ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይዘንባሉ።የሰው ልጅም በነኚህ ችግሮች ሥር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ብቻውን መቆም ይከብደዋል።ልቁም ቢል እንኳን ከአቅሙ በላይ የሆነ መስዋእትነት ለመክፈል ይገደዳል።ወንድሞቹ ሊረዱት ከተረባረቡለት፣ ዓላማውንም ለማሳካት ካገዙት ግን ነገሮችን ሊቋቋም ይችላል።እንዲህ የሚል አባባል አለ፡- ‹የሰው ልጅ በራሱ ብቻውን ነው።ከወንድሞቹ ጋር ሲሆን ግን ብዙ ነው።›

ከወንድማማችነት መብቶች መካከል አንድ ሙስሊም ወንድሞቹ በድብቅም ሆነ በይፋ ከጎኔ ናቸው ብሎ ማሰቡ ነው።ሰው -በዚህች ምድር ላይ እያለ የሚንቀሳቀስበት ጉልበቱ የሳሳ ነው።ስለሆነም የአማኞች ኃይል እገዛ ሊሆነውና ሊያጠነክረው ይገባል።የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡- “ሙእሚን ለሙእሚን እንደ አንድ ግንብ ነው፤ አንደኛው ሌላኛውን ያጠነክረዋል በማለት ጣቶቻቸውንበማቆላለፍ አሳዩ

ስለሆነም ንፁህ ወንድማማችነት ድርብርብፀጋ ነው።ይህን ስንል በመንፈስ መቀራረብ ብቻ አይደለም ቁሳዊ በሆነ ነገር መተጋገዝም አንዱ ነው።አላህ (ሱ.ወ)ይህንን ፀጋ በአንድ የቁርኣን አንቀጽ ውስጥ ደጋግሞ አንስቶታል -እንዲህ በማለት!-

وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنْتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُمْ بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا

“ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ፀጋ አስታውሱ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፤ በፀጋውም ወንድማማቾች ሆናችሁ፤”(አል-ኢምራን፡ 103)

በሶላት ውስጥ ‹ሰልፋችሁን አስተካክሉ› በማለት የቀደመውን ወደኋላ፣ ወደኋላ የቀረውን ወደፊት የመግፋቱና ከወንድሞቹ ጋር እንዲስተካከል የማድረጉ መርህ የወንድማማችነት ሚስጢር ነው።በመካከላቸው ግጭትና ጥል የተፈጠረ እንደሆነም የወንድማማችነት ድንጋጌና ፍርዱ በሁሉም ላይ ተግባራዊ ይደረጋል።አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

“ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፤ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ።”(አል-ሑጁራት፡ 10)

አንድነት ኃይል ነው።ይህም በሰው ልጆች ላይ ብቻ የተወሰነሳይሆን የፍጥረተዓለሙ ሁሉ ህግ ነው።ቀጭን ክርሌላ ቀጭን ክርሲጨመርበት ጠንካራና የማይበጠስ ገመድ ይሆናል።ይህ የምናየው ትልቅ ዓለምም የተለያዩ ቅንጣቶች ጥርቅምመሆኑን ማሰብ ይኖርብናል።

አንድ ጥበበኛ አባት በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሳለ ስለ አንድነት ምንነትና ዋጋ ሊያስተምራቸው ብሎ ለልጆቹ በአንድ ላይ የታሠረ እንጨት ሠጥቶ እንዲሰብሩትሠጣቸው።ልጆቹም አንድ ላይ የታሰረውን እንጨት መስበር አልቻሉም።እስሩ ሲፈታና እንጨቶቹ ሲበታተኑ ግን ልጆቹ እንጨቶቹን አንድ በአንድ መስበር ቻሉ።ይህ አንድ መሆን ምን ያህል ጥንካሬን እንደሚሠጥ የቀረበ ምሳሌ ነው።

እኛ ሙስሊሞች ካለፍንበት ታሪክ አንፃር ዛሬ ያለንበትን አስቸጋሪ ሁኔታና የደረሰብንን ውርደትና የፍላጎታችንን መለያየትዞርብለን ብናስተውልየአንድነት ጥቅም ይበልጥ ጎልቶ በታየን ነበር።

ዛሬ ላይ በርትቶ ያለው የመስቀለኞችና ተከትሎት የመጣው የፅዮናውያነት ጥቃት ኢስላማዊውን መንግሥት ሊያንበረክክ እና ተፈጥሯዊ ሀብቶቹንም በመዝረፉ ረገድ ሊሳካለት የቻለው ሙስሊሞችን እርስበርስ የሚባሉ ካደረገናበትንሽ ትልቁም ግጭት ላይ የሚወድቁ የተለያዩ ትናንሽ መንግሥታትን በመፍጠር የመከፋፈል ሴራውን ካሰፈነ በኋላ ነበር።ይህም ይኸው ዛሬ ላይ ምሥራቁ ዓለም ለምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ መንደርደሪያ ዋና ማዕከል ይሆን ዘንድ አግዞታል።

‹እስልምናየተከታዮቹን ሰላምና ክብር ለመጠበቅ የመጣና በዚህም ዘርፍየሚሠራ እምነት ነው።ስለሆነም በኃይልም ቢሆንየልዩነትን ምንጮች በእጅጉ ይዋጋል።እያንዳንዱ ሰውም በአንድነት እንዲንቀሳቀስና መለያየትን እንዲያስወግድ ያስተምራል።የኢስላምጠላቶች የልዩነት ስሜት ይፈጥርላቸው ዘንድከስብስቡ መካከል አንድን ግለሰብበማጥመድ በሱ በኩልማኅበረሰቡን ከመንገድ ለማስወጣት የቻሉትን ያህል ይጥራሉ።› (ኹሉቅ አልሙስሊም – ሸይኽ ሙሐመድ አልገዛሊ)

በሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅ እንዲሁም መተዛዘን ኢማን ግድ ከሚላቸው ነገሮች መካከል አንዱ ነው።ከአማኞች ባህሪ መካከል አላህም እንዲህ ይላል:

 

رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

“በመካከላቸው የሚተዛዘኑ”(አል-ፈትሕ፡ 29)

መሆናቸው አንዱ ነው።አላህ (ሱ.ወ)የሰይዳችንን የሙሐመድ እና የባልደረቦቻቸውን ምርጥ ባህሪ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡-

مُحَمَّدٌ رَسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ

“የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሀዲዎች ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው::”

(አል-ፈትሕ፡ 29)

በአማኞች መካከል የሚኖረው መተዛዘን የጎሳና ማኅበራዊ ትስስር ወገንተኝነት የሚወልደው አይደለም።ባይሆን ኢማን የወለደውና ይህ ኢማንምየመተዛዘንና የርህራሄን ስሜት በልቦች ውስጥ የሚያኖረው ነው።በየትኛው ግለሰብ ላይና መቼ ጠንከር ማለት እንዳለበትና መቼ መራራት እንዳለበትም በቀላሉ ያመለክተዋል።

በኢስላማዊ ሥነ ምግባር ውስጥ መተዛዘን ትልቅሥፍራ አለው።በግለሰብ ባህሪና በማኅበረሰባዊ ሕይወትውስጥም ትልቅ ቦታ አለው።ኢማን የሚሟላበትም ትልቅ መለያ ነው።ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ፡-

لن تؤمنوا حتى تراحموا

“አመናችሁ አይባልም፤ እስካልተዛዘናችሁ ድረስ(ጦበራኒ ዘግበውታል)

መተዛዘን ወደ አላህ እዝነት መዳረሻ መንገድም ነው።የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)

من لا يَرحم لا يُرحم

“የማያዝን አይታዘንለትም” ብለዋል(ቡኻሪ ዘግበውታል)

በሌላ ዘገባም:-

من لا يرحم الناس لا يرحمه الله

“ለሰዎች የማያዝን አላህ አያዝንለትም”ብለዋል (ጦበራኒ ዘግበውታል)

ቲርሚዚ ባስተላለፉት ታዋቂ ሐዲሥም

ارْحموا مَنْ في الأرض يرحمكم من في السماء

“በምድር ላይ ላሉት እዘኑ፤ በሰማይ ያለውእንዲያዝንላችሁ ዘንድ” ብለዋል።

የእዝነት መጥፋት የችግርና የሰቆቃ መንገድ ነው።  የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ፡-

لا تنزع الرحمة إلا من شقي

”ከመናጢ ካልሆነ በስተቀር እዝነት አትወገድም” (ሐኪም፣ ቡኻሪ፣ አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል)


የመወያያ ጥያቄዎች

  1. በሙስሊሞች ጉዳይ ምን ያህል እንደምታስብና እንደምትጨነቅእንዲሁም ያየኸውን ተግባራዊ ውጤት ግለጽ።
  2. ስለሙስሊሞች ጉዳይ ማሰብና መጨነቅ ያለውን አስፈላጊነት አብራራ።
  3. በሕይወትህ የኖርካቸው አሊያም ያጋጠመህን በሙስሊሞች ጉዳይ ስለመተሳሰብ መካከል ሁኔታ ጥቀስ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here