በሰዎች መካከል የሚፈጠሩ ልዩነቶችን ባህሪ እና መንስኤዎች ማወቅ

0
1599

በሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንነት

ልዩነት ወይም መለያየት ማለት አንድ ሰው በንግግርምሆነ በሁኔታው ከሌላው ሰው የተለየንመንገድ መከተል ማለት ነው።ልዩነት የሚለው ቃል በንግግር፤በሀሳብ፤ በሁኔታ አሊያም በአቋም የተለየ መሆን ለሚለው ይውላል።የአላህ መሻት ሆኖ የሰው ልጆች ካለባቸው የንግግር፤የቀለም እና የአመለካካት ልዩነት በተጨማሪ አእምሯቸውና አቋሞቻቸውም የተለያዩ አድርጎ ፈጥሯቸዋል።

وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِلْعَالِمِينَ

“ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ የቋንቋዎቻችሁና የመልካችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች ተዓምራት አሉበት”(አር-ሩም፡22)

ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ነገሮችወደተለያየአስተሳሰብ፤ውሳኔ የሚያደርሱ ናቸው።እንደየተናጋሪው እይታምይለያያሉ።

የቋንቋችን፤ የመልካችንና የውጫዊ ገፅታችን መለያየት ከአላህ ተዓምራት መካከል እንደሆነው ሁሉየአእምሮአዊ ግንዛቤ እና የአረዳድ ልዩነታችንና አጠቃላይ ውጤቱ በእርግጥምከአላህ(ሱ.ወ) ተዓምራት መካከል ስለመሆኑጥርጥር የለውም።እንዲያውም የአላህ ፍፁም ችሎታ ከሚገለፅባቸው ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ ነው።የሰው ልጆች በሁሉምነገራቸው በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ቢፈጠሩ ኖሮየፍጥረተ ዓለሙ ግንባታ፤ የፍጥረታቱ ብልፅግናየዚህ ዓለም ሕይወት ህልውና… አንዳቸውም ባልተረጋገጡ ነበር።ሁሉም ለተፈጠረለት ነገር የተገራ ነው።

وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ النَّاسَ أُمَّةً وَاحِدَةً ۖ وَلَا يَزَالُونَ مُخْتَلِفِينَ

إِلَّا مَنْ رَحِمَ رَبُّكَ ۚ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمْ ۗ وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ

“ጌታህም በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር፤ የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም።ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር (ከመለያየት አይወገዱም) ለዚሁም ፈጠራቸው” (ሁድ፡ 118 -119)

አላህ(ሱ.ወ)የሰው ልጅ ዝግጅትና ምርጫውን የተለያየ አድርጓል።የአመለካካት መንገድን የመምረጥ ችሎታና መንገዱን የመምረጥነፃነት ሠጥቶታል።የምርጫውንም ውጤት የመውሰድ ኃላፊነት አሸክሞታል።የዚህ አካል ከሆኑ ነገሮች መካከልም የሰው ልጆች የመለያየታቸው ነገርአንዱ ነው።ሌላው ቀርቶ ሰዎችአላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ በእምነት አመለካከት (ዐቂዳ) ላይ ጭምር እስከመለያየት ይደርሳሉ።(ፊዚላል አል ቁርኣን – ሰይድ ቁጥብ)

የሰዎች በሀሳብና አመለካከት መለያየት ሁኔታ አንደኛቸው አለያም ሁለቱም ንግግራቸውን የየራሳቸውን አመለካከት አሊያም አቋም ትክክል እንደሆነ በግድ ለማሳመንና ለማስረዳትጠንከር ወደማለትና ድንበር እስከመተላለፍ የሚደርሱበት ሁኔታ ይኖራል።ይህም አጉል ክርክር የምንለው ነው።ክርክር ማለት አንደኛው በአንደኛው ላይ የበላይነትን ለመጎናፀፍየሚደረግ ጭቅጭቅ ማለት ሲሆን አላህ(ሱ.ወ)ስለ ሰው ልጅ ሲናገር የሚከተለውን ብሏል፡-

وَكَانَ الْإِنْسَانُ أَكْثَرَ شَيْءٍ جَدَلً

“ሰውም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው።” (አል-ከህፍ፡ 54)

በተከራካሪዎች መካከል ክርክሩ ሲያይልና ሁሉም እውነትን ከመግለጽና ትክክለኛውን ከማሳየት ይልቅ ለማሸነፍ ብቻ የሚጓጓ ከሆነ አለመረዳዳት ወይም አለመግባባት ከተፈጠረ ይህ ሁኔታ ‹ሺቃቅ› ይሠኛል።አላህ ስለ ባል እና ሚስት አለመግባባት በሚያወሳው የቁርኣን አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል፡-

وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا

“(እናንተ ዋቢዎች) የመካከላቸውንም ጭቅጭቅ ብታውቁ” (አል-ኒሳእ፡ 35)

ይህም ማለት እጅግለጥላቻና ንትርክ የሚጋብዝ ሲሆን እያንዳንዱም ግለሰብ ከባልደረባው አንፃር ፍጹም ተቃራኒ የሆነ አቋም የሚይዝበት ሁኔታ ነው። በመሠረቱ   ልዩነት በቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ውስጥ ጭምር የተከሠተ ሲሆን ይህ ተፈጥሯዊ ሁኔታ ዛሬም ድረስ ያለ ጉዳይ ነው።ልዩነት ድንበር ያልታለፈበት ከሆነና ሙስሊሙ ማኅበረሰብም በሥርዓቱ ከታነፀ በአዎንታዊነቱ ውጤት ያለውናበርካታ ጠቀሜታም የሚያስገኝነው።

የልዩነት ዓይነቶች እና መንስኤዎች

1- ከባህሪ ችግር እና ከስሜት የሚመነጩ ልዩነቶች

ነገሮች በጥልቀት ባለመመልከትና መንስኤያቸውንም ባለማጤን አንድ ነገር ለማድረግእና አቋምም ለመያዝ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በሚያውቁ የሥነምግባር አስተማሪዎችና ልሂቃን ዘንድ የሚታወቅ ነው።ከነዚህመንስኤዎች መሀከል፡-

  • በራስነፍስ መጃጃል እና በራስ አመለካከት መደነቅ።
  • ሌሎችን በመጥፎ መጠርጠርና ያለ ማስረጃሥም ለማጥፋት መቻኮል።
  • ራስን መውደድና ስሜትን መከተል፡-ከምልክቶቹም መካከልየመሪነትን፣ የበላይነት እና ሥልጣንን ፍለጋ መጓጓት።
  • ለግለሰብ አመለካከት ወይም መዝሀብየሚኖር ጭፍን ወገንተኝነት።
  • ለአንድ ሀገር፣ ግዛት፤ አሊያም ቡድን ጭፍን ወገንተኝነት።

እነዚህ ሁሉ ውድቅና ርካሽ ባህሪያት ሲሆኑ ከነርሱየሚመነጭ ልዩነትም የተወገዘነው።

2- አስተሳሰብንና አመለካከትን መሠረት ያደረጉ ልዩነቶች

ይህ ሲባል ያ ነገር በዕውቀት ዙሪያ ለምሳሌ በሸሪዓ ቅርንጫፋዊና አንዳንድ መሠረታዊ እምነታዊ ጉዳዮች ላይ ወይም ደግሞ በዓለማዊ ጉዳዮች ለምሳሌ በፖለቲካዊ አቋም ዙሪያ ከራስ የዕውቀት ልክ እና ግምት በመነሳት አሊያም በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ መልኩ በአካባቢያዊ ሁኔታ ተጽዕኖ ሥር በመውደቅ በሀሳብ በመለያየት ምክንያት ውሳኔ ማስተላለፍ ሊሆን ይችላል።በዚህምየተነሳ ነው በነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ዘመንም ሆነከርሣቸው በኋላ በተተኩ በቅን መሪዎች ዘመን በብዙ ሰሐባዎች መካከል የአቋምልዩነቶች የተከሠቱት።የዚህም መነሻው በአንድ በተላለፈ መልዕክት ዙሪያ  ከቋንቋዊ ሀሳቡን በመተርጎም ረገድ ባደረጉት ጥረት ከመጣ ልዩነት ነው።ኋላ ላይም በሙስሊም ሊቃውንቶች ዘመን ከአንድ መልዕክት አሻሚ የቋንቋ ትርጉም በመነሳት መልዕክቱ በያዘው ትክክለኛ መልዕክት ዙሪያ ልዩነት ተፈጥሮ አስተውለናል።አንዳንዶቹ ልዩነቶችበሐዲሦች ዙሪያ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በመሠረታዊ መርሆችና መስፈርቶች ዙሪያ ነበሩ።የዚህ ዓይነቱ የአመለካከት ልዩነት መጠላት የለበትም።ሙስሊሞችንም ወደ አስከፊው መለያየት መምራት የለበትም።የዚህ ዓይነቱ ልዩነት ባይሆን በዓይነት የተለያዩ ጠቃሚ አመለካከቶችን ለማበልፀግ መዋል ነው ያለበት።በሁሉም ጥረቶችና አመለካከቶች ግለሰብ፣ ማኅበረሰብም ሆነ አጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ መጠቀም አለበትና።አንድ ተናጋሪ ስለዚሁ ጉዳይ እንዲህ ብሏል፡-
“በሚያስማሙን ጉዳዩች ላይ ተባብረን እንሰራለን፤በተለያየንባቸው ጉዳዮች ላይ ደግሞ አንደኛችን ለአንደኛችን ሆደ ሰፊ እንሆናለን።”
“በሀሳመለያየበመካከላችን ያለውን መዋደድ ማደፍረስ የለበትም።

የመወያያ ጥያቄዎች(ባሉበት ይወያዩ)

  1. በሰዎች መካከል የሚፈጠሩ የልዩነት ሁኔታዎችን አብራራ
  2. የልዩነትዓይነቶችን እና መንስኤዎቻቸውንልዩነት መቼ እንደሚወደድና መቼ እንደሚወገዝ አብራራ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here