እስልምና የሰላም ጎዳና

0
8849

ኢስላም ማለት ለአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ትዕዛዝ ሙሉ ለሙሉ እጅ መስጠትማለት ነው። እንዲሁም ኢስላም ሰላም ማለት ነው። ባጠቃላይ ኢስላም ስንልለአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ትዕዛዝ እጅ በመስጠት ሠላምን መጎናፀፍ ማለት ነው።አስ-ሰላም ከጌታችን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ስሞች መካከል አንደኛው ነው።ሠላም፣ ብልፅግና፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነፃነት ወዘተ ኢስላም እንደ አላማያስቀመጣቸው እሴቶች ናቸው።

ትዕዛዛቱም እነዚህን አላማዎች በተጨባጭ ህይወት ዘርተው በማህበረሠቡ ውስጥእንዲኖሩ የሚያደርጉ ናቸው። መለኮታዊነት፣ ሰብዓዊነት፣ ሁለንተናዊነት እንዲሁምሚዛናዊነት የዚህ ዲን (ኢስላም) ልዩ መገለጫ ባህሪያት ናቸው። ምንጩ አስ-ሰላም የሚባልስም ካለው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘንድ የተሠጠ ዲን ነዉ። ለሰብዓዊም ሆነ ማህበራዊ የህይወት ክፍል በቂ መመሪያን በማስቀመጥ ሁለንተናዊነቱ የተገለፀ ሲሆን በመርሆዎ ቹመካከል በሚስተዋለው ተመጋጋቢነትና አስደናቂ ጥምረት ሚዛናዊ መሆኑ በጉልህ ይንፀባረቃል። ታዲያ ይህን አይነት መሠረት ላይ የቆመው ኢስላም ሽብርተኝነትን እንዴት ይመለከታል? እስልምናና ሽብርተኝነት ፍፁም ተቃራኒ ናቸው። ሠላምን መፍጠር ከግለሠብ እንዲጀመር ያስተምራል። ከላይእንደተጠቀሠው ይህ ሁለንተናዊና ሐይማኖት የአንድን ግለሠብ አእምሮአዊ፣ ስሜታዊ፣ አካላዊና መንፈሣዊ ክፍሎች ከግንዛቤ ያስገባል። አንድግለሠብ ከራሱ ጋር የተስማማና ሠላም የሚሠማው እንዲሆን አቅጣጫ ያሳያል። በእስልምና እርም (ሐራም) የተደረጉ ነገሮችን ብንመለከት ሁሉየግለሠብን ሠላም ይጠብቃሉ። አደንዘዥ ዕፅና አስካሪ መጠጦችን በመከልከል፣ ለዝሙት፣ ስርቆትና መስና አግባብ የሆኑ ቅጣቶችን በማስቀመጥየግለሠብንም ሆነ የማህበረሰቡን ሠላም ያስጠብቃል።

ይህ ሐይማኖት ለሠው ልጅ ህይወት እጅግ የገዘፈ ዋጋ ይሠጣል፤ አስገራሚ ቅድስናን ይለግሣል። ከዛም አልፎ ለእንስሳትና ዕፅዋት በቁርዐን ላይ ግድያ በግልፅ ቋንቋ ተወግዟል።

مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِالْبَيِّنَاتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِي الْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ

“በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን። መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው። ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው።” (አል ማዒዳ፤ 32)

قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۖ وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُم مِّنْ إِمْلَاقٍ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكُمْ وَإِيَّاهُمْ ۖ وَلَا تَقْرَبُوا الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ ۖ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ» በላቸው። «በእርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ። ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)። ልጆቻችሁንም ከድህንት (ፍራቻ) አትግደሉ። እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና። መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ። ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጅ አትግደሉ። ይህን ታውቁ ዘንድ (አላህ) በእርሱ አዘዛችሁ።” (አንዓም፤ 101)

እዚህ ጋር በማህበረሰቡ ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉ ፍትሐዊ የሞት ቅጣት በተለየ መልኩ እንደሚታዩ ያስረዳል። የሰው ልጅ ዋጋ ይህንያህል ነው። ያለ አግባብ የጠፋች አንዲት ነፍስ ከሠው ዘር መጥፋ ጋር የሚመጣጠን ዋጋን ተችራለች።

“ለዓለማት ዕዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም።”

በዚህ መርህ ላይ የተነሣው የለውጥ ሂደት በነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መሪነት ሽብርተኝነትን መዋጋት የጀመረው ገና በጠዋቱነው። በወቅቱ የነበረውን የህይወት ስርዓት ምን እንደሚመስል ከጃዕፈር ኢብኑ አብ ጧሊብ አንደበት እንስማ።

ጃዕፈር ለሐበሻው ንጉስ ነጃሺ እንዲህ በማለት ነበር ጨለማውን ያስረዳው።

“ንጉስ ሆይ! የድንቁርና ስርዓት ተከታይ ህዝቦች ነበርን። ጣኦታትን እንገዛለን። የበከተ እንበላለን።ዝሙት እንፈፅማለን። ጠንካራው የደካማውን ገንዘብ ይበላል። በዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ነበርን። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ወደኛ ዘሩን፣ እውነተኛነሩን፣ ታማኝነቱንናጨዋነቱን የምናውቀውን መልዕክተኛ ላከልን። ይህ ነብይ ወደ አላህ ጠራን፣ አላህንም አንድ አድርገን እንድንገዛው፣ እኛም ሆንን አባቶቻችን ስንገዛው የነበረውን ድንጋይና ጣዖት እንድንተው አስተማረን። ለጎረቤቶቻችን መልካም እንድንውል አዘዘን፤ እንዲሁም(በተጨማሪም) ዝሙት ከመፈፀም፣ በሀሰት ከመመስከር፣ የየቲሞችን ገንዘብ ከመብላት፣ ጥብቅና ንፁሐት የሆኑ ሴቶችን ከመሣደብ እንድንቆጠብ አዘዘን። አላህን ብቻ እንድናመልክና በርሱም ላይ አንድም ነገር ላናጋራ፣ ሰላትንም ልንሠግድ፣ ዘካንም ልናወጣ፣ ፆምም ልንፆም አሣሠበን። እውነት ብለን ተቀብለነው ከአአላህ ይዞ በመጣው ነገር ተከተልነው። አላህን ብቻ መገዛት ጀመርን። በሱም ማጋራታችንን አቆምን። አላህ “ሐራም” (ክልክል) ያደረገውን ክልክል አደረግን። የፈቀደውን ነገርም መፈፀም ጀመርን። በዚህ የተነሣ ነው ወገኖቻችን ጠላት አድርገው የያዙንና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የፈፀሙብን። መከራው ሲበዛብን፣ ከሐይማኖታችን ሊቀለብሱን ሲጫኑን ተሰደድን። እርሶ ዘንድም እንደማንበደል እርግጠኞች ነን።”

በዚህ ንግግር ውስጥ በወቅቱ የተንሠራፋውን ችግር እንመለከታለን። ኢስላም ተከታዮቹን ያስጉዝ የነበረበትን ብርሐንም እናለያን።

ደም ያለአግባቡ ይፈስ የነበረበት ዘግናኝ ወቅት መሆኑን እንረዳለን። ለዚህ ነው ገና ከጅምሩ  ሽብርተኝነትን ሊዋጋ ተነሳ የሚያስብለን።ከነብዩ ውልደትና መላክ ባኋላ የታየው ሠላም እና ፍትህ በአረቦች ብቻ የተገደበ አልነበረም። ዓለም ሁሉ ከዚህ በረከት ተከፋይ ሆኗል።በቁርዓን ውስጥ የተቀመጠው በአንባገነንነት፣ ጭቆናና ሽብርተኝነት ላይ የሚደረገው ጦርነት በዓለም ላይ እራሱን ገለፀ። ጨለማውን በብርሃን ቀየረ።

ታላቁ ነብይ ተከታዮቻቸውን ሲያስተምሩ እንዲህ ነበር ያሉት “ከናንተ ውስጥ አንዳችሁም ለራሣችሁ የወደዳችሁትን ለወንድማችሁ እስካልወደዳችሁ ድረስ አላመናችሁም።” በዚህም ሙስሊሞች ሠላምን ለራሣቸውም ሆነ ለሌሎችም እንዲወዱ እንዲሁም ከደካማ ወገኖች ጎን እንዲቆሙ ያዛል።

وَمَا لَكُمْ لَا تُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ الرِّجَالِ وَالنِّسَاءِ وَالْوِلْدَانِ الَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْ هَٰذِهِ الْقَرْيَةِ الظَّالِمِ أَهْلُهَا وَاجْعَل لَّنَا مِن لَّدُنكَ وَلِيًّا وَاجْعَل لَّنَا مِن لَّدُنكَ نَصِيرًا

“በአላህ መንገድና ከወንዶች ከሴቶችና ከልጆችም የኾኑትን ደካሞች እነዚያን፡- «ጌታችን ሆይ! ከዚች ባለቤቶችዋ በዳይ ከኾኑት ከተማ አውጣን ከአንተም ዘንድ ለእኛ አሳዳሪን አድርግልን ከአንተ ዘንድም ለእኛ ረዳትን አድርግልን» የሚሉትን (ለማዳን) የማትጋደሉት ለእናንተ ምን አላችሁ?” (ኒሳእ፤ 75)

ሙስሊሞች የሐይማኖታቸውን አስተምህሮ ተከትለው በሲሪያ፣ ግብፅ፣ ስፔን እና ፐርሺያ ውስጥ ለነበሩ ጭቆናዎች ሠራዊት ልከዋል፤ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል። በታሪክ በአንድ ወቅት ሙስሊሞች የሣሣኒድን ኢምፓየር ተቆጣጥረው ነበር። ኢሽያብ ሦስተኛ የሚባለው የፐርሺያ ግዛት አማካሪ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ነበር የፃፈው።

“አረቦች በዚህ ወቅት ፈጣሪ ሐይልን ቸሮአቸዋል። በአሁኑ ሰዓት አንተ ዘንድ እንደሚገኙም ታውቃለህ። ሆኖም ግን እነርሱ የክርስትናን እምነት ፈፅሞ አልነኩም። በተቃራኒው ድጋፍን ለገሱን ለቀሣውስቶቻችንና ለቅዱሣናት ክብርን እንጂ ሌላ አላሣዩም። ቤተክርስቲያናትንና ገዳማትን ጠበቁ እንጂ አላወደሙም”

አሽያብ ምድር ላይ የነበረውን ተጨባጭ ሁኔታ ነበር በንግግሩ ያረጋገጠው። ሙስሊሞች እምነትን በግድ እንዳላስቀየሩ ይናገራል።(T.W,Arnold, preaching of islam , London, 1913, p, 81-82)

የሚከተለዉ አንቀፅ መልዕክት ለሁሉም ህይወት ላላቸው ነገሮች የቀረበ ነው። የተለየ ትኩረቱ ደግሞ ለሠው ልጅ ህይወት ነው።ህይወት ከፈጣሪ (አላህ) የተሰጠች ስጦታ እንጂ የባለ ህይወት ስሪት አይደለችም። ለመሆኑ እርሷን የማጥፋት መብትይከለከላል።ስለዚህ እርሷን ማጥፋት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የተከላከለ ይሆናል ማለት ነው።

እርሷን ማጥፋትን በተመለከተ ቁርዓንትዕዛዙን በማያሻማ መልኩ ሰስቀምጧል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ። ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ (ብሉ)። ነፍሶቻችሁንም አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና።” (ኒሳእ፤ 29)

በዚህች አንቀፅ ሠዎችን እራስን ወደ ማጥፋት የሚወስዱ ነገሮችን እንሰማለን። ችግር፣ የፍትህ መጓደል፣ መከራ ፣ ተስፋ መቁረጥናየመሣሰሉት ነገሮች ቢኖሩም በርሱ በአላህ እዝነት ተስፋ እንዲያደርጉ ታስታውሳለች። ፈጣሪያችሁ ለናንተ አዛኝ ነው ትላለች።ባጠቃላይ የመልዕክቱን አባይ እንደሚከተለው መሰብሠብ እንችላለን።

  • እራስን ማጥፋት የተከለከለ መሆኑን
  • እርስ በእርስ መገዳደል ክልክል መሆኑንና ለአንድ ሰው የራስን የማጥፋት ጉዞ ማመቻቸት ክልክል መሆኑን
  • አንድ ሰው የራሱን ነፍስ ሊያጠፋና ሊገድል በሚችል ተግባር ውስጥ መሣተፍ ክልክል መሆኑን። ድርጊቱ አምልኮዓዊ ቢሆንምእንኳን
  • መሠረታዊና ለህይወት አስፈላጊ ነገሮችን እራሱን ማሣጣት እንደሌለበት። በዚህም ለመጥፋቱ ምክንያት ከመሆን እንዲቆጠብ
  • ባጠቃላይ ህይወትን ሊያጠፋ የሚችል ማንኛውም ነገር ክልክል መሆኑን።

وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

“በአላህም መንገድ ለግሱ። በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ። በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና።”(በቀራ፤ 195)

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦

“እራሱን ከፍ ካለ ተራራ ላይ ወርውሮ የሞተ በመጪው አለም እሳት ውስጥም ይሄንኑ ተግባር በራሱ ላይ ይፈፅማል። ገዳይ መርዝ ጠጥቶ የሞተም በእሳት ውስጥ ያንኑ ገዳይ መርዝ በቋሚነት ይዞ እንዲጠጣ ይደረጋል። እራሱን በመሣሪያ የገደለም ተመሳሳይ ነገር በራሱ ላይ እንዲፈፅም ይደረጋል።” ህይወት ሰውዬው ዘንድ የተቀመጠች መለኮታዊአደራ ናት።

የራስንም ሆነ የሌሎችን ህይወት መንዳት ከዚህ ታላቅ አደጋ ጋር መለተም ይሆናል። በርግጥ ኢስላም ጭቆናና በደልን አይቀበልም።በደልና አንባ ገነንነት ሲንሰራፋም ዝም ብሎ አይመለከትም።

وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

“እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን (ከሓዲዎች) በአላህ መንገድ ተጋደሉ። ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና።”(በቀራ፤ 190)

በጦርነት ወቅት እንኳን ፈፅሞ የማይሸረሸሩ መስፈርቶች ህጎች የቀመጣሉ። ለምሳሌ ያክል በጦርነት ወቅት የሠላም ውል የገቡወገኖችን መጉዳትም ሆነ መግደል አይቻልም። በተጨማሪም መዋጋት የማይችሉ፣ ደካሞች፣ ህፃናት፣ አይነ ስውራን ቀሳውስሮች፣የአካል ጉዳተኞች እና የአእምሮ ህመምተኞችን መንካት በእጅጉ ይከለክላል። ከዚህም አልፎ እፅዋትን ማውደምን በጦርነት ወቅትእንኳን የተከለከሉ መሆኑን ያስተምራል።

لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

“ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም። አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና።” (አንዓም፤ 8)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here