አል ሂሣብ/ ምርመራ/ ክፍል 1

0
4515

ምርመራ የአምላክን ፍትሃዊነት ያመለክታል

የተላቀውና የተከበረው አላህ ፍፁም እና ምሉእ በሆኑ ባህሪዎች የሚገለፅ ጌታ ነው፡፡ ምሉእነቱን  ከሚያመለክቱ ባህሪዎች መካከል ፍትህ አድራጊነቱና የተሟላ ጥበብ ባለቤት መሆኑ ይጠቀሣሉ፡፡ አላህ ሱ.ወ ፍትሃዊ የሆነ አምላክ ነው፤ በርሱ ዘንድ ማንም አይበደልም፡፡ ጥበበኛም የሆነ ጌታም ነው፤ ነገሮችን ሁሉ ተገቢአቸው ነው ባለው ቦታ ላይ ያስቀምጣል፡፡

ከፍትሃዊነቱና ጥበበኛነቱ የተነሣም ፃድቅ መልካም ሰሪ የሆነውንና ጠማማ አመፀኛውን፣ አማኙንና ከሃዲውን፣ መልካም ሰሪውንና እኩይ የሆነውን እኩል አለማድረጉ ተጠቃሽ ነው፡፡ በርግጥም እነኚህን ተቃራኒ የሆኑ ጎራዎች በአንድ ዐይን እኩል መመልከት የግፎች ሁሉ ግፍ ከመሆኑም በላይ አላዋቂነትም ጭምር ነው፡፡

ጌታችን አላህ ሱ.ወ መልእክተኞቹን ግልፅ የሆኑ ማስረጃዎችን አስይዞ ልኳል፡፡ ሰዎች ፍትህን ያሠፍኑ ዘንድ ከነርሱ ጋርም መፅሃፍንና ሚዛንን አውርዷል፡፡

የመልእክተኞችን መላክ ተከትሎ ከፊሎች ሰዎች ወደ አላህ መንገድ የተመሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ከመንገዱ ተዘነበሉ፡፡ ትክክለኛ አመለካከት፣ ትክክለኛ የአምልኮ ሥርኣት እና የመልካም ሥራ መንገድንም መያዝ አልቻሉም፡፡ወደ ትክክለኛ መንገድ የተመሩ ሰዎች ለመስተካከል ከፍተኛ የሆነ ጥረትና መሪር የሆነ መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ስሜትን ለማሸነፍ፣ ውሸትን ለመዋጋት፣ ተንኮልን ወንጀልን ለማጥፋት በብዙ ታግለዋል፡፡ በዚሁ መንገድ ያደረጉት ትግልም እስከ ህይወታቸው መጨረሻ ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡ታዲያ የነዚያ የመልካም ሠሪ ሰዎች ጥረትና ከቀጥተኛው ጎዳና ይልቅ ጥመትን፣ ከመስተካከል ይልቅ ጥፋትን ከመረጡትና የርካሽ ስሜት ተከታይ ሆነው በጥፋት መንገድም ውስጥ እድሜ ልካቸውን  ከኖሩትና ለከልካይም ካስቸገሩት ሥራፈቶችና አመፀኞች ጋር አንድ ይሆናልን !? በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡

በርግጥ ሁለቱም ወገኖች የምድር ላይ ህይወትን አሣልፈዋል፡፡ አንደኛው የአላህ ሱ.ወ ቃል የበላይ እንዲሆን፤ ባንዲራውንም ከፍ ለማድረግ ምድርንም ከተንኮልና ከጥፋት ለመታደግ ብሎም ለማነፅ ሲል በመንገዱ ይታገላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ለስሜቱና ለዓለማዊ ጥቅሙ ሲል በሸይጧን ጎዳና ተሣፍሮ ክፉ ነፍሱ ያዘዘችበትን ሁሉ በማዳመጥ ሲንቀሣቀስ ይኖራል፡፡ ታዲያ ሁኔታውን ፍፁም ከሆነው የአላህ የፍትሃዊነትና የጥበበኛነት ባህሪ አንፃር ስናስተያይ የሁለቱ ሰዎች መጨረሻ አንድ መሆን ይችላልን!፡፡ አንድ ነው ብሎ ማሰብ በርግጥም ለትክክለኛ አዕምሮ ለማሰብ የሚከብድ ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ ከፍትህ አድራጊዎች ሁሉ ይበልጥ ፍትህ አድራጊ ከጥበበኞች ሁሉ እጅግ ጥበበኛ የሆነ ጌታ ነውና፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ اجْتَرَحُوا السَّيِّئَاتِ أَن نَّجْعَلَهُمْ كَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَوَاءً مَّحْيَاهُمْ وَمَمَاتُهُمْ ۚ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ
وَخَلَقَ اللَّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَلِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

እነዚያ ኀጢአቶችን የሠሩ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን እንደእነዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ)፡፡ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ!አላህም ሰማያትንና ምድርን (ለችሎታው እንደሚያመለክትባቸውና) ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳ ዘንድ በትክክል ፈጠረ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ አል ጃሲያህ ፤ 21-22

የደጋግ መልካም ሰዎችና የሌሎች በተቃራኒው የሆኑ ወገኖች መመለሻ አንድ ነው ብለው የሚያስቡ ካሉ የዚህች ዓለም ህይወት ቀልድና ጨዋታ ብቻ ነው ብለው የሚረዱት ናቸው፡፡ አላህ ሱ.ወ የሰው ልጅን፣  ሰማይንም ሆነ ምድርን ሁሉ ለትልቅ ዓላማ እንደፈጠረ ሲናገር እንዲ አለ ፡-

وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلًا ۚ ذَٰلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ
أَمْ نَجْعَلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَالْمُفْسِدِينَ فِي الْأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ الْمُتَّقِينَ كَالْفُجَّارِ

ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን? ሷድ ፤ 27-28

አብዛኞቹ ሰዎች ይህን እውነታ አያውቁም ፡፡ የሚያስታውሱም ቢሆኑ ጥቂቶች ናቸው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

لَخَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَكْبَرُ مِنْ خَلْقِ النَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
وَمَا يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَلَا الْمُسِيءُ ۚ قَلِيلًا مَّا تَتَذَكَّرُونَ
إِنَّ السَّاعَةَ لَآتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ ዕውርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሠሩና መጥፎ ሠሪው አይስተካከሉም፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ ጋፍር፤57-59

ያም ሆነ ይህ እውነታው የሚገለጥበትና የውስጥ ድብቅ ሚስጢር ይፋ የሚወጣበት ቀን መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ أَسَاءُوا بِمَا عَمِلُوا وَيَجْزِيَ الَّذِينَ أَحْسَنُوا بِالْحُسْنَى

በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡ አን ነጅም፤31

ቀደምት ሙሽሪኮች/በአላህ ያጋሩ የነበሩ ሰዎች/ የቂያማን ቀን እውነትነት ይጠራጠሩ ክስተቱንም በእጅጉ ያስተባብሉ ነበር፡፡ በተሣሣተ እምነታቸውም ‹ይህማ የማይሆን ነገር ነው› በማለት ይምሉ ነበር፡፡ አላህ ሱ.ወ ግን ማስተባበላቸውን በማውሣት እውነት ከሀሠት፤ ሀቀኛው ሰው ከውሸታሙ ይለይ ዘንድ አላህ በጥበቡ ያስቀመጠው ጉዳይ እንደሆነ በመግለፅ መለሠላቸው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

وَأَقْسَمُوا بِاللَّهِ جَهْدَ أَيْمَانِهِمْ ۙ لَا يَبْعَثُ اللَّهُ مَن يَمُوتُ ۚ بَلَىٰ وَعْدًا عَلَيْهِ حَقًّا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
لِيُبَيِّنَ لَهُمُ الَّذِي يَخْتَلِفُونَ فِيهِ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّهُمْ كَانُوا كَاذِبِينَ

መሓሎቻቸውምን አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም ሲሉ በአላህ ስም ማሉ፡፡ ሐሰት ነው (ያስነሳቸዋል)፡፡ በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ አረጋግጧል፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡(የሚቀሰቅሳቸውም) ለእነሱ ያንን በእርሱ የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸው፤ እነዚያ የካዱትም እነሱ ውሸታሞች የነበሩ መኾናቸውን እንዲያውቁ ነው፡፡ አን ነህል፤38-39

የምርመራ አደራረግ

አላህ ሱ.ወ በአዲስ መልክ ህይወትን ወደ ሰው ልጅ አካል ከመለሠ በኋላ ወደ አንድ ቦታ ይነዳቸዋል፣ ይሠበስባቸዋል፤ እያንዳንዱን የሰው ልጅም በሠራው መጥፎና ጥሩ ሥራ ላይ ይመረምራል፡፡ ምድርም በሷ ላይ የተፈፀመውን ሁሉ በዝርዝር ትናገራለች፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ

إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا
وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤ ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤ በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡ ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡ በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡ የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ አዝ ዘልዘላህ፤1-8

ከአቢ ሁረይራ ረ.ዐ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ

فقال: « أتدرون ما أخبارها ؟ » قالوا: الله ورسوله أعلم، قال: « فإن أخبارهم أن تشهد على كل عبد أو أمة بما عمل على ظهرها، أن تقول: عمل كذا وكذا، يوم كذا وكذا » قال: « فهذه أخبارها »

‹ያኔ ወሬዎቿን ትናራለች› የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ካነበቡ በኋላ ‹ወሬዋ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን!› በማለት ጠየቁ፡፡ እነሱም ‹አላህ እና መልአክተኛው ያውቃሉ፡፡› በማለት መለሡ፡፡ እርሣቸውም ‹ወሬዋ በያንዳንዱ ወንድ እና በያንዳንዷ ሴት ባሪያ ላይ እንዲህ ተሠራብኝ ብላ መመስከሯ ነው፡፡ የሆነ ቀን እንዲህ ሠራ፤ እንዲህ ሠራ ትላለች፡፡ ወሬዋ ይሄ ነው፡፡› አሉ፡፡

የቂያማ ቀን መሬት የተሠራባትን እንደምትናገረው ሁሉ ምላሦችም፣ እጆችም፣ እግሮችም፣ የሰውነት ቆዳዎችም ጭምር ይመሠክራሉ፡፡ በዚህ መልኩ የአላህ ማስረጃ በዓለም ፍጥረታት ላይ ይረጋገጣል፡፡

يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ

በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡ በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ (ሁሉን ነገር) ገላጭ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ አን ኑር፤24-25

وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَاءُ اللَّهِ إِلَى النَّارِ فَهُمْ يُوزَعُونَ
حَتَّىٰ إِذَا مَا جَاءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَارُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
وَقَالُوا لِجُلُودِهِمْ لِمَ شَهِدتُّمْ عَلَيْنَا ۖ قَالُوا أَنطَقَنَا اللَّهُ الَّذِي أَنطَقَ كُلَّ شَيْءٍ وَهُوَ خَلَقَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
وَمَا كُنتُمْ تَسْتَتِرُونَ أَن يَشْهَدَ عَلَيْكُمْ سَمْعُكُمْ وَلَا أَبْصَارُكُمْ وَلَا جُلُودُكُمْ وَلَٰكِن ظَنَنتُمْ أَنَّ اللَّهَ لَا يَعْلَمُ كَثِيرًا مِّمَّا تَعْمَلُونَ
وَذَٰلِكُمْ ظَنُّكُمُ الَّذِي ظَنَنتُم بِرَبِّكُمْ أَرْدَاكُمْ فَأَصْبَحْتُم مِّنَ الْخَاسِرِينَ

የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነርሱም የሚከመከሙ ኾነው ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡ ለቆዳዎቻቸውም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ፡፡ «ያ አንዳቹን ነገር ሁሉ ያናገረው አላህ አናገረን፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ጊዜ ፈጠራችሁ፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል፡፡ ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁም በእናንተ ላይ ከመመስከራቸው የምትደበቁ አልነበራችሁም፡፡ ግን አላህ ከምትሠሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ፡፡ ፉሲለት፤19-23

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا ۚ أَحْصَاهُ اللَّهُ وَنَسُوهُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ مَا يَكُونُ مِن نَّجْوَىٰ ثَلَاثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمْ وَلَا خَمْسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمْ وَلَا أَدْنَىٰ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمْ أَيْنَ مَا كَانُوا ۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አላህ ሁላቸውንም በሚቀስቃሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፡፡ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ የረሱት ሲኾኑ አላህ ዐውቆታል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡ አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን በምድርም ውሰጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መኾኑን አታይምን? ከሦስት ሰዎች መሾካሾክ አይኖርም እርሱ አራተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከአምስትም (አይኖርም) እርሱ ስድስተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከዚያ ያነሰም የበዛም (አይኖርም) እርሱ የትም ቢኾኑ እንጂ፡፡ ከዚያም በትንሣኤ ቀን የሠሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ አል ሙጃደላህ፤6-7

ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ ረ.ዐ እንደተዘገበው እንዲህ አለ – የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና እንዲህ በማለት መከሩን

يا أيها الناس، إنكم محشورون إلى الله تعالى حُفاة عُراة غُرْلاً

كَمَا بَدَأْنَا أَوَّلَ خَلْقٍ نُّعِيدُهُ ۚ وَعْدًا عَلَيْنَا ۚ إِنَّا كُنَّا فَاعِلِينَ

ألا إن أول الخلائق يكسى يوم القيامة إبراهيم، ألا وإنه سيجاء برجال من أمتى، فيؤخذ بهم ذات الشمال ن فـ أقول: يا رب أصحابى، فيقال: إنك لا تدرى ما أحدثوا بعدك، فـ أقول كما قال العبد الصالح

 ‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ወደ አላህ ሱ.ወ ባዶ እግራችሁን ፣ እርቃናችሁን ሆናችሁ እና ያልተገረዛችሁ ሆናችሁ ትቀሠቀሣላችሁ.. ካሉ በኋላ

የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን፡፡ (መፈጸሙ) በእኛ ላይ የኾነን ቀጠሮ ቀጠርን፡፡ እኛ (የቀጠርነውን) ሠሪዎች ነን፡፡ አል አንቢያእ፤104 የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡ፡፡ ከዚያም ‹አዋጅ! ከፍጡራን ሁሉ የቀያማ እለት መጀመሪያ የሚለበሠው ኢብራሂም ነው፡፡ አዋጅ! ከህዝቦቼ በተወሰኑ ሰዎች ይመጣል፡፡ ወደ ግራ በኩልም ይወሠዳሉ፡፡ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ! ህዝቦቼ ! እላለሁ፡፡›  ‹ አንተ ካለፍክ በኋላ ምን እንደፈፀሙ አታውቅም› እባላለሁ፡፡ እኔም ደጉ የአላህ ባሪያ እንዳለው እላለሁ-

 

وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِي كُنتَ أَنتَ الرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በነርሱ ላይ ተጣባበቂ ነበርኩ፡፡ በተሞላኸኝም ጊዜ (ባነሳኸኝ ጊዜ) አንተ በነሱ ላይ ተጠባባቂ ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» «ብትቀጣቸው እነርሱ ባሮችህ ናቸው፡፡ ለነርሱ ብትምርም አንተ አሸናፊው ጥበበኛው ነህ» (ይላል)፡፡ አል ማኢዳህ፤117-118

ለመልሱም እንዲህ እባላላሁ ‹አንተ ከተለየሃቸው ጊዜ ጀምሮ ወደኋላ ከመመለስ አልተወገዱም፡፡› እኔም ‹ይራቁ! ይራቁ!/ይጥፉ!/› እላለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡

« لا تزول قدما عبد حتى يسـأل: عن عمره فيم أفناه ؟ وعن علمه فيم فعل فيه ؟ وعن ماله من أين اكتسبه وفيم أنفقه ؟ وعن جسمه فيم أبلاه ؟ »

‹ በአራት ጉዳዮች ላይ እስካልተጠየቀ ድረስ የአንድ ባሪያ እግሮች አይንቀሣቀሱም፡፡ እድሜውን በምን እንዳሣለፈ፣ በእውቀቱ ምን እንደሠራበት፣ ገንዘቡን ከምን እንዳመጣና በምን ላይ እንዳዋለ እና ሰውነቱን በምን እንደጨረሠ፡፡›

******* ይቀጥላል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here