ልዩነትን በጥበብ ለማስተናገድ የሚረዱ የአስተሳሰብ መሠረቶች (ክፍል 1)

0
6442
 1. በጥቃቅንና በቅርንጫፍ አጀንዳዎች ዙሪያ መለያየት ጸጋ ነው፡፡
 2. ማእከላዊውን መንገድ መከተልና የሐይማኖት አጥባቂነትን መተው፡፡
 3. በአሻሚዎች ላይ ሳይሆን ግልጽና ጉልህ በሆኑ መልእክቶች ላይማተኮር፡፡
 4. በኢጅቲሐድ አጀንዳዎች ላይ ፍጹማዊነትን እና ውግዘትን መተው፡፡
 5. የዓሊሞችን የሐሳብ ልዩነቶች መነሻዎች መመርመር
 6. ስለቃላትና ለጽንሰ ሐሳቦች የጋራ ግንዛቤ መያዝ
 7. ሙስሊሙን በታላላቅ የኡምማው አጀንዳዎች እንዳያምጽ ማድረግ
 8. በሚግባቡበት ጉዳይ መረዳዳት
 9. የሐሳብ ልዩነት ባለባቸው ጉዳዮች መቻቻል
 10. ላኢላሀ ኢለላህያለን መጠንቀቅ

1- በጥቃቅንና ቅርንጫፍ አጀንዳዎች መወዛገብ ጸጋ ነው

በቅርንጫፍ የዲን አጀንዳዎች ሁሉንም ሰዎች በአንድ አስተያየትና በአንዲት ቀጭን መስመር ለማስኬድ የሚያስቡወገኖች የማይቻለውን እየሞከሩ ነው፡፡ በጥቃቅን አጀንዳናዎች ዙሪያ ያሉ የሐሳብ ልዩነቶችን ለማስቀረት የሚያደርጉትጥረት ልዩነትን ይበልጥ ያፋፍም እንደሆነ እንጅ አያጠፋውም፡፡ ግልጽ የሆነ የዋሕነትና አለመብሰልን የሚያመላክትምነው፡፡ ምክንያቱም በጥቃቅን የሸሪዓ አጀንዳዎች ዙሪያ የሐሳብና የግንዛቤ ልዩነት መኖሩ ሊቀር የማይችል ነገር ነውና፡፡ይህ ልዩነት እንዲከሰት ምክንያት የሆነው የራሱ የዲኑ ባህሪ፣ የዓረብኛ ቋንቋ ባህሪ፣ የሰው ልጅ ባህሪና የሕይወትናየተፈጥሮ ባህሪ ነው፡፡

የዲኑ ባህሪ

አላህ በዚህ ዲን ድንጋጌ የተላለፈባቸው እና በዝምታ የታለፉ አጀንዳዎች እንዲኖሩ ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ድንጋጌ ከተላለፈባቸውአጀንዳዎች ውስጥም ከፊሎችን ግልጽና የማያሻማ (ሙህከም) ሌሎችን ደግሞ አሻሚ (ሙተሻቢህ) በሆኑ ድንጋጌዎችገለጻቸው፡፡ የከፊሎቹ መረጃ ግልጽና ቁርጥ ያለ (ቀጥዒይ) ሲሆን የሌሎቹ ደግሞ አጠራጣሪ (ዞንይ) ነው፡፡ ከፊሎቹ መልእክታቸውበቀጥታ የሚታወቅ (ሶሪህ) ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በተዘዋዋሪ የሚታወቅ (ሙዓወል) ነው፡፡ ይህን ያደረገው አእምሮ ለምርምርክፍት በሆኑ አጀንዳዎች ዙሪያ ራሱን እንዲያስራና እንደመራመር፣ እንዲህ ያልሆነውን አጀንዳ ደግሞ በሩቅ ሚስጥርበማመን ያለ ጥያቄ እንዲቀበል ለማስቻል ነው፡፡ በዚህም አላህ የሰውን ልጅ ሲፈጥር የሻው ፈተና እውን ይሆናል፡፡                                                                            

إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا 

“እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡” (አል ኢንሳን፤ 2)

አላህ ቢሻ ኖሮ ሃይማኖትን በሙሉ አንድ ዓይነት ገጽታ እና ቅርጽ ያለው ለሐሳብ ልዩነት እና ለምርምር በር የማይከፍትያደርገው ነበር፡፡ የሐይማኖቱ ባህሪ፣ ከቋንቋ ባህሪ እንዲሁም ከሰው ልጆች ዝንባሌና ተፈጥሮ ጋር ተጣጥሞ የሰው ልጅ ሰፋና ዘና ያለ መስክ ያገኝ ዘንድ አላህ ይህን አላደረገም።

አላህ ቢሻ ኖሮ ሙስሊሞች በሁሉም ነገር ተመሳሳይ አቋም እንዲኖራቸው ያደርግ ነበር፡፡ እናም በምንም ነገር የሐሳብልዩነት አይኖርም፡፡ በቅርንጫፍም በመሠረታዊውም፡፡ ይህን ቢሻ ኖሮ ሁሉንም የቁርዓን ድንጋጌዎች ለተጨማሪ ግንዛቤ መንገድ የሚከፍቱ ግልጽና ጉልህ ያደርጋቸው ነበር፡፡ ግና አላህ በኪታቡ ውስጥ ግልጽና የማያሻሙ ድንጋጌዎች እንዲኖሩ ፈቀደ፡፡ እነዚህ የቁርአን እናቶች (መሰረቶች) እነርሱ ናቸው፡፡ ሌሎች ደግሞ አሻሚዎች እንዲሆኑ አደረገ፡፡በቁጥር አናሳ ናቸው፡፡

ይህ የሆነው በአንድ በኩል ለፈተና ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አእምሮ ምርምር እና ጥናት በማድረግ ለመሞረድናእንዲሰራ ለማስቻል ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

هُوَ الَّذِي أَنزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُّحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ 

እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው ሌሎችም ተመሳሳዮች አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡ (ትክክለኛ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ በዕውቀትም የጠለቁት «በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡ (አሊ-ዒምራን 7)

ወደ ትርጉሙ ከመሄዳችን በፊት ገና ከንባቡ ላይ እንኳ የስልት ልዩነት እናያለን፡፡ ሰባት አይነት የቁርአን ንባብ ስልቶች አሉ፡፡ እስከ አስርም ይደርሳሉ፡፡ ሁሉም በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ የንባብ ስልቶች ናቸው፡፡ ከሙስሊምዑለሞች አንዳቸውም እነዚህን የንባብ ስልቶች እንደ ችግር አላዩአቸውም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ከአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) የተገኙ ናቸውና፡፡

ቡኻሪ ኢብን መስዑድን በመጥቀስ የሚከተለውን ዘግበዋል፡-

አንድ ሰው አንዲት አንቀጽ ሲቀራ ሰማሁት፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ በተለየ ስልት ሲቀሯት ሰማሁ፡፡ ከሰውየው የሰማሁትን ነገርኳቸው፡፡ ከፊታቸው ላይ የመከፋት ስሜት አነበብኩ፡፡ እንዲህ አሉ፡-

ሁለታችሁም አሳምራችሁ አንብባችሁታል፡፡፡ አትወዛገ፡፡ ከናንተ በፊት የነበሩ ሕዝቦች ተወዛገና ጠፉ፡፡”  (ቡኻሪ)

ሌሎች የሐዲስ አውታሮችም ዑመር ቢን ኸጧብን በመጥቀስ ተመሳሳይ ዘገባ አስፍረዋል፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)

ኢብንል ወዚር ይህን ጉዳይ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ እንዲህ ብለዋል፡-

የአላህ መልዕክተኛ የከለከሉት መወዛገብ የጠላትነት ስሜት የተቀላቀለበትን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ስሜት በሌለበት ሁኔታ በሐሳብ መለያየት፣ አንድን ነገር በተለያየ አቅጣጫ መመልከትንማ እርሳቸው ራሳቸው አጽድቀውታል፡፡ ለኢብን መስዑድ፡-ሁለታችሁም አሳምራችሁ ቀርታችሁታል  ማለታቸውን አላስተዋልክምን? ይህን ያሉት የንባብ ልዩነት መኖሩን በነገራቸው ጊዜ ነው፡፡ ሁለቱም ትክክል እንደሆኑና እንዳሳመሩ ከነገሯቸው በኋላም እንዳይወዛገቡ አስጠነቀቋቸው፡፡ እናም የጥላቻ ስሜት የሌለበት የሐሳብ ልዩነት ተቀባይነት አለው፡፡ እንዲያውም በነቢዩ  መልካም  ተሰኝቷል፡፡ የሐሳብ ልዩነት የሚወገዘው የጠላትነት ስሜት ሲቀላቀልበትና መናቆር፣ መሻኮት፣ አንዱ ሌላውን የማስተባበል ሁኔታ ሲከሰትና ግንኙነት ሲበከል፣ እስልምና ሲዳከም፣ ጠላቶች በኢስላም ላይ የበላይነት የሚያገኙበት ሁኔታ ሲመቻች ነው፡፡ መልካሙ የሐሳብ ልዩነት ደግሞ ሁሉም በሚያውቀው ሲሰራና ከርሱ የተለየ እይታ ያለውን ወገን መጥላትንና ማውገዝን ሲያቆም ነው፡፡ ቀደምት ሙስሊሞች ማለትም የነቢዩ ቤተሰቦች፣ ሶሐቦችና ታቢዒዮች በዚሁ ስልትና መንገድ ኖረዋል፡፡

የቋንቋ ባህሪ

ከቋንቋ ባህሪ ጋር በተያያዘ የኢስላም አበይት ምንጮች ቁርአንና ሐዲስ እንደሆኑ እሙን ነው፡፡ አማኞች አምነው እንዲቀበሉም እንዲሰሩባቸውም የሚጠየቁት የቁርአንና የሐዲስ ውሳኔዎችን ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا 

አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ (አል አህዛብ 36)

ቁርዓን ቃላዊ ድንጋጌ ነው፡፡ ብዙዎች ሱንናዎችም እንዲሁ ቃላዊ ድንጋጌዎች ናቸው፡፡ የትኛውንም የቋንቋ አገላለጽ በመረዳቱ ሂደት የሚያጋጥ  የሐሳብ ልዩነቶች ሁሉ የቁርዓንን እና የሐዲስን ድንጋጌዎች በመረዳቱ ሂደትም ያጋጥማሉ፡፡ምክንያቱም ቁርአንና ሐዲስ የተነገሩት የዓረብኛ የቋንቋን ባህሪ መሠረት አድርገው ነውና፡፡ እናም ከአንድ በላይ ትርጉም ያለው ቃል፣ ግልጽ (ሐቂቃ)፣ ቅንያዊ (መጃዝ)፣ ቀጥተኛ መልእክት ያለው (መንጢቅ) እና ከዚህ የተለየ (መፍሁም) አለ፣አጠቃላይ (ዓም) እና የተለየ (ኻስ)፣ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) እና የተገደበ (ሙቀየድ) አገላለጾችን በቁርአንና በሐዲስውስጥ እናገኛለን፡፡ ከነዚህ ሁሉ ቀጥተኛ መልእክት ያለው እንዳለ ሁሉ አሻሚ የሆነም አለ፡፡ ሚዛን የማይደፋና ሚዛንየሚደፋ አለ፡፡ አንዱ ዓሊም ሚዛን ይደፋል ያለውን ሌላው ሚዛን አይደፋም ይላል፡፡

ለምሳሌ በአል ማኢዳህ ምእራፍ ውስጥ የሰፈረውን የጦሃራ አንቀጽ ለአብነት ማየት እንችላለን፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል፡–

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا قُمْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ فَاغْسِلُوا وُجُوهَكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ إِلَى الْمَرَافِقِ وَامْسَحُوا بِرُءُوسِكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ إِلَى الْكَعْبَيْنِ ۚ وَإِن كُنتُمْ جُنُبًا فَاطَّهَّرُوا ۚ وَإِن كُنتُم مَّرْضَىٰ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَاءَ أَحَدٌ مِّنكُم مِّنَ الْغَائِطِ أَوْ لَامَسْتُمُ النِّسَاءَ فَلَمْ تَجِدُوا مَاءً فَتَيَمَّمُوا صَعِيدًا طَيِّبًا فَامْسَحُوا بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُم مِّنْهُ ۚ مَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيَجْعَلَ عَلَيْكُم مِّنْ حَرَجٍ وَلَٰكِن يُرِيدُ لِيُطَهِّرَكُمْ وَلِيُتِمَّ نِعْمَتَهُ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ 

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ። ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡ (አል-ማኢዳህ 6)

በዚህ አንቀጽ ዙሪያ ከቋንቋ ግንዛቤ ጋር በተያያዘ ብቻ በርካታ እይታዎች ከዑለሞች ተሰንዝረዋል፡፡

 • በአንቀጹ ውስጥ የተጠቀሱ የአካል ክፍሎችን በተቀመጡበት ቅደም ተከተል ማጠብ ግዴታ ነው ወይስ አይደለም?
 • እስከ ክርናችሁና እስከ ቁርጭምጭሚታችሁ እጠቡ በሚለው ገለጻ ውስጥ ቁርጭምጭሚት እና ክንድ ከትጥበትውስጥ ይካተታሉ ወይስ አይካተቱም?
 • የሚታበሰው ሙሉ ራስ ነው ወይስ ከፊሉ?
 • ሴት ከነካችሁ የሚለው አገላለጽ ሴት በአካል መንካትን ነው የሚያመለክተው ወይስ ኢብን አባስ እንደሚሉት ጾታዊግንኙነት ነው?
 • ለተየሙም እንደሚውል የተገለጸው የምድር አካል ምንድን ነው? አፈር ነው? ወይስ የምድር አካል የሆነ የትኛውምነገር?
 • በተየሙም ወቅት የሚታበሰው እስከመዳፍ አንገት ነው ወይስ ልክ እንደ ውዱእ እስከክርን ድረስ?
 • ውሃ ካላገኛችሁ የሚለው ገለጻ ምንን ያመለክታል? እርግጥ ውሃ ማጣትን ብቻ ነው ወይስ ውሃም እያለለመጠጥ፣ ለምግብ ማብሰያ እና መሰል መሠረታዊ አስፈልጎቶች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንደሌለ ይቆጠራል?

በእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች የፊቅህ ጠበብት የየራሳቸውን አቋም ይዘዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here