መልእክተኞች (ክፍል 1)

0
4985
  • ወደ ሁሉም ህዝቦች መልእክተኛ ተልኳል
  • መልእክተኛ የሰው ልጅ ነው
  • መልእክተኛ በፆታ ወንድ ነው
  • መልእክተኞች የተላኩበት ዋና ምክኒያት
  • ነቢያቶች ከማንኛውም ወንጀል የተጠበቁ (ማዕሱም) ናቸው
  • ስለ አላህ መልእክተኞች ከተባሉት
  • ከአላህ መልእክተኞች መካከል እጅግ ፅኑዎች /ኡሉል ዐዝም/
  • የነቢይነትና የሰማያዊ መልእክት መቋጫ ማግኘት
  • የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያከናወኗቸው ትላልቅ ተግባራት
  • እውነተኝነታቸውን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች
  • ስለ መምጣታቸው የተነገሩ ብሥራቶች
  • የመልክተኞች ሙዕጂዛ /ተዓምራት/
  • በመልእክተኞች ተዓምራትና በሌሎች ተዓምራት (ኸዋሪቅ) መካከል ያለው ልዩነት
  • የሙዕጂዛና የከራማ ልዩነት
  • የነቢያት መጨረሻ የሆኑት የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሙዕጂዛ

ሙስሊም የሆነ ሰው ሁሉ ያለ አንዳች ልዩነት በአላህ መልእክተኞች በሙሉ ያምን ዘንድ አላህ (ሱ.ወ) ግዴታ አድርጎበታል። ልቅናው ከፍ ያለ ጌታ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ:

قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

“በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን በሉ።” (አል-በቀራህ 2፤ 136)

ይህም በአላህ ያመኑ ሰዎች እምነት መሆኑን በመግለፅም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ:

آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ ۚ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ

“መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ። ምእምኖቹም (እንደዚሁ)። ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ ‘በአንድም መካከል አንለይም’ (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ። ‘ሰማን፤ ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)። መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው’ አሉም።” (አል-በቀራህ 2፤ 285)

መልካምነትም (ቢር) በኢማን ውስጥ የሚጠቃለል መሆኑን ተናግሯል። እንዲህ በማለት

وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ

“ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው” (አል-በቀራህ 2፤ 177)

አንድ ሰው ከአላህ (ሱ.ወ) መልእክተኞች መካከል በከፊሎቹ ቢያምንና በከፊሎቹ ደግሞ ቢክድ አሊያም ቢያስተባብል ከማመንም አንፃር በነሱ መካከል ልዩነት የሚያደርግ ከሆነ የከሀዲ /ካፊር/ ብይን ይሠጠዋል። ለምን ቢባል አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ ውስጥ ይህን ብይን አስተላልፏልና ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

إِنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُوا بَيْنَ اللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ وَنَكْفُرُ بِبَعْضٍ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُوا بَيْنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا
أُولَٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ حَقًّا 

“እነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ የሚክዱ፣ በአላህና በመልክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉ፣ ‘በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን’ የሚሉ፣ በዚህም መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፤ እነዚያ በውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው።” (አን-ኒሣእ 4፤ 150-151)

ከተላኩት መልእክተኞች ውስጥም አላህ (ሱ.ወ) ስለ ከፊሎቹ የነገረን ሲሆን ሥማቸውንም በቁርኣን ውስጥ አንስቶልናል። ስለነሱ ያልነገረንም እንዲሁ አሉ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَرُسُلًا قَدْ قَصَصْنَاهُمْ عَلَيْكَ مِن قَبْلُ وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ

“ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውን መልክተኞች (እንደላክን ላክንህ)።” (አን-ኒሣእ 4፤ 164)

የተነገሩን የአላህ መልእክተኞች ብዛታቸው ሀያ አምስት ሲሆን አብዛኞቹም በሚከተለው የቁርኣን አንቀፅ ውስጥ የተጠቀሱት ናቸው።

وَتِلْكَ حُجَّتُنَا آتَيْنَاهَا إِبْرَاهِيمَ عَلَىٰ قَوْمِهِ ۚ نَرْفَعُ دَرَجَاتٍ مَّن نَّشَاءُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ
وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ۚ كُلًّا هَدَيْنَا ۚ وَنُوحًا هَدَيْنَا مِن قَبْلُ ۖ وَمِن ذُرِّيَّتِهِ دَاوُودَ وَسُلَيْمَانَ وَأَيُّوبَ وَيُوسُفَ وَمُوسَىٰ وَهَارُونَ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
وَزَكَرِيَّا وَيَحْيَىٰ وَعِيسَىٰ وَإِلْيَاسَ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّالِحِينَ
وَإِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَيُونُسَ وَلُوطًا ۚ وَكُلًّا فَضَّلْنَا عَلَى الْعَالَمِينَ

“ይህችም ማስረጃችን ናት። ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ (አስረጅ እንድትኾን) ሰጠናት። የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና። ለርሱም ኢስሐቅን (የልጅ ልጁን) ያዕቁብንም ሰጠነው። ሁሉንም መራን። ኑሕንም በፊት መራን። ከዘሮቹም ዳውድን፣ ሱለይማንንም፣ አዩብንም፣ ዩሱፍንም፣ ሙሳንም፣ ሃሩንንም (መራን)። እንደዚሁም በጎ ሰሪዎችን እንመነዳለን። ዘከሪያንም፣ የሕያንም፣ ዒሳንም፣ ኢልያስንም (መራን)። ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው። ኢስማዒልንም፣ አልየስዕንም፣ ዩኑስንም፣ ሉጥንም (መራን)። ሁሉንም በዓለማት ላይ አበለጥናቸውም።” (አል-አንዓም 6፤ 83-86)

ከላይ በተጠቀሰው የቁርኣን አንቀፅ ውስጥ የተዘረዘሩት መልእክተኞች በቁጥር አሥራ ስምንት ሲሆኑ በተለያየ የቁርኣን አንቀፅ ውስጥ በተጠቀሱት ሌሎች ሰባቶችም ማመን ግዴታ ነው። እነኚህም አንቀፆች

إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ آدَمَ وَنُوحًا وَآلَ إِبْرَاهِيمَ وَآلَ عِمْرَانَ عَلَى الْعَالَمِينَ

“አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ የዒምራንንም ቤተሰብ በዓለማት ላይ መረጠ።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 33)

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا

“ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። (አል-አዕራፍ 7፤ 65)

وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا 

“ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)።” (ሁድ 11፤ 61)

وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا

“ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)።” (ሁድ 11፤ 84)

وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ

وَأَدْخَلْنَاهُمْ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُم مِّنَ الصَّالِحِينَ

“ኢስማዒልንም ኢድሪስንም ዙልኪፍልንም (አስታውስ)። ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው።ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው። እነሱ ከመልካሞቹ ናቸውና።” (አል-አንቢያእ 21፤ 85-86)

مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ

“ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም። ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው። አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።” (አል-አህዛብ 33፤ 40)

የነቢያት ቁጥር በአጠቃላይ 124 ሺህ እንደሆነ ተዘግቧል።

መልእክተኛ ያልተላከለት ህዝብ የለም

እነኚህንም መልእክተኞች አላህ (ሱ.ወ) በየዘመኑ ወደ ተለያዩ ህዝቦች የላከ ሲሆን ይህም የሆነው በረጅም ዘመናት ውስጥ ነው። በአጠቃላይ መልኩ ግን ወደ አላህ (ሱ.ወ) መንገድ የሚጠራ ሀቅንም የሚያመላክት የሆነ መልእክተኛ ሣይላክበት የቀረ አንድም ህዝብ የለም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

تَاللَّهِ لَقَدْ أَرْسَلْنَا إِلَىٰ أُمَمٍ مِّن قَبْلِكَ

“በአላህ እንምላለን፤ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ (መልክተኞችን) ልከናል።” (አን-ነህል 16፤ 63)

وَإِن مِّنْ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٌ

“ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም።” (ፋጢር 35፤ 24)

وَلِكُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولٌ

“ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው።” (ዩኑስ 10፤ 47)

وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ

“ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።” (አር-ረዕድ 13፤ 7)

መልእክተኛ የሚመረጠው ከዚያው ከተላከበት ህዝብ ውስጥ ነው

የአላህ መልእክተኛ የሰው ልጅ ሲሆን የሚመረጠውም ከዚያው ከተላከበት ህዝብ የተከበረ ቤተሰብ ውስጥ ነው። የተመረጠውንም መልእክተኛ አላህ (ሱ.ወ) በርካታ በላጭና ምርጥ ነገሮችን የሚሠጠው ሲሆን በአዕምሮም ሆነ በመንፈሣዊ አቋሙም የበለፀገ እንዲሆን ያደርገዋል። ይህም የተደረገው መልእክተኛው መለኮታዊውን ራእይ ለመቀበል ዝግጁ ይሆን ዘንድ ነው። መለኮታዊው ራእይ ከባድ አደራ ነውና ብቃት ላለው ሰው እንጂ አይሠጥም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

اللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُ

“አላህ መልክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ዐዋቂ ነው።” (አል-አንዓም 6፤ 124)

اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

“አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል። ከሰዎችም (እንደዚሁ)፤ አላህ ሰሚ ተመልካች ነው።” (አል ሀጅ 15፤ 75)

አላህ (ሱ.ወ) ለመረጠው ለመልእክተኛው ለየት ያሉና የተከበሩ ነገሮችን የሚሠጠው ታላቁን መልእክት ለመሸከም እንዲችል ሊያጠናክረውና ሰዎችም በሃይማኖታዊም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮቻቸው ውስጥ ምሣሌያቸው አድርገው እንዲከተሉት ነው። የአላህ መልእክተኞች በነኚህ ልዩና ምጡቅ በሆኑ መንፈሣዊም ሆነ አእምሮኣዊ ስብእና ከሌሎች ባይለዩ ኖሮ ሰዎችን ወደ አላህ መንገድ የመምራትን ሀላፊነት ለመሸከም በተሳናቸው ነበር።

መልእክተኛ እንደ ማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ይበላል ይጠጣል

በአላህ (ሱ.ወ) የተመረጠ መልእክተኛ በባህሪውና በስብእናው ካልሆነ በስተቀር በአፈጣጠሩ ከሰው ልጅ የተለየ አይደለም። እንደማንኛውም የሰው ልጅ ይበላል ይጠጣል፤ ይገበያያልም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَمَا أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ الْمُرْسَلِينَ إِلَّا إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ الطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِي الْأَسْوَاقِ

“ከአንተ በፊትም ከመልክተኞች እነሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም።” (አል ፉርቃን 25፤ 20)

መልእክተኛ ያገባል

በአላህ (ሱ.ወ) የተመረጠ መልእክተኛ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ሁሉ ትዳር አለው፤ ያገባል ፤ ልጅም ይወለድለታል።

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَاجًا وَذُرِّيَّةً

“ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል። ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል።” (አር-ረዕድ 13፤ 38)

አንድ የአላህ መልእክተኛ ከድሎትም ይሁን ከችግር የሰው ልጅ የሚገጥመው ነገር ሁሉ ይገጥመዋል

የአላህ መልእክተኛ ከጤናም ይሁን ከበሽታ፤ ከጥንካሬና ብርታት፤ ከህመምና ከድሎት፣ ከሕይወትም ይሁን ከሞት የሰውን ልጅ የሚያገኝ ነገር ሁሉ ያገኘዋል። ነገር ግን ከሌሎች የሚለየው ለክስተቶቹ በሚሠጠው አፀፋ ነው። አንድ የአላህ መልእክተኛ ለአስደንጋጭ ነገሮች እንኳ የሚሠጠው ምላሽ በዙሪያው ያሉትን የሚያስበረግግ አይደለም። የአላህ መልእክተኛ በስብእናው የተሟላ ነውና ሁሉንም ዓይነት የህይወት ገፅታዎች አላህ በሚወደው መልኩ ያስተናግዳል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَكَشَفْنَا مَا بِهِ مِن ضُرٍّ ۖ وَآتَيْنَاهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَابِدِينَ

“አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን ‘እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ’ ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)።ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው። ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን። ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው።” (አል-አንቢያእ 21፤ 83-84)

وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ انقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا
 

“ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም። ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 144)

የአላህ መልእክተኛ በራሱ ሀይል የለውም። የችሎታውም ምንጭ አላህ (ሱ.ወ) ነው። እንቅስቃሴውም ሁሉ በአላህ ፈቃድ ሥር ነው። የትኛውም መልእክተኛ ቢሆን በነገሮች ላይ የማዘዝ ፍፁም የሆነ ሥልጣንም ሆነ ነገሮችን የመገለባበጥና እንደሻው የማድረግ አቅም የለውም። በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ለራሱም ይሁን ለሌላ ጥቅምን ማስገኘት ሆነ ጉዳትን ማራቅ አይቻለውም። በአላህ ፈቃድ ላይም ተፅእኖ ማሣደር አቅም የለውም። ከሩቅ እውቀትም ቢሆን እንዲያውቅ አላህ የሻለትን መጠን እንጂ ሊያውቅ አይችልም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

“አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም። ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር። እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው።” (አል-አዕራፍ 7፤ 188)

በሌላም አንቀፅ እንዲህ ብሏል

عَالِمُ الْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِ أَحَدًا
إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا
لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

“(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው። በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም። ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)። እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል። እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)።” (አጅ-ጅን 72፤ 26-28)

መልእክተኛ በፆታ ወንድ ነው

የመልእክተኛ ፆታ ወንድ ነው። አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች መልእክተኛ አድርጎ መልዓክ አሊያም ሴት ልጅን አልላከም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَمَا أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ

“ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም።” (አል-አንቢያእ 21፤ 7)

قُل لَّوْ كَانَ فِي الْأَرْضِ مَلَائِكَةٌ يَمْشُونَ مُطْمَئِنِّينَ لَنَزَّلْنَا عَلَيْهِم مِّنَ السَّمَاءِ مَلَكًا رَّسُولًا

“በምድር ላይ ረግተው የሚኼዱ መላእክት በነበሩ ኖሮ በእነሱ ላይ (ከጎሳቸው) የመልአክን መልክተኛ ባወረድን ነበር በላቸው።” (አል-ኢስራእ 17፤ 95)

……

(ይቀጥላል)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here