ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር (ክፍል 1)

0
4334

ሥነ-ምግባር ቁርዐን ውስጥ

ሃያልና አሸናፊው አላህ የተከበረ ቁርዐኑን ያወረደው ለነብያቱ መሪ መንገድን ሊያበራላቸው ሲሆን ይህ ብርሃን ከመንገዶች ሁሉ ሙሉ ወደሆነው የሚመራቸውና የተመረጠም ነው። ይህ መንገድ መልካም ስነምግባርን የሚያላብስ፣ ጉብጠትን የሚያርቅ፣ ብልሹውን የሚስተካክል ነው። ስለሆነም ያማረ ስነ-ምግባርን በሚመለከት የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤትን የሚያሞካሽና መልካም ስነ-ምግባር የሚሠሩትን የሚያሞግሱ በርካታ መረጃዎች በቁርዐን ውስጥ መምጣታቸው የሚደንቅ አይደለም። እንዲሁም በጣም በርካታ የቁርኣን መረጃዎች የአላህ ባርያዎች የአላህን ውዴታና ከአላህ የሚገኘውን ምንዳ ያገኙ ዘንድ ሊላበሷቸው ስለሚገቧቸው ባህሪያት አትተዋል።

  • የሉቅማን ምክሮች

ሃያልና አሸናፊው አላህ፣ ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ጥቅል የሆኑ ምክሮችን በመከሩበት አጋጣሚ ስለባህርይው ይነግረናል። ቁርኣን በሉቅማን ምዕራፍ ቁጥር 13 ላይ:-

وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

“ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣኦትን) አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና። ያለውን (አስታውስ)”  (ሉቅማን 31፤13)

ሉቅማን ምክራቸውን የጀመሩት ከሁሉም የላቀና የከበደ የሆነውን እንዲሁም አጥብቆ ሊይዙት የሚገባ የሆነውን ሃያልና አሸናፊው አላህን ብቻ ማምለክ እንዳለበት ነው። ይህም የነገሩ ሁሉ ቁንጮና የኢስላም መሠረት ነው። ከዚያ የጥራትና የልዕልና ባለቤት የሆነውን አላህን ታላቅነቱን፣ በሁሉም ነገሮች ላይ ያለውን እውቀት፣ ያብራሩለታል፡-

يَا بُنَيَّ إِنَّهَا إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ فَتَكُن فِي صَخْرَةٍ أَوْ فِي السَّمَاوَاتِ أَوْ فِي الْأَرْضِ يَأْتِ بِهَا اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ

“(ሉቅማንም) ልጄ ሆይ! እሷ (ደጊቱም ሠናይቱም ሥራ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትኾንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትኾን አላህ ያመጣታል። አላህ ሩህሩህ ውስጠ ዐዋቂ ነውና” (ሉቅማን31፤16)

ከዚያም ሉቅማን ልጃቸውን ሃያልና አሸናፊው የሆነው አላህ ያዘዘውን ግዴታ እንዲወጣ ምክራቸውን ቀጥለው፣ ሶላት ላይ ቀጥ እንዲል፣ በመልካም እንዲያዝ፣ ከአፀያፊ ተግባር እንዲርቅ፣ በሚያጋጥሙት ችግሮች በትዕግስት እንዲወጣቸው ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-

يَا بُنَيَّ أَقِمِ الصَّلَاةَ وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

“ልጄ ሆይ! ሰላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ፤ ከሚጠላው ሁሉ ከልክል በሚያገኝህ መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚይያዙ ነገሮች ነው” (ሉቅማን31፤17)

ይህ ቁርኣናዊ መልዕክት አማኝ አንቀጹ ውስጥ የተወሱትን ተግባሮች የግዴታ መፈጸም እንዳለበት ጠቋሚ ነው። ዐብደላ ኢብኑ ዐባስ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና:-

من حقيقة الإيمان الصبر على المكاره

ከእምነት የእውነትነት መገለጫ ውስጥ መካከል በሚጠሉት ነገር ላይ የሚደረግ ትዕግስት ነው” ይላሉ።

አሁንም ሉቅማን ምክራቸውን በመቀጠል ልጃቸው ከአንዳንድ መጥፎ ባህሪያት መራቅ እንዳለበት እንዲህ ይመክሩታል፡-

وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ

“ጉንጭህንም (በኩራት) ከሠዎች አታዙር በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛና ሁሉ አይወድምና” (ሉቅማን31፤18)።

በመጨረሻም እራሡን እንዲያስተናንስ፣ በአረማመዱ የኩራተኛ አካሄድን እንዳይሄድ፣ ድምጹን ዝግ እንዲያደርግ ይመክሩታል፡-

وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِن صَوْتِكَ ۚ إِنَّ أَنكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ

“በአካሄድህም መካከለኛ ኹን ከድምፅህም ዝቅ አድርግ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የእህዬች ድምጽ ነውና” (ሉቅማን፣ 19)።

  • የሩህሩህ የሆነው አላህ ባርያዎች (ኢባዱረህማን ) ባህሪያት

አላህ ባርያዎቹን በመልካም ባህሪይ ይታነጹ ዘንድ በአልፉርቃን ምዕራፍ ቁጥር 63-76 ላይ የሱን ቅን አገልጋይ ባርያዎች ባህሪያት ሠብሠብ አድርጎ ያቀርብልናል። ከባህሪያቱም መካከል በአረማመዳቸው ከኩራትና ከአምባገነንነት አካሄድ የራቀ አካሄድን መሄድ እንዳለባቸው ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡-

وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا

“የአልረህማንም ባሪያዎች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት” (አል-ፉርቃን25፤63) ይላል።

የአላህ ባርያዎች ከቂላቂሎች የራቁ መሆናቸውን ሲገልፁ ደግሞ፡-

وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا

“…ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት  ናቸው” (አል-ፉርቃን25፤63)።

በሌላ አንቀጽ ደግሞ የአል-ረህማንም ባሪያዎች የአላህን ውዴታና ፍቅር ለማግኘት ሃያልና አሸናፊውን አላህ ሌት ከቀን የሚገዙ መሆናቸውን አላህ ሲገልጽ፡-

وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا
“እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው” (አል-ፉርቃን25፤64) ይላል።
እነሡም ለሃያልና አሸናፊው ጌታቸው ተገዢ ከመሆናቸውም ባሻገር የሡን ቅጣት ፈርተው ከገሃነም ቅጣት እንዲጠብቃቸው አላህን የሚማፀኑ መሆናቸውን አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا إِنَّهَا سَاءَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

“እነዚያም ጌታችን ሆይ የገሃምን ቅጣት ከኛ ላይ መልስልን ቅጣቱ የማያልቅ ነውና የሚሉት ናቸው እርሷ መርጊያና መቀመጫ በመሆን ከፋች!”  (አል-ፉርቃን 25፤65-66) ይላል ።

በሚለግሱበት ጊዜ ገንዘባቸውን አባካኞችና ንፉጎች (ገንዘባቸውን ያላግባብ የሚቆጥቡ) አለመሆናቸውን አላህ ሲገልጽ፡-

وَالَّذِينَ إِذَا أَنفَقُوا لَمْ يُسْرِفُوا وَلَمْ يَقْتُرُوا وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا

“እነዚያም በለገሡ ጊዜ የማያባክኑት የማይቆጥቡትም ናቸው በዚህም መካከል (ልግሥናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው” (አል-ፉርቃን25፤67)።

እንዲሁም ከባዕድ አምልኮ የራቁ፣ ያለአግባብ የሰውን ህይወት ለማጥፋት የማይሞክሩ፣ የሠዎችን ክብር ለማጉደፍ የማይሞክሩ ናቸው። እነዚህን ወንጀሎች መስራት ከባድ ወንጀልና ለገሃነም እሳት የሚዳርግ መሆኑን ስለሚገነዘቡ ነው። አላህ በዚህ ላይ ሲነግረን፡-

وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا 
يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا
إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَإِنَّهُ يَتُوبُ إِلَى اللَّهِ مَتَابًا

“እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክን የማይገዙት ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት የማያመነዝሩትም ናቸው ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። በትንሳቼ ቀን ቅጣቱ ለርሱ ይደራረባል በርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል። ተፀፅቶ የተመለሰና ያመነ መልካምም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል አላህም እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው። ተፀፅቶ የተመለሰም ሰው መልካምንም የሠራ እርሱ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል”  (አል-ፉርቃን 25፤68-71) ይለናል።

በእብለትና በሀሰት መጥፎና እኩይ መሆናቸውን ለሚመሰክሩባቸው ሰዎች የማይተባበሩ መሆናቸውን አላህ ሲገልጽ፡-

وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ
“እነዚያ እብለትን የማይመሰክሩ ናቸው” (አል-ፉርቃን25፤72) ይላል።
ጊዜያቸውን በአግባቡ ጠብቀውና ውድቅ ከሆነ ቀልድና ጨዋታ ጊዜያቸውን የማያሳልፉ መሆናቸውን ሲገልፅ:-
وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا

“በውድቅ ቃልም (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ ጊዜ የከበሩ ኾነው የሚያልፉት ናቸው”  (በአል-ፉርቃን25፤72) ይላል።

በቁርኣን አንቀጾች በተገሠጹ ጊዜ አላህን የሚፈሩና ታዛዥነታቸውን የሚገልጹ ስለመሆናቸው ደግሞ፡-

وَالَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ لَمْ يَخِرُّوا عَلَيْهَا صُمًّا وَعُمْيَانًا

“እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች በተገሠጹ ጊዜ (የተረዱና ተቀባዮች ኾነው እንጂ) ደንቆሮዎችና እውሮች ኾነው በርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው” (አል-ፉርቃን25፤73) ይላል።

እንዲሁም ሃያልና አሸናፊውን አላህ ከችሮታው መልካም የሆኑ ሚስቶችንና ከነሱም መልካም ዘሮችን እንዲሰጣቸው የሚለምኑና ዘሮቻቸውን (ልጆቻቸውን) ቅን መሪ እንዲያደርጋቸው የሚጠይቁ መሆናቸውን አላህ ሲነግረን፡-

وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا

“እነዚያም ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያ ለኛ ስጠን አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን የሚሉት ናቸው”      (አል-ፉርቃን25፤74) ይላል።                                                                                                       አላህ በመልካም ባህሪያት ለታነፁ ሰዎች ጀነትን ቃል የገባላቸው መሆኑን አላህ ሲገልጽ ፡-

أُولَٰئِكَ يُجْزَوْنَ الْغُرْفَةَ بِمَا صَبَرُوا وَيُلَقَّوْنَ فِيهَا تَحِيَّةً وَسَلَامًا
خَالِدِينَ فِيهَا ۚ حَسُنَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

“እነዚያ በመታገሣቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ በርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይሠጣሉ። በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ኾነው (ይሰጣሉ) መርጊያና መኖሪያነቱ አማረች።”  (አል-ፉርቃን25፤75-76) ይላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here