ከሰማይ የወረዱ /ሰማያውያን/ መፅሃፍት (ክፍል 1)

0
4166
  •  በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት
  • የተከበረው ቁርኣን.. የመጨረሻው መፅሃፍ
  • የተውራት /ኦሪት/ መበረዝ
  • የኢንጂል /ወንጌል/ መበረዝ
  • የተከበረው ቁርኣን የቀደሙትን መፅሃፎች እውነትነት ስለማረጋገጡ
  • ወደ እውነት የሚያደርሰው መንገድ

ከሰማይ በወረዱት መፅሃፍት ማመን (አል-ኢማን ቢኩቱብ አስ-ሰማዊያ) ከስድስቱ የእምነት ምሶሶዎችን (አርካን አል-ኢማን) ውስጥ በሶስተኛ ደለጃ የተጠቀሰ ነው። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አበይት የእምነት ክፍል በዝርዝል እንመለከታለን።

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ወደ መልእክተኞቹና ነቢያቶቹ ወህይ ያደረጋቸው /በራእይ የገለፀላቸው/ የሆኑ ምክሮችና ትምህርቶች አሉ። ከነኚህም መካከል በመፅሀፍ መልክ የተጠረዙ ያሉ ሲሆን ከነኚህም ውጭ እኛ የማናውቃቸው የሆኑ አሉ። ሁሉም ነቢይ የተላከበትን መልእክት ወደ ህዝቦቹ አድርሷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَمَا اخْتَلَفَ فِيهِ إِلَّا الَّذِينَ أُوتُوهُ مِن بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۖ فَهَدَى اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا لِمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ مِنَ الْحَقِّ بِإِذْنِهِ ۗ وَاللَّهُ يَهْدِي مَن يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
[٢:٢١٣]
“ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)። አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ። ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ።” (አል-በቀራህ 2፤ 213)

فَإِن كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِّن قَبْلِكَ جَاءُوا بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَالْكِتَابِ الْمُنِيرِ
[٣:١٨٤]
“ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በጽሑፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል።”(ኣሊ ዒምራን 3፤ 184)

በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት 

1. በነቢዩ ሙሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ተውራት /ኦሪት/

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

إِنَّا أَنزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ ۚ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالْأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِن كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ ۚ فَلَا تَخْشَوُا النَّاسَ وَاخْشَوْنِ وَلَا تَشْتَرُوا بِآيَاتِي ثَمَنًا قَلِيلًا ۚ وَمَن لَّمْ يَحْكُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ
[٥:٤٤]
“እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን። እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ። ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 44)

وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنزَلَ اللَّهُ عَلَىٰ بَشَرٍ مِّن شَيْءٍ ۗ قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ
[٦:٩١]

2. በነቢዩ ዒሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ኢንጂል /ወንጌል/

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَقَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ ۖ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ
[٥:٤٦]
“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን። ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 46)
3. በነቢዩ ዳውድ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ዘቡር

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
[١٧:٥٥]
“ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል።” (አል-ኢስራእ 17፤ 55)

4. በነቢዩ ኢብራሂም እና በነቢዩ ሙሣ (ዓ.ሠ) ላይ የወረዱት ፅሁፎች /ሱሁፍ/

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ﴿٣٦﴾ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ﴿٣٧﴾ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ﴿٣٨﴾ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ﴿٣٩﴾ وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ﴿٤٠﴾ ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ﴿٤١﴾ وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنتَهَى

 

“ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል። መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው።” (አን-ነጅም 53፤36-42)

 

قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ﴿١٤﴾وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ ﴿١٥﴾ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ﴿١٦﴾ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ﴿١٧﴾ إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ﴿١٨﴾ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ﴿١٩﴾

 

“የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ። የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ። ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ። መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን። ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው። በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ።” (አል-አዕላ 87፤ 14-19)

 ከአቢ ዘር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው ለአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

“በኢብራሂም ላይ የወረዱ ፅሁፎች ምን ይመስሉ ነበር? በማለት ጠየቅኳቸው። እርሣቸውም ‘ሁሉም ምሣሌዎች ናቸው።’ በማለት መለሱ።

أيها الملك المسلط، المبتلى، المغرور، إنى لم أبعثك بتجمع الدنيا بعضها على بعض، ولكنى بعثتك لترد عنى دعوة المظلوم، فإنى لا أردها وإن كانت من كافر

‘አንተ አምባገነን፣ የተፈተንክና የተታለልክ ንጉስ ሆይ! እኔ ዱኒያን አንዷን ባንደኛዋ ላይ እንድትሰበስብ አይደለም የላክሁህ። ነገር ግን የላክሁህ የተበዳይ ስሞታን ከኔ ምላሽ እንድትሰጥ ነው። እኔ እሷ /የተበዳይ ስሞታ/ የከሀዲ እንኳን ብትሆን ምላሽ ሣልሠጥ የምተው አይደለሁም።’

وعلى العاقل – ما لم يكن مغلوبًا على عقله – أن يكون ساعات:

فساعة يناجى فيها ربه.

وساعة يحاسب فيها نفسه.

وساعة يتفكر فيها فى صنع الله عز وجل.

وساعة يخلو فيها لحاجته من المطعم والمشرب

ማንኛውም ብልህ የሆነ ሰው በአእምሮው ጤነኛ እስከሆነ ድረስ የተከፋፈሉ ሰዓታት ሊኖሩት ይገባል:-

ከጌታው የሚመሣጠርበት ሰዓት

እራሱን የሚገመግምበት ሰዓት

የአላህ ሥራዎችን በመመልከት ጊዜ ሰጥቶ የሚያስተነትንበት ሰዓት

ምግብና መጠጥን ለመሣሰሉ ጉዳዮች እራሱን የሚያገልበት ጊዜ።’

وعلى العاقل، ألا يكون ظاعنًا إلا لثلاث:

تزود لمعاد، أو لمعاش.

أو لذة فى غير محرم.

‘ብልህ ሰው ለሦስት ነገሮች ካልሆነ ትልቅ ትኩረት መስጠት የለበትም፡-

ለመመለሻው /ለአኺራው/ አለያም ለኑሮው /ለምድር ላይ ህይወቱ/ ለመሠነቅ

ሀራም ባልሆነ ነገር እራሱን ለማስደሠት።’

وعلى العاقل أن يكون بصيرًا بزمانه، مقبلاً على شأنه، حافظًا للسانه؛ ومن

حسب كلامه من عمله قل كلامه إلا فيما يعنيه

‘ብልህ ሰው ስላለበት ዘመን ሁኔታ በጥልቀት ማወቅ አለበት። የራሱንም ሁኔታ መገምገም ይኖርበታል። ከንግግሩና ከሥራው አንፃር ምላሱን ጠባቂና በሚያገባው ነገር ላይም ብቻ የሚናገር መሆን ይገባዋል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የሙሣ ፅሁፎችስ ምን የያዙ ነበሩ?’ እርሣቸውም ‘ሁሉም በጥበባዊ ምክሮች የተሞሉ ናቸው’ አሉ።

عجبت لمن أيقن بالموت، ثم هو يفرح.

‘ሞት እንዳለበት እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የሚደሰት ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن بالنار، ثم هو يضحك.

‘እሣት እውነት መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የሚስቅ ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن بالقدَر، ثم هو ينصب

‘ቀደር እውነት መሆኑን እያወቀ የሚደክመው ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن رأى الدنيا وتقلبها بأهلها، ثم اطمأن إليها.

‘ዱኒያንና በሰዎች የመቀየር ባህሪዋን እያስተዋለ በሷ የሚረጋ ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن الحساب غدًا، ثم لا يعمل.

‘ነገ ምርመራ ያለ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የማይሠራ ሰው ይገርመኛል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይምከሩኝ።’ አልኳቸው። እርሣቸውም፡-

أوصيتك بتقوى الله، فإنها رأسُ الأمر كله

‘አላህን በመፍራት ይሁንብህ አደራህን። እሱ የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ነውና።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይጨምሩኝ’ አልኳቸው።

عليك بتلاوة القرآن، وذكر الله ، فإنه نور لك فى الأرض، وذخر لك فى السماء

‘ቁርኣንን በማንበብና አላህን በማውሣት ይሁንብህ አደራህን። እሱ በምድር ላይ ብርሃን በሰማይ ቤትም ሀብት ይሆንሃል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ’ አልኳቸው።

إياك وكثرة الضحك، فإنه يميت القلب، ويذهب بنور الوجه

‘ሣቅ አታብዛ እሱ ቀልብን ይገድላል፣ የፊትን ብርሃን ይወስዳል።’

‘ይጨምሩኝ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!’።

عليك بالجهاد، فإنه رهبانية أمتى

‘በጅሃድ ላይ በርታ አደራህን፤ እሱ የህዝቦቼ ምንኩስና ነው።’

የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’ አልኳቸው።

أحبَّ المساكين وجالسهم

‘ድሆችን ውደድ ከነሱም ጋር ተቀማመጥ።’ አሉኝ

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

انظر إلى من هو تحتك، ولا تنظر إلى ما هو فوقك، فإنه أجدر أن لا تزدرى نعمة الله عنك

‘ከበታችህ ወዳለው ሰው ተመልከት። ከበላይህ ወዳለው አትመልከት። ይህም አላህ ባንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ይበልጥ እንድታስታውስ ያግዝሃልና።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

قل الحق وإن كان مُرًا

‘የቱን ያህል መራር ቢሆንም እንኳ እውነትን ከመናገር ወደኋላ አትበል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

ليردك عن الناس ما تعلمه من نفسك، ولا تجد عليهم فيما تـ أتى، وكفى بك عيبًا أن تعرف من الناس ما تجهله من نفسك، وتجد عليهم فيما تـ أتى

‘አንተ የማትሰራበት ስትሆን ስለራስህ የምታውቀው ነገር ስለሰው ከማውራት ይቆጥብህ። አንተ የምትሠራበት ስትሆን በራስህ ላይ ያላስተዋልከው ነገር በሰው ላይ ማየትህ ከነውር ይብቃህ።’ አሉኝ።

ከዚያም በእጃቸው ደረታቸውን መታ በማድረግ፡-

يا أبا ذر، لا عقل كالتدبير، ولا ورع كالكف، ولا حسب كحُسن الخُلُق

‘አባዘር ሆይ! እንደ ማስተንተን አዕምሮ የለም፤ እንደ መታቀብ ፍራቻ የለም፤ እንደ መልካም ሥነ-ምግባር ክብር የለም።’ አሉ።” (ኢብኑ ሂባንና ሀኪም ዘግበውታል)

 5. የተከበረው ቁርኣን የመጨረሻው ሰማያዊ መፅሃፍ ነው።

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

 

 

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ﴿٢﴾ نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ ﴿٣﴾ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَانَ ۗ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ ذُو انتِقَامٍ

አላህ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። (እርሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው። ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ። ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል። (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)። ፉርቃንንም አወረደ።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 2-4)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here