ጥያቄ፡- እባካችሁን አንዳንድ የመንግስት ወይም የግል ድርጅት ሰራተኞች -በተለይም ኃላፊዎች- ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያካብቱት ኃብት ላይ ያለው ሸሪዐዊ አቋም ምን እንደሆነ አስረዱን? መልስ፡- የህዝብ ኃብት ማለት -የፊቅህ ልሂቃን ዘንድ- ባለቤቱ ያልተለየ በሀገር ውስጥ የተገኘ የሀገሪቱ ህዝቦች ንብረት ነው። አል-ቃዲ አል-ማወርዲይና ቃዲ አቡ የዕላ እንዲህ ይላሉ፡- “የህዝብ ኃብት ማለት ባለቤቱ ውስን ያልሆነ ሁሉም የህዝብ የሆነ ኃብት ነው።” (አል-መውሱዐቱል-ፊቅሂያ፣ […]
ጥያቄ፡- ሶደቃን በሚስጥር መስጠት ይሻላል ወይስ በይፋ? መልስ፡- የመልካም ሥራዎች መዘውር ኢኽላስ ነው። መልካም ሥራ መልካም ነው የሚባለው ኢኽላስ ሲኖረው ነው። ስለዚህ ሰውየው ልታይ ባይነት (ሪያእ) ይፈጠርብኛል ብሎ ከፈራ በይፋ ከሚደረግ ምጽዋት በሚስጥር የሚደረገው የተሻለ ነው። የዐርሽ ጥላ እንጂ ሌላ ጥላ በሌለበት የትንሳዔ ቀን ከዐርሽ ጥላ ሥር ከሚሆኑት ሰባት ሰዎች መሀል “ምጽዋት ሲሰጥ ቀኙ የምትሰጠውን […]
ጥያቄ፡- ኒቃብ መልበስ ወይም ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው? ሸሪዐዊ ሒጃብን የማትለብስ ሴት ቅጣቷ ምንድን ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላትወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ቀዳሚው ጉዳያችን፡- የኒቃብ ብይን ምንድን ነው? ዑለሞች በሙሉ ለዓቅመ ሄዋን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ከፊትና ከመዳፏ በስተቀር መላ አካላቷን መሸፈን ግዴታዋ እንደሆነ ያምናሉ። በመሀላቸውም ልዩነት የለም። በማንኛውም መልኩ ሴት ፈታኝ አካሏን ማጋለጥ እንደማይፈቀድላትም ያምናሉ። […]
ጥያቄ፡- በየትምህርት ቤቱ፣ በየከተማው በሀገር ዐቀፍ ብሎም በኢንተርናሽናል ደረጃ ሳይቀር የሚሰናዱ የቁንጅና ውድድሮች በኢስላም እንዴት ይታያሉ? መልስ፡- እነዚህ ውድድሮች የመቆሸሽ እና የመበከል ምልክቶች ናቸው፡፡ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመት መሀይምነት መገለጫዎች ናቸው፡፡ የሴቶችን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ወራዳ ነገሮች ናቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ውድድሮች ላይ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው ኃጢያተኛ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ውድድሮች ላይ በመካፈል ነፍሷን ማዋረድ የመረጠች ሴትም […]
ጥያቄ፡- ሴት ስፖርት መስራት ትችላለች? መከተል ያለባት ወሳኝ መርሆችስ ምንድን ናቸው? መልስ፡- ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አካልን ለማጠንከርና ጤናን ለመጠበቅ ብሎ መከወን ወንድና ሴት የማይለያዩበት ጉዳይ ነው። የስፖርት ዓይነቱ ደግሞ ሸሪዓዊ ብይኑን ይወስናል። አካልን ለማጠንከር ወይም እንደ እግር ኳስ ያሉ አዝናኝ የሆኑ ስፖርቶችም ቢሆኑ ይፈቀዳሉ። እንደውም አንዳንዴ ግዴታ ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠርም ይችላል። ነገርግን በስፖርት እንቅስቃሴዎች ጊዜ ሃፍረተ […]
ጥያቄ:- በእሰልምና ዉስጥ የሒጃብ ድንጋጌ ምንድነው? መልስ:- ሒጃብ ለአካለመጠን በደረሠች ሙስሊም ሴት ላይ ሁሉ ግዴታ ነው። ይህም ሴት ልጅ ሐይድ የምታይበት ዕድሜ ነው። ድንጋጌውም በቁርኣን፣ በሐዲሥና በዑለሞች ስምምነት የፀና ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል:- “አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው።” […]
ጥያቄ፡- ኢስላም አሉባልታን ስለማሰራጨት ያለው አቋም ምንድን ነው? መልስ፡- ኢስላም እውነተኛ መሆንን ያሞግሳል፤ ውሸትን ያስጠነቅቃል። ከዐብዱላህ ቢን መስዑድ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- إِنَّ الصِّدْقَ يَهْدِي إِلَى الْبِرِّ، وَإِنَّ الْبِرَّ يَهْدِي إِلَى الْجَنَّةِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَصْدُقُ حَتَّى يُكْتَبَ صِدِّيقًا. وَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وَإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَكْذِبُ حَتَّى يُكْتَبَ كَذَّابًا […]
ጥያቄ፡- ነጋዴ ወይም ሻጭ የዕቃውን ጉድለት ለገዢው መግለፅ ግዴታ አለበት? ለገዢው ጉድለቱን ከተናገረ ግን ሊከስር ይችላልና ምን ያድርግ? መልስ፡- ሻጭ ለገዢው እቃው ላይ ያለውን ነውር የመበየን ግዴታ አለበት። ነውሩን መደበቅ ማታለል ነው። ማጭበርበር እና ማምታትም ነው። ይህ ደግሞ ያለጥርጥር ሐራም ነው። የኢብኑ ማጀህ “ሱነን” ላይ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- المسلم أخو المسلم لا […]
ጥያቄ፡- አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ። ባጠገቤ እጅግ ብዙ ጊዜ የሚያስነጥስ ባልደረባ አለኝ። በጣም በተከታታይ ያስነጥሳል። (የርሐሙከሏህ) ማለት አለብኝ? ወይስ አስነጥሶ ሲጨርስ ለሁሉም አንድ ጊዜ ልበለው? አመሰግናለሁ። መልስ፡- አንድ ሰው በሚያስነጥ ጊዜ “አልሐምዱሊላህ” ወይም “አል-ሐምዱሊላህ ዐላ ኩሊ ሐል” ወይም “አልሐምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን” ማለት ይወደድለታል። ይህ በሐዲስ የተዘገበ ነው። ዑለሞች በሙሉ ይህንን ማለት ተወዳጅ እንደሆነ ያምናሉ። አሏህን ሲያመሰግን […]
ጥያቄ፡- አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱሁ። የስፖርት ውድድሮች፣ ትምህርታዊ ውድድሮች፣ የጠቅላላ ዕውቀት ውድድሮች ሽልማት ሸሪዓዊ ብይን ምን እንደሆነ እንድታሳውቁኝ እፈልጋለሁ። በተጨማሪም የተለያዩ ካምፓኒዎች የሚያወጧቸው ሽልማት የሚያስገኙ ኩፖኖች እና ሎተሪዎች ይፈቀዳሉ? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም። አልሐምዱሊላሂ ረቢል-ዐለሚን። ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዓላ ረሱሊላህ ወበዕድ፡- የተለያዩ የውድድር ሽማቶች አሉ። ሁሉም ዓይነት ሽልማት የራሱ የሆነ ሸሪዓዊ ብይንም አለው። የሚከተሉት የተለመዱ የሽልማት ዓይነቶች ናቸው። አንደኛ፡- […]