Category: ጤናና ህክምና

Home የፈትዋ ገጽ
የስኳር በሽተኛን ማግባት

  ጥያቄ፡- በጠባይ፣ በዲናዊም ሆነ በማህበረሰባዊ መመዘኛዎች ብቁ የሆነ ሰው አጭቶኝ ነበር። ነገርግን ቤተሰቦቼ የስኳር በሽተኛ ስለሆነ ጋብቻውን ማገድ ይችላሉ? ሁለታችንም እንዋደዳለን፤ እንፈላለጋለን። ቤተሰብ በዚህ ዓይነት ምክንያት ጋብቻችንን ማገድ ይችላል? ቤተሰቦቼ እንዲስማሙስ እንዴት ላሳምን እችላለሁ? ምክራችሁን እሻለሁ። መልስ፡- የህክምና ባለሙያዎች የስኳር በሽታ የጋብቻ ህይወት ላይ እክል እንደማይፈጥር አስረድተዋል። ለጋብቻ ህይወት የሚያዳግት ለእይታ የሚያስጠላ በሽታ አይደለም። በንክኪና […]

የሴት ልጅን እንቁላል ማምረቻ ቱቦ ስለማሰር

ጥያቄ:– በስኳር በሽታ ምክንያት ማህፀኗ ስለተጎዳ ባለቤቴ የእርግዝና መከላከያ ክኒን እንዳትወስድ ተከልክላለች። ስለሆነም የባለቤቴን ማህፀን እንቁላል ማምረቻ እንዳያመርት በማሰር ማሳገዱ ይፈቀዳል ወይ? መልስ:- የእንቁላል ቱቦን ዳግም ፍሬ እንዳያፈራ አድርጎ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሰር በሸሪዓችን የተከለከለ ነው። የግድ መሆን ለሚገባው አሳማኝ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር። ክልከላው የተደረገው እስልምና የቆመለትን የሰውን ልጅ ዘር የማስቀጠል ዓላማ ስለሚፃረር ነው። በአንገብጋቢና […]

ሴቶች ስፖርት ሲሰሩ መከተል ያለባቸው ስርዐት

ጥያቄ፡- ሴት ስፖርት መስራት ትችላለች? መከተል ያለባት ወሳኝ መርሆችስ ምንድን ናቸው? መልስ፡- ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አካልን ለማጠንከርና ጤናን ለመጠበቅ ብሎ መከወን ወንድና ሴት የማይለያዩበት ጉዳይ ነው። የስፖርት ዓይነቱ ደግሞ ሸሪዓዊ ብይኑን ይወስናል። አካልን ለማጠንከር ወይም እንደ እግር ኳስ ያሉ አዝናኝ የሆኑ ስፖርቶችም ቢሆኑ ይፈቀዳሉ። እንደውም አንዳንዴ ግዴታ ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠርም ይችላል። ነገርግን በስፖርት እንቅስቃሴዎች ጊዜ ሃፍረተ […]

አስከሬንን ስለ መክፈት

ጥያቄ:- በህክምና የትምህርት ክፍል ተማሪ ነኝ። አልፎ አልፎ ባለቤት የሌላቸው አስከሬኖችን እናገኛለን። እነዚያን አስከሬኖች ከፍቶ ለመማርና ማስተማር መጠቀም ይፈቀዳል ወይ? መልስ:– ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- የሸሪዓ መርሆና መንፈሱ እንደሚያመለክተው አንድ ነገር ማድረግ ያለው ጥቅም ጎልቶ የወጣ እንደሆነ ይፈቀዳል። አስከሬንን መክፈትና መጠቀምም እንዲሁ ነው። ይህ መሆኑ በሐዲሥ ከተላለፈው “كسر عظم الميت ككسره حيا – የሟችን አጥንት መስበር […]

ጥርስን ስለማስተካከል

ጥያቄ:- ወጣት ነኝ። ጥርሴ ወደፊት ወጣ ወጣ ያለ ነው። በተለይ በምስቅበት ጊዜ ተቸግሬያለሁ። በዚህም የሥነልቦና ጉዳት እየደረሰብኝ ነው። በዚሁ የተነሳ አንዳንዴም ከመሳቅ የምቆጠብበት ሁኔታ አለ። ስለሆነም ጥርስን ማስተካከል በሸሪዓ እንዴት ይታያል? ክልክል ነው ወይንስ ይፈቀዳል? መልስ:- ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ አስዉቦ ነው የፈጠረው። እሱ ከፈጠረበት አፈጣጠሩም […]

ከ120 ቀናት በኋላ ጽንስን ስለማስወረድ

ጥያቄ፡- ካረገዝኩ ስድስት ወር ሆኖኛል። ጽንሱ ዕድገት የሚቀጥል ከሆነ ለሕይወቴ አስጊ መሆኑን ሐኪሞች ነግረውኛል። ይህንኑ የሚገልጽ የሐኪሞች ውሳኔ እንዲሠጠኝ አመልክቻለሁ። በዚህ ሁኔታ ላይ ጽንስን ማስወረድ አንዴት ይታያል? መልስ:- ሙስሊም ምሁራን እንደተስማሙበት አንድ ጽንስ በእናቱ ሆድ ዉስጥ የ120 ቀን ዕድሜ ከሞላው (ሕይወት የሚነፋበት የጊዜ ርዝመት ነው) ጽንስን ማስወረድ አይቻልም። በዚህ ሁኔታ ላይ ጽንስን ማስወረድ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ […]