ጥያቄ፡- ሱብሒን ስሰግድ ከፋቲሓ በኋላ ረዣዥም አንቀጾች እቀራለሁ። አንዳንዴ ግን እንቅልፍ ያስቸግረኛል። ቁርኣኑን እያነበብኩም አንጎላጃለሁ። ይህ እንዴት ይታያል? ቁርኣንን በማንበቤ የማገኘውን ምንዳ ያመክንብኝ ይሆን? መልስ፡- አዎን! ቁርኣን እየቀሩ ማንጎላጀት ምንዳው ላይ ተፅዕኖ አለው። ከባድ ማንጎላጀት ካስቸገረውና መቋቋም ካልቻለ ቂርኣቱን ማርዘም አይገባም። ምክንያቱ ንባቡ ላይ ይሳሳታል። ጣዕምም አይኖረውም። ማንጎላጀት ያስቸገረው ሰው ሶላቱን አያርዝመው። ያሳጥረው። ከፋቲሓ በኋላ አጭር […]
ጥያቄ፡- መእሙም ፋቲሓን ይቀራል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አልሐምዱሊላሂ ረብ-ቢል-ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊል-ላህ የፊቅህ ልሂቃን በዚህ ጉዳይ ላይ አራት ዓይነት ሃሳቦችን አንጸባርቀዋል፡- አንደኛው፡- ሐነፊዮች ዘንድ ድምጽ ከፍ ተደርጎም ሆነ ዝቅ ተደርጎ በሚሰገዱ ሶላቶች ላይ ተከታይ የሆነ ሰው ፋቲሐን ማንበቡ በጥብቅ የተጠላ ነው፡፡ ምክንያቱም በሐዲስ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- من كان له إمام فقراءة الإمام […]
ጥያቄ፡- የረመዳን ቀዷ እንዲሆንልኝ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ብጾም እና የሸዋልን የስድስቱን ቀናት ጾም አብሬ ብነይት ይበቃኛል? የስድስቱን ቀን የሸዋል ሱና ምንዳ አገኛለሁ? መልስ፡- የሚሻለው ሁለቱን ኒያዎች መለያየት ነው። ለቀዳእ የሚጾመው ጾም ለብቻው ይነየት። የስድስቱ የሸዋል ቀናት ጾምም ለብቻው ይነየት። አንዳንድ ዑለሞች በአንድ ላይ ሁለቱንም መነየት ይከለክላሉ። ሁለቱን በአንድ ላይ መሰብሰብ ከፈለገ -ለምሳሌ፡- ቀዳ በማውጣት ተጠምዶ […]
ጥያቄ፡- ተራዊሕ መስገድ ከዒሻእ በዕዲያ ያብቃቃል። ተራዊሕ እርሱን የማይተካው ከሆነ ይች ሱና ሶላት መቼ ትሰገድ? የተራዊሕ ሶላት የወቅት መጀመሪያ እና መጨረሻ መቼ ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላትወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ከዒሻእ ሶላት በፊት ተራዊሕን መስገድ አይቻልም። የተራዊሕ ሶላት -ያለ ምንም የዑለሞች ልዩነት- ተቀባይነት የሚያገኘው ከዒሻእ ሶላት በኋላ ነው። የዒሻእን በዕዲያ ከሰገዱ በኋላ መሆኑ ደግሞ እጅግ […]
ጥያቄ፡- በረመዳን ፊልሞችን መመልከት እና ዘፈን መስማት ብይኑ ምንድን ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም። አልሐምዱሊላሂ ረቢል-ዐለሚን። ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዓላ ረሱሊላህ ወበዕድ፡- በጥቅሉ ፊልምና ቲያትሮችን መመልከትና ዘፈንን መስማት ብይን በነዚህ መስፈርቶች ይቃኛል፡- የሚታዩና የሚደመጡ የ “ጥበብ” ውጤቶች የተበከለ ንግግር ካዘሉ፣ ወደ ሐራም ከተጣሩ፣ አስተሳሰብና ጠባይ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ካላቸው፣ ከግዴታዎች ካዘናጉ ወይም እርም የሆነ ነገር ከተቆራኛቸው -ለምሳሌ፡- አልኮል […]
ጥያቄ፡- ጥርስን ማፅዳት በሸሪዐው በጥብቅ የታዘዘ መሆኑ ይታወቃል። ነገርግን ይህ ሸሪዐዊ ትዕዛዝ የጾመኛን የአፍ ጠረን ከሚያሞግሰው ሐዲስ ጋር አይጋጭም? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም። አልሐምዱሊላሂ ረቢል-ዐለሚን። ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዓላ ረሱሊላህ ወበዕድ፡- ቡኻሪይ እና ሙስሊም ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ የሚል ንግግር ዘግበዋል፡- والذي نفس محمد بيده لخلوف فم الصائم أطيبُ عند الله من ريح المسك “የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ […]
ጥያቄ፡- ከዱዐ በኋላ ፊትን በእጆች መዳበስ እንዴት ይታያል? መልስ፡- ዱአዕ ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ታላላቅ ስራዎች መካከል አንዱ ነው። አላህን እጅግ መፈለግና እርሱን መከጀል የሚታይበት ተግባር ነው። ሰውየው የራሱን ድህነትና የአላህን ሀብታምነት የሚያውጅበትም ድርጊት ነው። የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) አምልኮ (ዒባዳ) ብለው ሰይመውታል። አቡ ዳዉድ፣ ቲርሙዚይ (ሶሒሕ አድርገውት)፣ አሕመድ፣ ኢብኑ ሒባን፣ አል-ሐኪም (ሶሒሕ አድርገውት) ከኑዕማን ቢን በሺር እንደዘገቡት […]
ጥያቄ:- በተሸሁድ ጊዜ ጣቶችን ማነቃነቅ እንዴት ይታያል? ቢድዐ ነው ወይስ ሱና? መልስ፡- የፊቅህ ልሂቃን – በጥቅሉ – በተሸሁድ ወቅት ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለውን ጠቋሚ ጣት ከፍ ማድረግ ሱና እንደሆነ ይስማማሉ። መልዕክቱም የአላህን አንድነት፣ ኢኽላስን ያመላክታል። ነገርግን ጣት እንዴት ከፍ እንደሚደረግ የዑለሞች ልዩነት አለ። ነገርግን ልዩነቶቻቸው የቱ ነው የተሻለው በሚል ሃሳብ ዙርያ እንጂ የመፈቀድ እና ያለመፈቀድ […]
ጥያቄ:- ያለ ኢማም እና ያለ ኸጢብ/ኹጥባ አድራጊ ራዲዮ አዳምጠን አስከትለን ጁሙዐን መስገድ እንችላለን? መልስ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ):- صلوا كما رأيتموني أصلي “ስሰግድ እንዳያችሁት አድርጋችሁ ስገዱ።” ይላሉ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ ጁሙዐን በስብስብና በህብረት እንጂ አልሰገዱም። “ሁለት ኹጥባ ከሶላት በፊት ያደርጉም ነበረ። ሁለቱን ኹጥባዎች ደግሞ በመሀል በመቀመጥ ይለዯቸዋል።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ለዚህ ነው ዑለሞቹ በአንድነት/በኢጅማዕ “ጁሙዐ በህብረት […]
ጥያቄ፡- እንደሚታወቀው ከቦታ ጥበት የተነሳ መስጂዶቻችን ፎቅ እየሆኑ ነው። እናም የሰፈራችን መስጂድ ባለ ሦስት ፎቅ ተደርጎ ተሰርቷል። ሚሕራብና ሚንበር የተሰራው ደግሞ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው። ስለዚህ ኢማማችን ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው የሚሰግዱት። ምክንያቱም ሁለተኛው ፎቅ ከሌሎቹ ይሰፋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው? ሁለተኛው ፎቅ ላይ ያለው ሚሕራብ ፈርሶ ወደ አንደኛው ፍሎር መምጣቱ ግዴታ ይሆናል? እንዳለ ቢተውስ ሶላታችን […]