ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል? መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው። የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡- ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው […]
ጥያቄ፡- የኔ ጥያቄ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎች ላይ ለምሣሌ ከእግር ላይ እና ብብት ሥር የሚገኘውን ፀጉር መላጨትን ይመለከታል። እነኚህ የሰውነት ክፍሎች በአደባባይ የማይታዩ መሆናቸው ይታወቃል። ነገርግን ቢስተካከሉ ባልንም ሆነ ሴቷን ያስደስታሉ። እስልምና በዚህ ዙሪያ ምን ይላል? መልስ፡- በበርካታ የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ሀዲሦች እንደተገለፀው ለሴት ልጅም ሆነ ለወንድ ልጅ ብብት ሥር እና ብልት አካባቢ የሚገኝን ፀጉር […]
ጥያቄ፡- ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷን በሚመጣበት ጊዜም አይፆሙም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ? አንድ ሰው እንደነገረኝ ከሆነ ወላጆቼ አላህን እስካልታዘዙ ድረስ እኔም ለነሱ መታዘዝ እንደሌለብኝ ነው። ይህ በርግጥም ትክክል ነውን? እባክዎ ምክርዎን ይለግሱኝ መልስ፡- አላህ ቤተሰቦችህን ወደ ቀጥተኛ መንገድ እንዲመራቸው እንለምነዋለን። አንተም ለነሱ ዱዓእ ማድረግ ይኖርብሃል። ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎችን ለነሱ ክብርና ትህትናን በተላበሠ መልኩ አስታውሳቸው። ለወላጆችህ በመታዘዙ ጉዳይ ላይ […]
ጥያቄ፡- ኢስላም አሉባልታን ስለማሰራጨት ያለው አቋም ምንድን ነው? መልስ፡- ኢስላም እውነተኛ መሆንን ያሞግሳል፤ ውሸትን ያስጠነቅቃል። ከዐብዱላህ ቢን መስዑድ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- إِنَّ الصِّدْقَ يَهْدِي إِلَى الْبِرِّ، وَإِنَّ الْبِرَّ يَهْدِي إِلَى الْجَنَّةِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَصْدُقُ حَتَّى يُكْتَبَ صِدِّيقًا. وَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وَإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَكْذِبُ حَتَّى يُكْتَبَ كَذَّابًا […]
ጥያቄ፡- እድገቴና ቤተሰቤ በመልካም የዲን መንገድ ላይ ቢሆንም ሰይጣን አሳስቶኝ ነፍሴን በደልኩ። በአንድ አጋጣሚ ላይ ለእረፍትና ለመዝናናት ከትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ከአዲስ አበባ እርቀን ወደ ሶደሬ ሄደን ነበር። እናም በዚሁ አጋጣሚ በጓደኞቼ ግፊት እርኩሱን ኸምር (አልኮል) ጠጣሁ። ዝሙትም ፈጸምኩ። አሁን ግን ሆኜ ሳስብ ለአንድ ቀን ከንቱ ይሉኝታና እርካታ የፈፀምኩት ወንጀል እንደ እግር እሳት ይለበልበኛል። ኸምር […]