ጥያቄ:- በእርግዝና ወራትም ሆነ በሌላ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ከሴት ልጅ ማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ብይኑ ምንድነው? ነጃሳ ነውን? ዉዱእ ማድረግን ያስገድዳልን? መልስ:- ሴት ልጅ በንጽሕና ጊዜያት አሊያም በእርግዝና ወቅት ልጅ በሚወጣበት በኩል የሚፈሳት ፈሳሽ ጠሃራ (ንፁህ) ነው። ደም የተቀላቀለበት ካልሆነ በስተቀር። ዉዱእ ያበላሻል የሚል ማስረጃም የለም። በሽንት መውጫ በኩል የሚወጣው ፈሳሽ ግን ከሽንት መጣራቀሚያ ፊኛ ጋር […]
ጥያቄ፡- አንድ ሰው በሙሉ ሰውነቱ ላይ ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን? ወይራ ዘይቱ ከተቀባ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተመጦ ይጠፋል። ታዲያ የተቀባው ሰው ዘይቱን በሣሙና መታጠብ ይኖርበታል ወይ? መልስ፡- ቀለል ያለ ዘይት ተቀብተን ከሆነ ውዱእ ከማድረጋችን በፊት ዘይቱን አሊያም የቆዳ ቅባቱን በሣሙና ለማስወገድ መጨናነቅ አያስፈልግም። አንድ ሰው ማረጋገጥ ያለበት ነገር ቢኖር ውሃው […]
ጥያቄ፡- ሆዴ በጋዝ የተሞላ ነው። ከሆዴ የሚወጡ ጋዞች አይቋረጡም። በዚህ ችግር እጅግ በጣም እየተሰቃየሁ ነው። ሶላት መስገድም ያስቸግረኛል። ፈሴ ያለማቋረጥ ከሆዴ ስለሚወጣ ዉዱእ አይቆይልኝም። ፈፅሞ ዉዱእ ማቆየት አልችልም። ስለዚህ ምን ማድረግ አለብኝ? መልስ፡- በቅድሚያ አላህ ጤና እንዲሰጥህ እንለምናለን። ሶላት ያለዉዱእ ውድቅ እንደሆነ የታወቀ ነው። አካልን ከነጃሳ ንፁህ ማድረግና ዉዱእ ማድረግ የሶላት መስፈርት ነው። ከሁለቱ የተለመዱ መንገዶች […]
ጥያቄ፡- ባለቤቴ ከአንድ ወር ከግማሽ በፊት በተፈጥሯዊው መንገድ ወልዳ ነበር። ከወለደች በኋላ ግን ለሦስት ወራት ያህል የሚያገለግል የእርግዝና መከላከያ መርፌ ወስዳለች። ችግሩ ግን የኒፋስ ደም ላይ ነበረችና ደሙ መፍሰሱን አላቋረጠም። ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ መውለዷ ታሳቢ ይደረግ። ያኔ ደም ወዲያው ነበር የቆመላት። ጥያቄዬ ምንድን መሰላችሁ፡ በወሰደችው መርፌ ምክንያት ነው ደሙ ያላቋረጠው? አርባ ቀኗ አልፏልና ምንድን […]
ጥያቄ፡- ሰላት በወር አበባ ላይ ላለች ሴት የማይፈቀድ መሆኑን አውቃለሁ። ዱዓእ ማድረግስ ይፈቀዳል ወይ? መልስ፡– በወር አበባ (ሀይድ) ላይ ያለች ሴት ልጅ ዱዓ ብታደርግ ክልክልነት የለውም። በርግጥ ሰላት መስገድም ሆነ ፆም መፆም አይፈቀድላትም። ነገር ግን ዚክር እና ዱኣ ማድረግ ትችላለች።