Category: ገንዘብ ነክ

Home የፈትዋ ገጽ
ስልጣንን አስታኮ የህዝብን ኃብት ለግል ጥቅም ማዋል

ጥያቄ፡- እባካችሁን አንዳንድ የመንግስት ወይም የግል ድርጅት ሰራተኞች -በተለይም ኃላፊዎች- ስልጣናቸውን በመጠቀም የሚያካብቱት ኃብት ላይ ያለው ሸሪዐዊ አቋም ምን እንደሆነ አስረዱን? መልስ፡- የህዝብ ኃብት ማለት -የፊቅህ ልሂቃን ዘንድ- ባለቤቱ ያልተለየ በሀገር ውስጥ የተገኘ የሀገሪቱ ህዝቦች ንብረት ነው። አል-ቃዲ አል-ማወርዲይና ቃዲ አቡ የዕላ እንዲህ ይላሉ፡- “የህዝብ ኃብት ማለት ባለቤቱ ውስን ያልሆነ ሁሉም የህዝብ የሆነ ኃብት ነው።” (አል-መውሱዐቱል-ፊቅሂያ፣ […]

በወረቀት ብር ላይ ሪባ (ወለድ/ አራጣ) አለ?

ጥያቄ፡- አበዳሪ ከተበዳሪ የሚያገኘውን ኢንተረስት ወይም ወለድን አስመልክቶ አንዳንድ ውዝግቦች ይነሳሉ። አንድ ሰው አንድ ሺህ ብር ያበድርና በውል በታወቀው ጊዜ ላይ ሲመልስ አንድ ሺህ አንድ መቶ ወይም አንድ ሺህ ሁለት መቶ አድርጎ ለአበዳሪው ይመልሳል። ውሉ የተካሄደው ደግሞ በወረቀት ገንዘብ ነው። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ ውል ሪባ/አራጣ እንዳልሆነ ያምናሉ። በወርቅና በብር (ሲልቨር) እስካልሆነ አራጣ/ሪባ የለም ባዮች ናቸው። እነዚህ […]

ከሐራም የተገኘ የውርስ ገንዘብ

ጥያቄ፡- ወላጃችን መሬቶች እና የመኖሪያና የንግድ ቤቶች አውርሶን ሞቷል። ነገርግን በወለድ ይሰራ ነበር። ጉቦም ይቀበል ነበር። ከርሱ ያገኘነው ውርስ ለኛ ይፈቀድልናል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላረሱሊላህ ኢማም አል-ገዛሊይ “ኢሕያእ ዑሉሚዲን” የተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፡- “ሰውየው ከወረሰው ሰው ያገኘው ገንዘብ ከሐራም ወይም ከሐላል እንደመጣ የማያውቅ ከሆነ፣ ከሐራም የሆነውን እና ከሐላል የሆነውን የሚለይበት ምልክት […]