በቀብር ወቅት ዱዐ ማድረግ
ጥያቄ:- የሞተን ሰው የሚሸኙ ሰዎች ምን ያድርጉ? ድምፃችንን ከፍ አድርገን በህብረት ለሞተ ሰው ዱዐ ማድረግ እንችላለን? መልስ:- ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- ከቀብር ስነስርዐት በኋላ ሸኚዎቹ በቀብሩ ላይ ቆይተው ለሟቹ ዱዐ ማድረግ ይወደድላቸዋል። ምክንያቱም አቡዳዉድና ሐኪም- በሶሒሕ ሰነድ- ከዑስማን ይዘው እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞተን ሰው ቀብረው ካገባደዱ በኋላ ቀብሩ ላይ በመቆም እንዲህ ይሉ ነበር:- استغفروا […]
የጀናዛ ሶላትን ለማስገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው
ጥያቄ:- የጀናዛ ሶላትን ለማሰገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው ማነው? የመስጂዱ ኢማም ወይስ የሟቹ የቅርብ ዘመድ? መልስ፡- ዑለሞች በሟች ላይ ሶላት ለማሰገድ እጅግ ተገቢው ሰው የትኛው ነው በሚለው ቅደም ተከተል ላይ ወጥ አቋም መያዝ አልቻሉም። ከፊሎቹ ጭቅጭቅና ዉዝግብን ለማስወገድ ሲባል ሥልጣኑ ያለው- ማለትም የሥልጣን ባለቤት የሆነው ክፍል እንዲያሰግድ፣ ኹጥባ እንዲያደርግና ለሌላም ነገር የወከለው መደነኛ ኢማም ነው ተገቢው […]