Category: ቤተሰብ

Home የፈትዋ ገጽ
ልጆችን በሷሊሖች ስም መጥራት ምን ጥቅም ያስገኛል?

ጥያቄ፡- …ከዘመዶቼ ጋር ተሰብስበን እየተጨዋወትን እያለን አዲስ ለተወለደው ልጄ ሥም ስለማውጣት መወያየት ጀመርን። በዚህ መሀል በአንቢያዎች ወይም በሶሐቦች ስም በመጠራት ዙርያ ክርክር ጀመርን። አንዷ ሙሐመድ ወይም ዘከሪያ የሚባሉ ስሞችን እንደማትወድ ተናገረች! “ያረጁ ሥሞች ናቸው” ስትል ምክንያቷንም አስረዳች። የአላህን መልእክተኛ- ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ)- እንደምትወድና እንደምታፈቅር ግን አስረግጣ ተናገረች። ሥሙ ግን ዘመናዊ አይደለም። ስለዚህ ዘመናዊ ሥም እመርጣለሁ አለች። […]

ኒቃብ ግዴታ ነው?

ጥያቄ፡- ኒቃብ መልበስ ወይም ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው? ሸሪዐዊ ሒጃብን የማትለብስ ሴት ቅጣቷ ምንድን ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላትወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ቀዳሚው ጉዳያችን፡- የኒቃብ ብይን ምንድን ነው? ዑለሞች በሙሉ ለዓቅመ ሄዋን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ከፊትና ከመዳፏ በስተቀር መላ አካላቷን መሸፈን ግዴታዋ እንደሆነ ያምናሉ። በመሀላቸውም ልዩነት የለም። በማንኛውም መልኩ ሴት ፈታኝ አካሏን ማጋለጥ እንደማይፈቀድላትም ያምናሉ። […]

የቁንጅና ውድድር እና የሴቶች መብት

ጥያቄ፡- በየትምህርት ቤቱ፣ በየከተማው በሀገር ዐቀፍ ብሎም በኢንተርናሽናል ደረጃ ሳይቀር የሚሰናዱ የቁንጅና ውድድሮች በኢስላም እንዴት ይታያሉ? መልስ፡- እነዚህ ውድድሮች የመቆሸሽ እና የመበከል ምልክቶች ናቸው፡፡ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመት መሀይምነት መገለጫዎች ናቸው፡፡ የሴቶችን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ወራዳ ነገሮች ናቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ውድድሮች ላይ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው ኃጢያተኛ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ውድድሮች ላይ በመካፈል ነፍሷን ማዋረድ የመረጠች ሴትም […]

ባሏ የሞተባት ሴት በ “ዒድ-ዳ” ጊዜዋ ላይ የምትከተለው የአለባበስ እና የጌጥ ስርዐት

ጥያቄ፡- ባሏ የሞተባት ሴት በ“ዒድ-ዳ” ጊዜዋ ላይ የምትከተለው የአለባበስ እና የጌጥ ስርዐት ምንድን ነው? በዒድ ቀንስ የተለየ ብይን ይሰጥ ይሆናል? መልስ፡- ባሏ የሞተባት ሴት በዒድ-ዳ ጊዜዋ ላይ (አራት ወር ከአስር ቀን) እያለች ለጌጥ የሚሆኑ አልባሳትን ትከለከላለች። ያለምክንያት ከቤት መውጣትም ትከለከላለች። ነገርግን የተለየ ጌጥነት የሌለውን ጥሩ ልብስ ግን መልበስ ትችላለች። የአካሏን ንፅህናም ትጠብቃለች። ፀጉሯን ልታፀዳና ልታበጃጅ፣ […]

ከሐራም የተገኘ የውርስ ገንዘብ

ጥያቄ፡- ወላጃችን መሬቶች እና የመኖሪያና የንግድ ቤቶች አውርሶን ሞቷል። ነገርግን በወለድ ይሰራ ነበር። ጉቦም ይቀበል ነበር። ከርሱ ያገኘነው ውርስ ለኛ ይፈቀድልናል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላረሱሊላህ ኢማም አል-ገዛሊይ “ኢሕያእ ዑሉሚዲን” የተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፡- “ሰውየው ከወረሰው ሰው ያገኘው ገንዘብ ከሐራም ወይም ከሐላል እንደመጣ የማያውቅ ከሆነ፣ ከሐራም የሆነውን እና ከሐላል የሆነውን የሚለይበት ምልክት […]

የልጅ ልጆችን በስጦታ እኩል ማድረግ

ጥያቄ፡- አባቴ መኪና አለው። እናም መኪና ስላልነበረኝ ለአራት አመታት ለኔ ትቶልኝ እጠቀምበት ነበር። ከስድስት ወር በፊት አላህ ልጅ ሰጠኝና በአባቴ ስም ሰየምኩት። አባቴም መኪናው ለልጄ ስጦታ እንዲሆን መወሰኑን ተናገረ። ጥያቄዬ ምን መሰላችሁ? እኔ አምስት ወንድሞች አሉኝ። ሦስቱ ከኔ በፊት አግብተዋል። ሁሉም ልጆች ወልደዋል፤ አልሐምዱሊላህ። ልጆቻቸውንም በአባቴ ስም ነው የጠሯቸው። ነገርግን አባቴ ለማናቸውም ስጦታ አልሰጠም። ይህ […]

የስኳር በሽተኛን ማግባት

  ጥያቄ፡- በጠባይ፣ በዲናዊም ሆነ በማህበረሰባዊ መመዘኛዎች ብቁ የሆነ ሰው አጭቶኝ ነበር። ነገርግን ቤተሰቦቼ የስኳር በሽተኛ ስለሆነ ጋብቻውን ማገድ ይችላሉ? ሁለታችንም እንዋደዳለን፤ እንፈላለጋለን። ቤተሰብ በዚህ ዓይነት ምክንያት ጋብቻችንን ማገድ ይችላል? ቤተሰቦቼ እንዲስማሙስ እንዴት ላሳምን እችላለሁ? ምክራችሁን እሻለሁ። መልስ፡- የህክምና ባለሙያዎች የስኳር በሽታ የጋብቻ ህይወት ላይ እክል እንደማይፈጥር አስረድተዋል። ለጋብቻ ህይወት የሚያዳግት ለእይታ የሚያስጠላ በሽታ አይደለም። በንክኪና […]

ሒጃብ የማትለብስ ሴት ሶላትና ጾም ቀቡል ይሆናል?

ጥያቄ፡- ሒጃብ ለባሽ አይደለሁም። አላህ ይቅር እንዲለኝና ሒጃብን እንዲያገራልኝ ዱዓ አድርጉልኝ። አሁን መጠየቅ የፈለኩት ሶላቴንና ጾሜን አላህ ይቀበለኝ ይሆን? መልስ፡- ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- የሙስሊም ሴት የአለባበስ ስርዐት አላህ የደነገገው ግዴታ ነው።  አላህ እንድትሸፍነው ያዘዛትን አካሏን ከባዳ ወንዶች መሸፈን አለባት።  ሸሪዐው የደነገገው የሴት አለባበስ – ከፊትና ከእጅ ውጪ- መላ አካሏን የሚሸፍን ልብስ ነው። ቅርፅና […]

ዐቂቃ ጥቅሙ አስፈላጊነቱና አደራረጉ እንዴት ነው?

ጥያቄ፡- የዐቂቃ ጥቅሙ ምንድነው? የዝግጅቱ አስፈላጊነትስ ምን ያህል ነው? ትክክለኛ አደራረጉስ በምን መልኩ ነው? መልስ፡- “ዐቂቃ” ማለት ጥሬ ትርጉሙ “እራስ ላይ የሚገኝ የፊት ፀጉር” ማለት ነው። ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚታረድ እንሠሣም ዐቂቃ ይባላል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ “ኑሱኪያ” ወይንም “ዘቢሃ” (እርድ) ይሉታል። የዐቂቃ ዓላማው ለአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ምስጋና ለማድረስ ነው። ይህም አንድ ሰው ልጅ ስለተወለደለት ደስታውን […]

ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷንን አይፆም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ?

ጥያቄ፡- ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷን በሚመጣበት ጊዜም አይፆሙም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ? አንድ ሰው እንደነገረኝ ከሆነ ወላጆቼ አላህን እስካልታዘዙ ድረስ እኔም ለነሱ መታዘዝ እንደሌለብኝ ነው። ይህ በርግጥም ትክክል ነውን? እባክዎ ምክርዎን ይለግሱኝ መልስ፡- አላህ ቤተሰቦችህን ወደ ቀጥተኛ መንገድ እንዲመራቸው እንለምነዋለን። አንተም ለነሱ ዱዓእ ማድረግ ይኖርብሃል። ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎችን ለነሱ ክብርና ትህትናን በተላበሠ መልኩ አስታውሳቸው። ለወላጆችህ በመታዘዙ ጉዳይ ላይ […]