Category: ሐጅና ዑምራ

Home የፈትዋ ገጽ
ከዘዋል (ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት) ጠጠር ስለመወርወር

ጥያቄ፡- የሐጅ ስነስርዐት ላይ- በተለይም ጠጠር በሚወረወርበት ወቅት ከፍተኛ ግፊያ እናስተውላለን። የተሸሪቅ ቀናት ላይ ጠጠርን ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት ጠጠር መወርወር እንችላለን? መልስ፡- የዙልሒጃ ወር አስራ አንደኛው፣ አስራ ሁለተኛው እና አስራ ሶስተኛው ቀን ወይም የተሸሪቅ ቀናት ተብለው በሚጠሩት ቀናት ላይ ጠጠር መወርወር የሚገባው ፀሀይ ወደ ምዕራብ ካጋደለች በኋላ ነው። ነገርግን አንዳንድ ዑለሞች ከፍተኛ ግፊያ የሚፈጠር […]

ኢሕራም ላይ ያለ ሰው ቀበቶ መታጠቅ ይችላል?

ጥያቄ፡- ገንዘብ እና ልዩልዩ መረጃዎቼን ለመያዝ እንዲመቸኝ የተሰፋ ቀበቶ መታጠቅ እችላለሁ? መልስ፡- ብዙ ሰዎች ኢሕራም ላይ ያለ ሰው የተሰፋ ልብስን በምንም መልኩ መልበስ እንደማይችል ያስባሉ። ነገርግን ጉዳዩ እንዲህ በጥቅሉ ሳይሆን ማብራሪያ ይፈልጋል። ኢሕራም ውስጥ ባለ ሰው ላይ እርም የሚሆነው ልብስ በአካላት ልክ የተሰፋ- እንደ ሱሪና እና እንደ ቀሚስ ያለ ልብስ- ነው። ክር የነካውን ልብስ ሁሉ እርም […]

ሐጅ ላይ ያለ ሰው በምን አይነት ስራ ይጠመድ?

ጥያቄ፡- በሐጅ ጊዜ ውስጥ ሐጀኛ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ስራዎች ምንድን ናቸው? መልስ፡- ታላቁ ዐሊም ዶክተር ዩሱፍ አል-ቀረዳዊ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡- “ሐጀኛ በሐጅ ጊዜው አላህን በማውሳት-በዚክር-፣ በዒባዳ፣ የአላህን ትዕዛዛት በመከወን እና ወደ አላህ የሚያቃርቡ በሆኑ በጎ ሥራዎች-በሶደቃ፣ ደካሞችን በማገዝ፣ እውቀት የሌላቸውን በማስተማር…- ራሱን መጥመድ ነው ያለበት። ባገኘው አጋጣሚ አብዝቶ ቁርኣንን ማንበብ ይወደድለታል። በቻለው አቅም ታላቁ መስጂድ (መስጂዱል-ሐረም) […]

የሴቶች ኢሕራም ፊትን መግለጥ የሆነበት ብይን እና ጥበብ

ጥያቄ፡- ኢሕራም ላይ ያለች ሴት ፊቷን መሸፈን ወይም ኒቃብ መልበስ እርም ይሆንባታል? ፊቷን ብትሸፍን ኃጢያተኛ ትሆናለች ማለት ነው? ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ሴት ኢሕራም ላይ ፊቷን እንድትገልጥ የታዘዘበት ጥበብ ምንድን ነው? መልስ፡- አብዝሃኞቹ ዑለሞች በኢሕራም ወቅት ሴት ፊቷን መሸፈን እርም እንደሚሆንባት ያምናሉ። ስለዚህ ኒቃብም ሆነ ጓንት አትለብስም። ምክንያቱም የሴት የኢሕራም መገለጫ ፊቷን መክፈቷ ነው። የሐዲስ ኢማሞቹ ቡኻሪይ፣ […]

ሐጅ ላይ ሁለት ኒያዎችን መሰብሰብ

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ጾም ሱና የሆነበትን ቀን ከአንድ በላይ በሆነ ኒያ ከጾመው ምንዳው በኒያው ልክ እንደሆነ አውቃለሁ። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ኢነመል አዕማሉ ቢኒያ” (ስራ ሁሉ የሚለካው በኒያ ነው) ብለዋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው፡- ሰውየው ግዴታ የሆነበትን ሐጅ በሑለት ኒያዎች መፈፀም ይችላል? ለምሳሌ አንዲትን ሐጅ ለራሱ እና ለአንድ ወላጁ ሊነይትባት ይችላል? አላህ ይስጥልኝ! መልስ፡- የአንድ ሰው ጫንቃ- […]

ሀጃጆች ኢሕራም የሚያደርጉበት ቦታ

ጥያቄ፡- መካ ወይም መዲና ውስጥ ለሐጅ የተወሰነ የኢሕራም ቦታ አለ? ካለ የት ነው? መልስ፡- ሐጅ ወይም ዑምራ ማድረግ የሚሻ ሰው ኢሕራም የሚያደርግበት ቦታን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የገደቡት ቦታ አለ። ሐጅ ወይም ዑምራ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ሊያልፋቸው የማይገቡ የኢሕራም ስፍራዎችን (ሚቃትን) ወስነው ገልፀዋል። ሰውየው እነዚህን ስፍራዎች ከማለፉ በፊት ኢሕራም ማድረግ እንዳለበትም አሳውቀዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለመዲና […]

ሴት የሐጅ ስራዎችን እንዲከውንላት ሌላን ሰው መወከል ትችላለች?

ጥያቄ፡- በዚህ አመት- አላህ ካለ- እናቴን ይዤ ሐጅ አደርጋለሁ። እናቴ እድሜዋ ትልቅ ነው። አርጅታለች። ህመምተኛና ደካማ ሴት ናት። ስለዚህ እናቴን ተክቼ መስራት የምችላቸው የሐጅ ስራዎች የትኞቹ ናቸው? መልስ፡- ጠጠር መወርወር እና እርድ ማከናወን ላይ እናትህን መተካት ትችላለህ። ከዚህ ውጪ ያሉት የሐጅ ስራዎች ላይ ግን እናትህ በራሳቸው መፈጸም አለባቸው እንጂ ልትወከላቸው አትችልም። ክብርት እናትህ በመኪና ተሳፍረው ወደ […]

በኢሕራም ውስጥ የተከለከሉ ነገሮችን መፈፀምና ቅጣቱ

ጥያቄ፡ በኢሕራም ወቅት ክልክል የሆኑ ነገሮችን መፈፀም ብይኑ ምንድን ነው? ጥፋቱን የፈፀመ ሰውስ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? መልስ፡- በኢሕራም ወቅት እርም የሆኑ ነገሮችን የፈፀመ ሰው የሚቀጣው ቅጣት እንደፈፀመው ነገር ይለያያል። ዐረፋ ላይ ከመቆሙ በፊት ወሲብ ፈፅሞ ከሆነ ሐጁ ይበላሽበታል። በሚመጣው ዓመት ቀዷ ከማውጣት ጋር ግመል ማረድ ግዴታ ይሆንበታል። አብዝሃኞቹ ዑለሞች ዘንድ ዐረፋ ላይ ከቆመ በኋላ ቢሆንም ቅጣቱ […]

ካዕባ አጠገብ ያለው የሰይዲና ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) መቃም ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ ያለው የእግር አሻራ

ጥያቄ፡- መቃሙ ኢብራሂም (የኢብራሂም የመቆሚያ ስፍራ) ተብሎ የሚጠራው ቦታ ላይ ያለው የእግር አሻራ የራሳቸው የኢብራሂም የእግር አሻራ ነው? መልስ፡- መቃሙ ኢብራሂም የሚባለው ስፍራ የጥንታዊው ቤተ-መለኮት (አል-በይቱል-ዐቲቅ) መሰረት ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ አላህ እስካሁን ጠብቆ ያቆየው የኢስላም ቅርስ ነው። ቦታው ውዱ የአላህ ነብይ- ኢብራሂም- ካዕባን ሲገነቡ የቆሙበት ድንጋይ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- “ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል። […]

የሐጅ መጓጓዣ እና የእንግልቱ ምንዳ

ጥያቄ፡- ወደ ሐጅ በአውሮፕላን መሄድ ይሻላል ወይስ በመኪና ወይም በእግር? በእግራችን ስለመጣን የሚከፈለን ምንዳ ከሌላው ይበልጣል ብለው የሚያስቡ ከፓኪስታን በእግራቸው የመጡ ሰዎች አጋጥመውኝ ነው። ሃሳባቸው ትክክል ነው? መልስ፡- በዒባዳ የሚገኝ ምንዳ በእንግልት ላይ ብቻ የተመሠተ አይደለም። ታሳቢ መሆን ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ቀደምት መስፈርቶች ተደርገው የሚታዩ ብዙ ነገሮች አሉ። ዋናው ኢኽላስ ነው፤ ስራን ጥርት አድርጎ ለአላህ […]