ፎቅ ላይ ሆኖ ኢማምን መከተል ይቻላል?

Home የፈትዋ ገጽ ሰላት ፎቅ ላይ ሆኖ ኢማምን መከተል ይቻላል?

ጥያቄ፡- እንደሚታወቀው ከቦታ ጥበት የተነሳ መስጂዶቻችን ፎቅ እየሆኑ ነው። እናም የሰፈራችን መስጂድ ባለ ሦስት ፎቅ ተደርጎ ተሰርቷል። ሚሕራብና ሚንበር የተሰራው ደግሞ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው። ስለዚህ ኢማማችን ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው የሚሰግዱት። ምክንያቱም ሁለተኛው ፎቅ ከሌሎቹ ይሰፋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው? ሁለተኛው ፎቅ ላይ ያለው ሚሕራብ ፈርሶ ወደ አንደኛው ፍሎር መምጣቱ ግዴታ ይሆናል? እንዳለ ቢተውስ ሶላታችን ላይ የሚፈጥረው ችግር አለ?


መልስ፡- የመጀመሪያውም ሆነ ሦስተኛው ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች የኢማሙን እንቅስቃሴ እሚያውቁ እስከሆነ ድረስ ሶላታቸው ትክክል ነው። ኢማም ፎቅ ላይ መሆኑም ሆነ መእሙም ወደ ታች ዝቅ ማለቱ ወይም በተቃራኒው መሆኑ ሶላት ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም። ስለዚህ መስጂዱን እንዳለው ተዉት። ምክንያቱም ኢማሙ ከፍም አለ ዝቅ በሶላታችሁ ላይ የሚፈጥረው ምንም አይነት ችግር የለም።

አላሁ አዕለም!