የጉዞ ላይ ሰላት አሰጋገድ

Home የፈትዋ ገጽ ሰላት የጉዞ ላይ ሰላት አሰጋገድ

ጥያቄ፡- አንድ መንገደኛ የመግሪብ ሰላቱን ወደ ዒሻ መውሰድ አሊያም የዒሻ ሰላቱን ወደ መግሪብ ማምጣት ይችላልን?


መልስ፡- መንገደኛ (ሙሳፊር) ለሆነ ሰው የዙህር ሰላትን ከዐስር የመግሪብን ሰላት ደግሞ ከዒሻ ጋር አሰባስቦ መስገድ የተፈቀደ ነው። አንድ ሰው የዙህርና የዐስር ሰላትን በዙህር አሊያም በዐስር ሰዓት አሰባስቦ መስገድ ይችላል። መግሪብ እና ዒሻን በመግሪብ አሊያም በዒሻ ወቅት መስገድም ይችላል። አራት ረከዓ የሆኑትን ሰላቶች ወደ ሁለት ማሳጠር (ተቅሲር) ይችላል። በፊቅህ ቋንቋ ሁለቱን ሰላቶች አስቀድሞ መስገድ “ጀምዕ ተቅዲም” ሲባል ወደኋላ አስቀርቶ መስገዱ ደግሞ “ጀምዕ ተእኺር” ይባላል። ባይሆን ከጀምዕ ተእኺር ይልቅ ጀምዕ ተቅዲም ማድረጉ ይመረጣል። ምክኒያቱም እስከዚያኛው ሰላት ድረስ በህይወት ስለመቆየቱ አያውቅምና ነው። በመሆኑም ሁሉንም ሰላቶች ወቅታቸው በገባ ጊዜ መስገዱ የተሻለ ነው። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም “በላጩ ሥራ ሰላትን በወቅቷ መጀመሪያ ላይ መስገድ ነው” ማለታቸው ተዘግቧል (አቢ ዳውድ)። አንድ ሰው መመቻቸቱ እያለው ሰላትን ሆን ብሎ ማዘግየት የለበትም። ወቅቱ እንደገባ ሰላትን መስገድ ይኖርብናል። በዚያ ሰዓት ላይ ላለመስገዳችን አሣማኝ የሆነ ምክኒያት ያለን ከሆነ እንጂ።