የሴት ልጅን እንቁላል ማምረቻ ቱቦ ስለማሰር

Home የፈትዋ ገጽ ጤናና ህክምና የሴት ልጅን እንቁላል ማምረቻ ቱቦ ስለማሰር

ጥያቄ:– በስኳር በሽታ ምክንያት ማህፀኗ ስለተጎዳ ባለቤቴ የእርግዝና መከላከያ ክኒን እንዳትወስድ ተከልክላለች። ስለሆነም የባለቤቴን ማህፀን እንቁላል ማምረቻ እንዳያመርት በማሰር ማሳገዱ ይፈቀዳል ወይ?


መልስ:- የእንቁላል ቱቦን ዳግም ፍሬ እንዳያፈራ አድርጎ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሰር በሸሪዓችን የተከለከለ ነው። የግድ መሆን ለሚገባው አሳማኝ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር። ክልከላው የተደረገው እስልምና የቆመለትን የሰውን ልጅ ዘር የማስቀጠል ዓላማ ስለሚፃረር ነው። በአንገብጋቢና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ ግን ለምሳሌ የእርግዝናው መከሰት በሴቷ ሕይወት ላይ በርግጠኝነት አደጋ ያመጣል ተብሎ ከተፈራ ወይም ደግሞ ከእናት ወደ ጽንስ በዘር የሚተላለፍ በሽታ ከተሰጋ የእንቁላል ማምረቻውን ማሰር ይፈቀዳል። ይህም በዘርፉ በሙያው በተካነ ታማኝ ሐኪም መረጋገጥ ይኖርበታል። ለዚህች ሴት ብቸኛው መፍትሄ ይህ ነው ተብሎ ከታመነ ይፈቀዳል። ካልሆነ ግን ወንጀል ነው።