የረመዷን አስተምህሮ ምንድን ነው?

Home የፈትዋ ገጽ ዒባዳ ጾምና ኢዕቲካፍ የረመዷን አስተምህሮ ምንድን ነው?

ጥያቄ፡- በረመዷን ውስጥ ትኩረት የሚሰጣቸው አስተምህሮዎች ምንድን ናቸው? እነዚህን አስተምህሮዎችስ እንዴት ማስተላፍ ይቻላል? በተለይም እኔ የጀመዓ አሚር ነኝ…


መልስ፡- የተከበርክ ወንድማችን ሆይ የረመዷን አስተምህሮዎች ብዙ ናቸው። ከነርሱ መሀል የተወሰኑትን እንጠቅስልህ፡-

  1. ረመዷን የተቅዋ ወር ነው። ስለዚህ ይህ ቃል (ተቅዋ) ለሚያካትታቸው ነገሮች ሁሉ ትኩረት ስጥ። ይህ ቃል የሚያካትታቸው ጥቅል ነገሮች ሁለት ናቸው። የአላህን ትእዛዝ መፈፀም እና ክልክሉን መከልከል። ትእዛዙን መፈፀም ሲባል -ግዴታ ያልሆኑ- ደጋግ ነገሮችንም መፈፀምን ያካትታል።
  2. ረመዷን የለውጥ ወር ነው። ከኢማን ድክመት ወደ ጥንካሬ እራሳችንን የምንለውጥበት፣ ከአሉታዊ ገፅታዎች ወደ አውንታዊነት የምንለወጥበት፣ ከመታከትና መሰላቸት ወደ ወኔ፣ ንቃትና ጥንካሬ የምንመጣበት እና ሌሎች መንፈሳዊ እድገቶችን የምንሰንቅበት ወር ነው።
  3. በረመዷን ውስጥ ጀነትን ለመሸመት ማቀድ ነው። ይህን በይበልጥ ለመረዳትና ስሜት ለመቀስቀስ የታላላቅ የሠለፍ ዘመን አባቶች ታላላቅ ተሞክሮዎችን ማጥናት ይጠቅማል።
  4. የረመዷንን ቱሩፋቶች ማስተማር ጠቃሚ ነው። እነዚህን ቱሩፋት ለማግኘት የሚጠቅሙ ዘዴዎችን በመቀየስ እና በመሰባሰብ የጀመዐ ጥረት ቢደረግ መልካም ነው እንላለን።
  5. እድልን መጠቀም። ረመዷን መልካም ለመስራት የሚያግዝ ጥሩ እድል ነው። በጀመዓችሁ ላይ ያሉ ድክመቶችን ለማስወገድም ጥሩ አጋጣሚ ነው። ስለዚህ የጋራ ትብብራችሁን የምታጠናክሩበትና እራሳችሁን ገምግማችሁ እርምት ማድረግ የምትችሉበት መልካም ጊዜ ነው።

አላህ የተሻለ ያውቃል!