ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷንን አይፆም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ?

Home የፈትዋ ገጽ ቤተሰብ አኽላቅና አዳብ ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷንን አይፆም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ?

ጥያቄ፡- ወላጆቼ አይሰግዱም፤ ረመዷን በሚመጣበት ጊዜም አይፆሙም። እነሱን መታዘዝ ይጠበቅብኛል ወይ? አንድ ሰው እንደነገረኝ ከሆነ ወላጆቼ አላህን እስካልታዘዙ ድረስ እኔም ለነሱ መታዘዝ እንደሌለብኝ ነው። ይህ በርግጥም ትክክል ነውን? እባክዎ ምክርዎን ይለግሱኝ


መልስ፡- አላህ ቤተሰቦችህን ወደ ቀጥተኛ መንገድ እንዲመራቸው እንለምነዋለን። አንተም ለነሱ ዱዓእ ማድረግ ይኖርብሃል። ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎችን ለነሱ ክብርና ትህትናን በተላበሠ መልኩ አስታውሳቸው። ለወላጆችህ በመታዘዙ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሀራም በሆነ ነገር ላይ እስካላዘዙህ ድረስ ልታዳምጣቸውና ልትታዘዛቸው ይገባል። እንደ ሸሪዓችን አስተምህሮ አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ሥራ እስካልጠየቁህ ድረስ ለወላጆችህ ልትታዘዛቸው ግድ ይላል። ለዚህም ማስረጃው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በቁርዓን ውስጥ እንዲህ ይላል

وَإِن جَاهَدَاكَ عَلَىٰ أَن تُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا وَصَاحِبْهُمَا فِي الدُّنْيَا مَعْرُوفًا وَاتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَيَّ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

“ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው። በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው። ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል። ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው። ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)።” (ሉቅማን 31፤15)።