ከሐራም የተገኘ የውርስ ገንዘብ

Home የፈትዋ ገጽ ቤተሰብ ገንዘብ ነክ ከሐራም የተገኘ የውርስ ገንዘብ

ጥያቄ፡- ወላጃችን መሬቶች እና የመኖሪያና የንግድ ቤቶች አውርሶን ሞቷል። ነገርግን በወለድ ይሰራ ነበር። ጉቦም ይቀበል ነበር። ከርሱ ያገኘነው ውርስ ለኛ ይፈቀድልናል?


መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢልዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላረሱሊላህ

ኢማም አል-ገዛሊይ “ኢሕያእ ዑሉሚዲን” የተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፡-

“ሰውየው ከወረሰው ሰው ያገኘው ገንዘብ ከሐራም ወይም ከሐላል እንደመጣ የማያውቅ ከሆነ፣ ከሐራም የሆነውን እና ከሐላል የሆነውን የሚለይበት ምልክት እስካላገኘ ድረስ- ዑለሞች ያለ ልዩነት- እንደሚፈቀድ ያምናሉ። ገንዘቡ ላይ ሐራም እንደተቀላቀለ ካወቀና መጠኑን ካላወቀ ደግሞ በጥንቃቄና በምርምር ሐራሙን ይለይና ሐላሉን መጠቀም እንደሚችል ያምናሉ።”

አንዳንድ ዑለሞች ግን “ምንም ነገር የለበትም። ኃጢያቱ ያለው በአስወራሹ ሰው ላይ እንጂ በወራሹ ሰው ላይ አይደለም።” ብለዋል። አንድ ሰውዬ በስልጣን ላይ ሲባልግ ቆይቶ ሲሞት ሶሐባው፡-

الآن طابَ ماله

“አሁን ገንዘቡ አማረ።”

ማለቱን እንደማስረጃ ይጠቅሳሉ። የቆሸሸው በርሱ ላይ ነበር እርሱ በማለፉ ለወራሾቹ ገንዘቡ አማረላቸው ማለታቸው ነው።

ነገርግን ይህ ሃሳብ ደካማ ነው። ምክንያቱም ይህንን ያለው ሶሐቢይ ማንነት ራሱ አይታወቅም። ምናልባት በፈትዋ ላይ ቸላተኛ የሆነ ሰው ሃሳብ ሊሆን ይችላል።

አላህ የበለጠ ያውቃል!