እግር አካባቢ እና ብብት ሥር የሚገኘውን ፀጉር መላጨት እንዴት ይታያል?

Home የፈትዋ ገጽ አኽላቅና አዳብ እግር አካባቢ እና ብብት ሥር የሚገኘውን ፀጉር መላጨት እንዴት ይታያል?

ጥያቄ፡- የኔ ጥያቄ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎች ላይ ለምሣሌ ከእግር ላይ እና ብብት ሥር የሚገኘውን ፀጉር መላጨትን ይመለከታል። እነኚህ የሰውነት ክፍሎች በአደባባይ የማይታዩ መሆናቸው ይታወቃል። ነገርግን ቢስተካከሉ ባልንም ሆነ ሴቷን ያስደስታሉ። እስልምና በዚህ ዙሪያ ምን ይላል?


መልስ፡- በበርካታ የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ሀዲሦች እንደተገለፀው ለሴት ልጅም ሆነ ለወንድ ልጅ ብብት ሥር እና ብልት አካባቢ የሚገኝን ፀጉር ማሰወገዱ ሱና ነው። በእግር ላይ ስለሚገኘው ፀጉር ግን በቁርዓንም ሆነ በሀዲስ ምንም የመጣ መመሪያ የለም።

በእስልምና በድንጋጌዎች ዙሪያ ዋናውና መሠረታዊው ጉዳይ በአምልኮ ተግባራት ላይ ብቻ ሲቀር ማንኛውም ነገር ክልከላ እስከሌለበት ድረስ የሚፈቀድ መሆኑን ነው። አንዲት ሴት ለራሷና ለባሏ ለማማር ብላ በእግሯ ላይ ያለውን ፀጉር ብታስወግድ ይህን ማድረጓ ክልክልነት የለውም። ነገርግን ይህን ያደረገችው እግሯን በአደባባይ ለማሣየት ከሆነ ወንጀሏ እንዲያውም እጥፍ ይሆናል። አንደኛው እንዳታሣይ የታዘዘችውን የሰውነት ክፍሏን በአደባባይ በማሣየቷ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መጥፎ ሀሳብ በውስጧ ይዛ ለመጥፎ ዓላማ ብላ ፀጉሯን ማስወገዷ ነው።

አላሁ አዕለም!