እርጉዝ ሴት ፆም ማፍጠር ይፈቀድላታል?

Home የፈትዋ ገጽ ዒባዳ ጾምና ኢዕቲካፍ እርጉዝ ሴት ፆም ማፍጠር ይፈቀድላታል?

ጥያቄ፡- እርጉዝ ሴት በረመዳን ውስጥ በቀን ማፍጠር ይፈቀድላታል?


መልስ፡- ማፍጠር ይፈቀድላታል። ነገር ግን ከወለደችና ጥንካሬዋ ከተመለሰ በኋላ ቀዷ ማውጣት ግዴታ ይሆንባታል። ይህም ለተከታታይ ብዙ አመታት መፆም የማትችልበት ወሊድና ማጥባት ካልተከታተለባት ነው። ለተከታታይ አመታት ወሊድና ማጥባት ላይ ካሳለፈች ግን ላፈረሰችው እያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን (ደሀ) እየመገበች ታፈጥራለች። ከዚህ ውጭ ምንም የለባትም።

አላህ የተሻለ ያውቃል!