አንድ ሰው ሰውነቱን ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን?

Home የፈትዋ ገጽ ጣሃራ አንድ ሰው ሰውነቱን ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን?

ጥያቄ፡- አንድ ሰው በሙሉ ሰውነቱ ላይ ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን? ወይራ ዘይቱ ከተቀባ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተመጦ ይጠፋል። ታዲያ የተቀባው ሰው ዘይቱን በሣሙና መታጠብ ይኖርበታል ወይ?


መልስ፡- ቀለል ያለ ዘይት ተቀብተን ከሆነ ውዱእ ከማድረጋችን በፊት ዘይቱን አሊያም የቆዳ ቅባቱን በሣሙና ለማስወገድ መጨናነቅ አያስፈልግም። አንድ ሰው ማረጋገጥ ያለበት ነገር ቢኖር ውሃው በትክክል ወደ ሰውነት ቆዳው መድረሱንና ለውዱእ መታጠብ የሚገባውን ክፍል ማዳረሱ ነው። ነገር ግን ውሃ ወደ ሰውነት እንዳይደርስ የሚከለክል ወፈር ያለ ቅባት ከሆነ ግን ውዱእ ከማድረግ በፊት ቅባቱን ማስወገድ ይኖርበታል።