ተሸሁድ/አተሒያቱ ላይ ጣቶችን ማወዛወዝ ይፈቀዳል?

Home የፈትዋ ገጽ ሰላት ተሸሁድ/አተሒያቱ ላይ ጣቶችን ማወዛወዝ ይፈቀዳል?

ጥያቄ:- በተሸሁድ ጊዜ ጣቶችን ማነቃነቅ እንዴት ይታያል? ቢድዐ ነው ወይስ ሱና?


መልስ፡- የፊቅህ ልሂቃን – በጥቅሉ – በተሸሁድ ወቅት ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለውን ጠቋሚ ጣት ከፍ ማድረግ ሱና እንደሆነ ይስማማሉ። መልዕክቱም የአላህን አንድነት፣ ኢኽላስን ያመላክታል። ነገርግን ጣት እንዴት ከፍ እንደሚደረግ የዑለሞች ልዩነት አለ።  ነገርግን ልዩነቶቻቸው የቱ ነው የተሻለው በሚል ሃሳብ ዙርያ እንጂ የመፈቀድ እና ያለመፈቀድ ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም የተለያየ የጣት አነሳስ እንዳለ የሚያሳዩ ሐዲሶች ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ፉቀሃኦች ተሸሁድ ላይ ጣትን ማንሳት ብቻ ይበቃል ብለው ያምናሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ጣትን ከፍ ከማድረግ በተጨማሪ ማነቃነቅ ይወደዳል የሚሉ አሉ።

ነገርግን እነዚህ ሁሉ ሶላት ውስጥ መኖር ያለበትን ኹሹዕ/ተመስጥዖ የሚያጠፋ ይዘት ያላቸው መሆን የለባቸውም።

ወላሁ አዕለም!