ሬዲዮን ተከትሎ ጁሙዐ መስገድ ይቻላል?

Home የፈትዋ ገጽ ሰላት ሬዲዮን ተከትሎ ጁሙዐ መስገድ ይቻላል?

ጥያቄ:- ያለ ኢማም እና ያለ ኸጢብ/ኹጥባ አድራጊ ራዲዮ አዳምጠን አስከትለን ጁሙዐን መስገድ እንችላለን?


መልስ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ):-

صلوا كما رأيتموني أصلي

“ስሰግድ እንዳያችሁት አድርጋችሁ ስገዱ።” ይላሉ።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ ጁሙዐን በስብስብና በህብረት እንጂ አልሰገዱም። “ሁለት ኹጥባ ከሶላት በፊት ያደርጉም ነበረ። ሁለቱን ኹጥባዎች ደግሞ በመሀል በመቀመጥ ይለዯቸዋል።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ለዚህ ነው ዑለሞቹ በአንድነት/በኢጅማዕ “ጁሙዐ በህብረት መሆን እንዳለበት፣ ከስብስቡ መሀልም አንዱ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንዳለበት ያመኑት፤ ኢማም ነወዊይ ስምምነታቸውን “አል-መጅሙዕ” ላይ ጠቅሰውታል። ይህ ባልሆነበት ተጨባጭ ሶላቱ ውድቅ ነው።

ኢማም ኢብኑ ቁዳማ ሙግኒ የተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ:- “ኹጥባ ለሶላቱ ቀዳሚ መስፈርት ነው። ያለ ኹጥባ ሶላቱ አያብቃቃም። ይህ የአራቱ መዝሀብ ዑለሞች እምነትና ስምምነት ነው።” ስለዚህ ያለ ኢማምና ያለ ኸጢብ ጁሙዐን መስገድ ውድቅ ነው። በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን የኢማሙን እንቅስቃሴ ማወቅና መስማት ብቻውን ዋጋ የለውም።

ወላሁ አዕለም!