Category: ዒባዳ

Home የፈትዋ ገጽ
ኢሕራም ላይ ያለ ሰው ቀበቶ መታጠቅ ይችላል?

ጥያቄ፡- ገንዘብ እና ልዩልዩ መረጃዎቼን ለመያዝ እንዲመቸኝ የተሰፋ ቀበቶ መታጠቅ እችላለሁ? መልስ፡- ብዙ ሰዎች ኢሕራም ላይ ያለ ሰው የተሰፋ ልብስን በምንም መልኩ መልበስ እንደማይችል ያስባሉ። ነገርግን ጉዳዩ እንዲህ በጥቅሉ ሳይሆን ማብራሪያ ይፈልጋል። ኢሕራም ውስጥ ባለ ሰው ላይ እርም የሚሆነው ልብስ በአካላት ልክ የተሰፋ- እንደ ሱሪና እና እንደ ቀሚስ ያለ ልብስ- ነው። ክር የነካውን ልብስ ሁሉ እርም […]

ሐጅ ላይ ያለ ሰው በምን አይነት ስራ ይጠመድ?

ጥያቄ፡- በሐጅ ጊዜ ውስጥ ሐጀኛ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ስራዎች ምንድን ናቸው? መልስ፡- ታላቁ ዐሊም ዶክተር ዩሱፍ አል-ቀረዳዊ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡- “ሐጀኛ በሐጅ ጊዜው አላህን በማውሳት-በዚክር-፣ በዒባዳ፣ የአላህን ትዕዛዛት በመከወን እና ወደ አላህ የሚያቃርቡ በሆኑ በጎ ሥራዎች-በሶደቃ፣ ደካሞችን በማገዝ፣ እውቀት የሌላቸውን በማስተማር…- ራሱን መጥመድ ነው ያለበት። ባገኘው አጋጣሚ አብዝቶ ቁርኣንን ማንበብ ይወደድለታል። በቻለው አቅም ታላቁ መስጂድ (መስጂዱል-ሐረም) […]

የሴቶች ኢሕራም ፊትን መግለጥ የሆነበት ብይን እና ጥበብ

ጥያቄ፡- ኢሕራም ላይ ያለች ሴት ፊቷን መሸፈን ወይም ኒቃብ መልበስ እርም ይሆንባታል? ፊቷን ብትሸፍን ኃጢያተኛ ትሆናለች ማለት ነው? ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ሴት ኢሕራም ላይ ፊቷን እንድትገልጥ የታዘዘበት ጥበብ ምንድን ነው? መልስ፡- አብዝሃኞቹ ዑለሞች በኢሕራም ወቅት ሴት ፊቷን መሸፈን እርም እንደሚሆንባት ያምናሉ። ስለዚህ ኒቃብም ሆነ ጓንት አትለብስም። ምክንያቱም የሴት የኢሕራም መገለጫ ፊቷን መክፈቷ ነው። የሐዲስ ኢማሞቹ ቡኻሪይ፣ […]

ሐጅ ላይ ሁለት ኒያዎችን መሰብሰብ

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ጾም ሱና የሆነበትን ቀን ከአንድ በላይ በሆነ ኒያ ከጾመው ምንዳው በኒያው ልክ እንደሆነ አውቃለሁ። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ኢነመል አዕማሉ ቢኒያ” (ስራ ሁሉ የሚለካው በኒያ ነው) ብለዋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው፡- ሰውየው ግዴታ የሆነበትን ሐጅ በሑለት ኒያዎች መፈፀም ይችላል? ለምሳሌ አንዲትን ሐጅ ለራሱ እና ለአንድ ወላጁ ሊነይትባት ይችላል? አላህ ይስጥልኝ! መልስ፡- የአንድ ሰው ጫንቃ- […]

ሀጃጆች ኢሕራም የሚያደርጉበት ቦታ

ጥያቄ፡- መካ ወይም መዲና ውስጥ ለሐጅ የተወሰነ የኢሕራም ቦታ አለ? ካለ የት ነው? መልስ፡- ሐጅ ወይም ዑምራ ማድረግ የሚሻ ሰው ኢሕራም የሚያደርግበት ቦታን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የገደቡት ቦታ አለ። ሐጅ ወይም ዑምራ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ሊያልፋቸው የማይገቡ የኢሕራም ስፍራዎችን (ሚቃትን) ወስነው ገልፀዋል። ሰውየው እነዚህን ስፍራዎች ከማለፉ በፊት ኢሕራም ማድረግ እንዳለበትም አሳውቀዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለመዲና […]

ሴት የሐጅ ስራዎችን እንዲከውንላት ሌላን ሰው መወከል ትችላለች?

ጥያቄ፡- በዚህ አመት- አላህ ካለ- እናቴን ይዤ ሐጅ አደርጋለሁ። እናቴ እድሜዋ ትልቅ ነው። አርጅታለች። ህመምተኛና ደካማ ሴት ናት። ስለዚህ እናቴን ተክቼ መስራት የምችላቸው የሐጅ ስራዎች የትኞቹ ናቸው? መልስ፡- ጠጠር መወርወር እና እርድ ማከናወን ላይ እናትህን መተካት ትችላለህ። ከዚህ ውጪ ያሉት የሐጅ ስራዎች ላይ ግን እናትህ በራሳቸው መፈጸም አለባቸው እንጂ ልትወከላቸው አትችልም። ክብርት እናትህ በመኪና ተሳፍረው ወደ […]

በኢሕራም ውስጥ የተከለከሉ ነገሮችን መፈፀምና ቅጣቱ

ጥያቄ፡ በኢሕራም ወቅት ክልክል የሆኑ ነገሮችን መፈፀም ብይኑ ምንድን ነው? ጥፋቱን የፈፀመ ሰውስ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? መልስ፡- በኢሕራም ወቅት እርም የሆኑ ነገሮችን የፈፀመ ሰው የሚቀጣው ቅጣት እንደፈፀመው ነገር ይለያያል። ዐረፋ ላይ ከመቆሙ በፊት ወሲብ ፈፅሞ ከሆነ ሐጁ ይበላሽበታል። በሚመጣው ዓመት ቀዷ ከማውጣት ጋር ግመል ማረድ ግዴታ ይሆንበታል። አብዝሃኞቹ ዑለሞች ዘንድ ዐረፋ ላይ ከቆመ በኋላ ቢሆንም ቅጣቱ […]

አንድ ሰው ሰውነቱን ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን?

ጥያቄ፡- አንድ ሰው በሙሉ ሰውነቱ ላይ ወይራ ዘይት ቢቀባና ከዚያም ውዱእ ቢያደርግ ውዱኡ ትክክል ነውን? ወይራ ዘይቱ ከተቀባ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተመጦ ይጠፋል። ታዲያ የተቀባው ሰው ዘይቱን በሣሙና መታጠብ ይኖርበታል ወይ? መልስ፡- ቀለል ያለ ዘይት ተቀብተን ከሆነ ውዱእ ከማድረጋችን በፊት ዘይቱን አሊያም የቆዳ ቅባቱን በሣሙና ለማስወገድ መጨናነቅ አያስፈልግም። አንድ ሰው ማረጋገጥ ያለበት ነገር ቢኖር ውሃው […]

የጀመዐን ምንዳ ለማግኘት ፈርድ ሶላትን ደግሞ መስገድ

ጥያቄ፡- የመግሪብን ሶላት ለብቻዬ ከሰገድኩኝ በኋላ በጀመዐ ሲሰገድ አገኘሁኝ። አብሬያቸው ደግሜ መስገድ እችላለሁ? ስሰግድስ ሦስት ረከዐ ነው የምሰግደው ወይስ አራት አድርጌ ልስገደው? መልስ፡- ሶላትን በህብረት (በጀመዐ) መስገድ ብቻውን ከመስገድ በሃያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “صَلَاةُ الْجَمَاعَةِ تَفْضُلُ صَلَاةَ الْفَذِّ بِسَبْعِ وَعِشْرِينَ دَرَجَةً“ موطأ مالك، وفي رواية “بِخَمْسٍ وَعِشْرِينَ“ “የጀመዐ ሶላት ለብቻ ከሚሰገድ […]

ካዕባ አጠገብ ያለው የሰይዲና ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) መቃም ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ ያለው የእግር አሻራ

ጥያቄ፡- መቃሙ ኢብራሂም (የኢብራሂም የመቆሚያ ስፍራ) ተብሎ የሚጠራው ቦታ ላይ ያለው የእግር አሻራ የራሳቸው የኢብራሂም የእግር አሻራ ነው? መልስ፡- መቃሙ ኢብራሂም የሚባለው ስፍራ የጥንታዊው ቤተ-መለኮት (አል-በይቱል-ዐቲቅ) መሰረት ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ አላህ እስካሁን ጠብቆ ያቆየው የኢስላም ቅርስ ነው። ቦታው ውዱ የአላህ ነብይ- ኢብራሂም- ካዕባን ሲገነቡ የቆሙበት ድንጋይ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- “ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል። […]