Category: ዒባዳ

Home የፈትዋ ገጽ
በሶላት ውስጥም ሆነ ከሶላት ውጪ ከዱዐ በኋላ ፊትን በእጆች መዳበስ

ጥያቄ፡- ከዱዐ በኋላ ፊትን በእጆች መዳበስ እንዴት ይታያል? መልስ፡- ዱአዕ ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ታላላቅ ስራዎች መካከል አንዱ ነው። አላህን እጅግ መፈለግና እርሱን መከጀል የሚታይበት ተግባር ነው። ሰውየው የራሱን ድህነትና የአላህን ሀብታምነት የሚያውጅበትም ድርጊት ነው። የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) አምልኮ (ዒባዳ) ብለው ሰይመውታል። አቡ ዳዉድ፣ ቲርሙዚይ (ሶሒሕ አድርገውት)፣ አሕመድ፣ ኢብኑ ሒባን፣ አል-ሐኪም (ሶሒሕ አድርገውት) ከኑዕማን ቢን በሺር እንደዘገቡት […]

ተሸሁድ/አተሒያቱ ላይ ጣቶችን ማወዛወዝ ይፈቀዳል?

ጥያቄ:- በተሸሁድ ጊዜ ጣቶችን ማነቃነቅ እንዴት ይታያል? ቢድዐ ነው ወይስ ሱና? መልስ፡- የፊቅህ ልሂቃን – በጥቅሉ – በተሸሁድ ወቅት ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለውን ጠቋሚ ጣት ከፍ ማድረግ ሱና እንደሆነ ይስማማሉ። መልዕክቱም የአላህን አንድነት፣ ኢኽላስን ያመላክታል። ነገርግን ጣት እንዴት ከፍ እንደሚደረግ የዑለሞች ልዩነት አለ።  ነገርግን ልዩነቶቻቸው የቱ ነው የተሻለው በሚል ሃሳብ ዙርያ እንጂ የመፈቀድ እና ያለመፈቀድ […]

ሬዲዮን ተከትሎ ጁሙዐ መስገድ ይቻላል?

ጥያቄ:- ያለ ኢማም እና ያለ ኸጢብ/ኹጥባ አድራጊ ራዲዮ አዳምጠን አስከትለን ጁሙዐን መስገድ እንችላለን? መልስ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ):- صلوا كما رأيتموني أصلي “ስሰግድ እንዳያችሁት አድርጋችሁ ስገዱ።” ይላሉ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ ጁሙዐን በስብስብና በህብረት እንጂ አልሰገዱም። “ሁለት ኹጥባ ከሶላት በፊት ያደርጉም ነበረ። ሁለቱን ኹጥባዎች ደግሞ በመሀል በመቀመጥ ይለዯቸዋል።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ለዚህ ነው ዑለሞቹ በአንድነት/በኢጅማዕ “ጁሙዐ በህብረት […]

ፎቅ ላይ ሆኖ ኢማምን መከተል ይቻላል?

ጥያቄ፡- እንደሚታወቀው ከቦታ ጥበት የተነሳ መስጂዶቻችን ፎቅ እየሆኑ ነው። እናም የሰፈራችን መስጂድ ባለ ሦስት ፎቅ ተደርጎ ተሰርቷል። ሚሕራብና ሚንበር የተሰራው ደግሞ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው። ስለዚህ ኢማማችን ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው የሚሰግዱት። ምክንያቱም ሁለተኛው ፎቅ ከሌሎቹ ይሰፋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው? ሁለተኛው ፎቅ ላይ ያለው ሚሕራብ ፈርሶ ወደ አንደኛው ፍሎር መምጣቱ ግዴታ ይሆናል? እንዳለ ቢተውስ ሶላታችን […]

ሶላት ውስጥ ከፋቲሐ ጋር ድምፅን ከፍ አድርጎ “ቢስሚላሂር-ራሕማኒር-ረሒም” ማለት

ጥያቄ፡- ድምጽን ከፍ አድርጎ በሚሰገድባቸው ሶላቶች ውስጥ ፋቲሐን ስንቀራ ድምፅን ከፍ አድርጎ ቢስሚላሂ ማለት ግዴታ ነው? ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ የማያነባትን ሰው ተከትለን አንስገድ ወይስ ድምፅን ከፍ ማድረግም ሆነ ዝግ ማድረግ እኩል ነው? መልስ፡- በሶላት ውስጥ “ቢሰሚላሂን…” ከፍ ባለ ድምፅ ማንበብ (አል-ጃህር ቢበስመላህ) ዑለሞች የተለያዩበት ጉዳይ ነው። ሻፊዒዮቹ ድምፅን ከፍ ማድረግ ሱና ነው ብለው ያምናሉ። ሌሎች […]

በቀብር ወቅት ዱዐ ማድረግ

ጥያቄ:-  የሞተን ሰው የሚሸኙ ሰዎች ምን ያድርጉ? ድምፃችንን ከፍ አድርገን በህብረት ለሞተ ሰው ዱዐ ማድረግ እንችላለን?  መልስ:- ለተመሳሳይ ጥያቄ የግብፁ ዳሩል-ኢፍታእ የሚከተለውን መልስ አስፍሯል፡- ከቀብር ስነስርዐት በኋላ ሸኚዎቹ በቀብሩ ላይ ቆይተው ለሟቹ ዱዐ ማድረግ ይወደድላቸዋል። ምክንያቱም አቡዳዉድና ሐኪም- በሶሒሕ ሰነድ- ከዑስማን ይዘው እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞተን ሰው ቀብረው ካገባደዱ በኋላ ቀብሩ ላይ በመቆም እንዲህ ይሉ ነበር:-  استغفروا […]

ከሴት ልጅ ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ብይን

ጥያቄ:- በእርግዝና ወራትም ሆነ በሌላ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ከሴት ልጅ ማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ብይኑ ምንድነው? ነጃሳ ነውን? ዉዱእ ማድረግን ያስገድዳልን? መልስ:- ሴት ልጅ በንጽሕና ጊዜያት አሊያም በእርግዝና ወቅት ልጅ በሚወጣበት በኩል የሚፈሳት ፈሳሽ ጠሃራ (ንፁህ) ነው። ደም የተቀላቀለበት ካልሆነ በስተቀር። ዉዱእ ያበላሻል የሚል ማስረጃም የለም። በሽንት መውጫ በኩል የሚወጣው ፈሳሽ ግን ከሽንት መጣራቀሚያ ፊኛ ጋር […]

ኃጢያተኛ ኢማም

ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል? መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው። የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡- ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው […]

የጀናዛ ሶላትን ለማስገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው

ጥያቄ:- የጀናዛ ሶላትን ለማሰገድ ይበልጥ ተገቢው ሰው ማነው? የመስጂዱ ኢማም ወይስ የሟቹ የቅርብ ዘመድ? መልስ፡- ዑለሞች በሟች ላይ ሶላት ለማሰገድ እጅግ ተገቢው ሰው የትኛው ነው በሚለው ቅደም ተከተል ላይ ወጥ አቋም መያዝ አልቻሉም። ከፊሎቹ ጭቅጭቅና ዉዝግብን ለማስወገድ ሲባል ሥልጣኑ ያለው- ማለትም የሥልጣን ባለቤት የሆነው ክፍል እንዲያሰግድ፣ ኹጥባ እንዲያደርግና ለሌላም ነገር የወከለው መደነኛ ኢማም ነው ተገቢው […]

ከዘዋል (ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት) ጠጠር ስለመወርወር

ጥያቄ፡- የሐጅ ስነስርዐት ላይ- በተለይም ጠጠር በሚወረወርበት ወቅት ከፍተኛ ግፊያ እናስተውላለን። የተሸሪቅ ቀናት ላይ ጠጠርን ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊት ጠጠር መወርወር እንችላለን? መልስ፡- የዙልሒጃ ወር አስራ አንደኛው፣ አስራ ሁለተኛው እና አስራ ሶስተኛው ቀን ወይም የተሸሪቅ ቀናት ተብለው በሚጠሩት ቀናት ላይ ጠጠር መወርወር የሚገባው ፀሀይ ወደ ምዕራብ ካጋደለች በኋላ ነው። ነገርግን አንዳንድ ዑለሞች ከፍተኛ ግፊያ የሚፈጠር […]