Category: ጾምና ኢዕቲካፍ

Home የፈትዋ ገጽ
ከሦስቱ መስጂዶች ውጭ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይቻላል?

ጥያቄ፡- ከሦስቱ መስጂዶች ውጭ በሌሎች መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይቻላል? ምንድን ነው ማስረጃው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ከሦስቱ መስጂዶች- ከመካው የሐረም መስጂድ፣ ከመዲናው የነብዩ መስጂድ እና ከአል-አቅሷ መስጂድ- ውጪ በሌሎች መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይቻላል። ምክንያቱም ይህን የሚያስረዱ ጥቅል የሐዲስ እና የቁርኣን መረጃዎች ተገኝተዋል። ሦስቱን መስጂዶች ለይተው የመጡ የሐዲስ ዘገባዎች […]

ኢዕቲካፍ፡- ድንጋጌው፣ መስፈርቶቹ፣ የሚያበላሹት እና ጊዜው

ጥያቄ፡- ብዙ ጊዜ ኢዕቲካፍ የማድረግ ልምድ ቢኖረኝም በተጨባጭ ስለኢዕቲካፍ የማላውቃቸው ነገሮች ሞልተዋል። በኢዕቲካፍ ወቅት የሚፈቀድልኝ ነገሮች ምንድን ናቸው? በኢዕቲካፍ ወቅት ሐራም የሚሆኑብ ነገሮችስ ምንድን ናቸው? ለስራ እየወጣሁ ተመልሼ መግባት እችላለሁ?… መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ኢዕቲካፍ ወደ አላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ነው። ሱናም ነው። በተለይም በረመዷን ውስጥ እጅግ ከሚወደዱ ተግባራት መሀል […]

የእስረኛ ጾም

ጥያቄ፡- ምርኮ ወይም በምርመራ ላይ ያለ እስረኛ ጾም ግዴታ ይሆንባቸዋል? መልስ፡- ጾም ከስሜት መታቀብ ነው። ጾም ወደ አላህ ለመቃረብ ብሎ አስቦ ከሚያስፈጥሩ ነገሮች- ከምግብ፣ ከመጠጥና ከስሜት ንከኪ መከልከል ነው። ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታው ላይ ሆኖ ጾም ሊነይት ይችላል። ምርኮ መሆን ወይም እስር ከዚህ ተግባር አያግደውም። ሁለቱን  የጾም ማዕዘናት- ኒያንና መታቀብን- እስካሟላ ድረስ መጾም ይችላል። ነገርግን እስረኛ […]

የህመምተኛ ጾም፤ ብይኑ እና ጥበቡ

ጥያቄ፡- ባለቤቴ የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ ናት። ቋሚ የሆነ የኩላሊት በሽታም አለባት። ሐኪሞች እንዳትጾም ቢመክሩም እርሷ ግን እምቢ ብላለች። በጾም ምክንያት አንዳንዴ ራሷን ትስታለች። ዲን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው እይታ ምንድን እንደሆነ ማወቅ እሻለሁ። ጀዛኩሙላሁ ኸይር። መልስ፡- አላህ ህመምተኛ በረመዷን እንዲያፈጥር ፈቅዷል። አላህ ያዘዛቸው ግዴታዎቹ ሲፈፀሙ እንደሚደሰተው ሁሉ ፍቃዶቹና ማግራራቶቹ ሲከወኑለትም ይወዳል። ሊያገራልን እንጂ ሊያጠብቅብን […]

ጾም ላይ ሳይነይት ንጋት ከቀደደ?

ጥያቄ፡- በለሊት ከሱብሒ በፊት ረስቼ አልነየትኩም። ከዚያም ከፈጅር በኋላ እንዳልነየትኩኝ ትዝ አለኝ። ጾሜ ትክክል ይሆንልኛል? መልስ፡- ጾም ያለኒያ አይሆንም። ተቀባይነት የለውም። አብዝሃኞቹ ዑለሞች ለየዕለቱ መነየት ግዴታ እንደሆነ ያምናሉ። አንዳንዶቹ የመጀመሪያው የረመዷን ለሊት ላይ የወሩን መነየት ይበቃል ብለው ያምናሉ። የኒያው ጊዜ ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ንጋት ከመቅደዱ በፊት ነው። በዚህ የጊዜ ገደቡ ውስጥ በማንኛውም ወቅት ሰውየው ኒያ […]

በረመዳን አውቆ ጾምን ማፍረስ ብይኑ ምንድን ነው?

ጥያቄ፡- አጎቴ እኔ ቤት ውስጥ ይኖራል። ረመዳንን አይጾምም። ሆን ብሎ እያወቀ ያፈጥራል። እኔ ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? ባለቤቴ ምግቡን በመስራቷ ኃጢያተኛ ትሆናለች? መልስ፡- ጾም ግዴታ መደረጉን ከድቶ ከሆነ ከኢስላም ይወጣል። ይከፍራል። በረመዷን የሚያፈጥረው -አውቆ፣ ያለበቂ ሸሪዓዊ ምክንያት እና እርም መሆኑን እያመነ ከሆነ ሙስሊም ነው፤ ከኢስላም አይወጣም። ነገርግን እጅግ ከባድ ኃጢያት ፈፅሟል። አመጸኛ ነው። ቅጣትም ይገባዋል። […]

መንገደኛ መቼ ነው የሚያፈጥረው?

ጥያቄ፡- ሰውየው ጉዞ ለመውጣት ከወሰነ በኋላ መቼ ነው ማፍጠር የሚፈቀድለት? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ሰማንያ አምስት ኪሎ ሜትር እና ከዚያ በላይ የሚጓዝ መንገደኛ በረመዷን የማፍጠር ፍቃድ አለው። ነገርግን በሌላ ጊዜ ያፈጠረውን ያካክሳል። በመንገደኛ ሰው ላይ የተገደቡ ህግጋት የሚጀምሩት መቼ ነው በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ዑለሞች የተለያየ ሀሳብ ሰንዝረዋል። የተሻለው ሃሳብ- ወላሁ […]

ኢፍጣርና የመግሪብ ሶላት፤ የቱን ላስቀድም?

ጥያቄ፡- የቱን እናስቀድም? ኢፍጣርን ወይስ የመግሪብን ሶላት?  ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ከመግሪብ ሶላት በፊት ትንሽ በመቅመስ ጾምን መፍታት ይበቃል ወይስ ሙሉ ምግብ መመገብ ይቻላል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በእሸት ተምርና በደረቅ ተምር ያፈጥሩ እንደነበር ተዘግቧል። ይህን ካላገኙ ግን በውሃ ያፈጥሩም ነበር። ጸሀይ መጥለቋን እንዳረጋገጡ ፊጥራቸውን ያቻኩሉ ነበር። ፊጥርን […]

ሱሑር በጾም ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ

ጥያቄ፡- ሱሑር መመገብ ግዴታ ነው? “ሱሑር ተመገቡ። ሱሑር መመገብ ውስጥ በረከት አለ።” የሚለው ሐዲስ ውስጥ በረክት/በረካ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ሱሑር ሱና ነው እንጂ ግዴታ አይደለም። ግዴታው ሰውየው በለሊት ከንጋት በፊት ኒያ አድርጎ ማደሩ ብቻ ነው። ኒያ በየዕለቱ መሆን አለበት ወይስ ለሙሉው ወር አንድ ኒያ ይበቃል […]

በረመዷን በቀን የፍትወት ፈሳሽን ማውጣት (ማስተርቤሽን)

ጥያቄ፡- በረመዷን በቀን ፍትወትን አውቆ ማፍሰስ እንዴት ይታያል? መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ ጥያቄውን እንደሚከተለው እንመልሳለን፡፡ ፍትወትን ለማውጣት ብልትን በእጅ መነካካት የፍትወት ፈሳሽን እስካላወጣ -እንደ ሐነፊዮቹ እይታ- ጾምን አያፈርስም፡፡ በእጁ ሲነካካ ፍትወቱ የፈሰሰ ከሆነ ግን ጾሙ ይፈርሳል፡፡ ነገርግን ሰውየው ቀዷ መክፈል ብቻ ነው ግዴታ የሚሆንበት፡፡ ነገርግን ሰውየው ከዚህ ቆሻሻ ተግባር ሰውየው […]