Category: ሰላት

Home የፈትዋ ገጽ
ተሸሁድ/አተሒያቱ ላይ ጣቶችን ማወዛወዝ ይፈቀዳል?

ጥያቄ:- በተሸሁድ ጊዜ ጣቶችን ማነቃነቅ እንዴት ይታያል? ቢድዐ ነው ወይስ ሱና? መልስ፡- የፊቅህ ልሂቃን – በጥቅሉ – በተሸሁድ ወቅት ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለውን ጠቋሚ ጣት ከፍ ማድረግ ሱና እንደሆነ ይስማማሉ። መልዕክቱም የአላህን አንድነት፣ ኢኽላስን ያመላክታል። ነገርግን ጣት እንዴት ከፍ እንደሚደረግ የዑለሞች ልዩነት አለ።  ነገርግን ልዩነቶቻቸው የቱ ነው የተሻለው በሚል ሃሳብ ዙርያ እንጂ የመፈቀድ እና ያለመፈቀድ […]

ሬዲዮን ተከትሎ ጁሙዐ መስገድ ይቻላል?

ጥያቄ:- ያለ ኢማም እና ያለ ኸጢብ/ኹጥባ አድራጊ ራዲዮ አዳምጠን አስከትለን ጁሙዐን መስገድ እንችላለን? መልስ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ):- صلوا كما رأيتموني أصلي “ስሰግድ እንዳያችሁት አድርጋችሁ ስገዱ።” ይላሉ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ ጁሙዐን በስብስብና በህብረት እንጂ አልሰገዱም። “ሁለት ኹጥባ ከሶላት በፊት ያደርጉም ነበረ። ሁለቱን ኹጥባዎች ደግሞ በመሀል በመቀመጥ ይለዯቸዋል።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ለዚህ ነው ዑለሞቹ በአንድነት/በኢጅማዕ “ጁሙዐ በህብረት […]

ፎቅ ላይ ሆኖ ኢማምን መከተል ይቻላል?

ጥያቄ፡- እንደሚታወቀው ከቦታ ጥበት የተነሳ መስጂዶቻችን ፎቅ እየሆኑ ነው። እናም የሰፈራችን መስጂድ ባለ ሦስት ፎቅ ተደርጎ ተሰርቷል። ሚሕራብና ሚንበር የተሰራው ደግሞ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው። ስለዚህ ኢማማችን ሁለተኛው ፎቅ ላይ ነው የሚሰግዱት። ምክንያቱም ሁለተኛው ፎቅ ከሌሎቹ ይሰፋል። ጥያቄዬ ምንድን ነው? ሁለተኛው ፎቅ ላይ ያለው ሚሕራብ ፈርሶ ወደ አንደኛው ፍሎር መምጣቱ ግዴታ ይሆናል? እንዳለ ቢተውስ ሶላታችን […]

ሶላት ውስጥ ከፋቲሐ ጋር ድምፅን ከፍ አድርጎ “ቢስሚላሂር-ራሕማኒር-ረሒም” ማለት

ጥያቄ፡- ድምጽን ከፍ አድርጎ በሚሰገድባቸው ሶላቶች ውስጥ ፋቲሐን ስንቀራ ድምፅን ከፍ አድርጎ ቢስሚላሂ ማለት ግዴታ ነው? ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ የማያነባትን ሰው ተከትለን አንስገድ ወይስ ድምፅን ከፍ ማድረግም ሆነ ዝግ ማድረግ እኩል ነው? መልስ፡- በሶላት ውስጥ “ቢሰሚላሂን…” ከፍ ባለ ድምፅ ማንበብ (አል-ጃህር ቢበስመላህ) ዑለሞች የተለያዩበት ጉዳይ ነው። ሻፊዒዮቹ ድምፅን ከፍ ማድረግ ሱና ነው ብለው ያምናሉ። ሌሎች […]

ኃጢያተኛ ኢማም

ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል? መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው። የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡- ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው […]

የጀመዐን ምንዳ ለማግኘት ፈርድ ሶላትን ደግሞ መስገድ

ጥያቄ፡- የመግሪብን ሶላት ለብቻዬ ከሰገድኩኝ በኋላ በጀመዐ ሲሰገድ አገኘሁኝ። አብሬያቸው ደግሜ መስገድ እችላለሁ? ስሰግድስ ሦስት ረከዐ ነው የምሰግደው ወይስ አራት አድርጌ ልስገደው? መልስ፡- ሶላትን በህብረት (በጀመዐ) መስገድ ብቻውን ከመስገድ በሃያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “صَلَاةُ الْجَمَاعَةِ تَفْضُلُ صَلَاةَ الْفَذِّ بِسَبْعِ وَعِشْرِينَ دَرَجَةً“ موطأ مالك، وفي رواية “بِخَمْسٍ وَعِشْرِينَ“ “የጀመዐ ሶላት ለብቻ ከሚሰገድ […]

የጉዞ ላይ ሰላት አሰጋገድ

ጥያቄ፡- አንድ መንገደኛ የመግሪብ ሰላቱን ወደ ዒሻ መውሰድ አሊያም የዒሻ ሰላቱን ወደ መግሪብ ማምጣት ይችላልን? መልስ፡- መንገደኛ (ሙሳፊር) ለሆነ ሰው የዙህር ሰላትን ከዐስር የመግሪብን ሰላት ደግሞ ከዒሻ ጋር አሰባስቦ መስገድ የተፈቀደ ነው። አንድ ሰው የዙህርና የዐስር ሰላትን በዙህር አሊያም በዐስር ሰዓት አሰባስቦ መስገድ ይችላል። መግሪብ እና ዒሻን በመግሪብ አሊያም በዒሻ ወቅት መስገድም ይችላል። አራት ረከዓ […]

ሱና ሶላቶች ላይ የኒያዎች መዋሃድ አለ?

ጥያቄ፡- እንደ ተሒየቱል-መስጂድ ያሉ ሱና ሶላቶችን በአዛንና በኢቃም መካከል ካሉት ሶላቶች ጋር አጣምሮ መስገድ ይቻላል? መልስ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ የገባ ሰው ከመቀመጡ በፊት ተሒየቱል-መስጂድ እንዲሰግድ አነሳስተዋል። እንዲህ ይላሉ፡- إِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمُ الْمَسْجِدَ فَلْيَرْكَعْ رَكْعَتَيْنِ قَبْلَ أَنْ يَجْلِسَ (متفق عليه واللفظ للبخاري) “እያንዳንዳችሁ መስጂድ ከገባችሁ ከመቀመጣችሁ በፊት ሁለት ረከዐ ስገዱ።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። አገላለፁ የቡኻሪይ ነው። […]

ሶላትን መርሳት እና ቀዷ መክፈል

ጥያቄ፡- ሰውየው ፈርድ ሶላትን ሳይሰግድ ረስቶ ከሁለት ቀን በኋላ እንዳልሰገደው ቢያስታውስ ምን ማድረግ ነው ያለበት? መልስ፡- ቢስሚላሂረሕማኒ-ር-ረሒም ወልሐምዱ ሊላሂ ወስ-ሶ-ላት ወስ-ሰ-ላም ዐላ ረሱሊላህ። ፊሊስጢን የሚገኘው አል-ቁድስ ዩኒቨርሲቲ የፊቅህና የኡሱሉል ፊቅህ መምህር ዶክተር ሑሳሙዲን ቢን ሙሳ ዒፋና እንዲህ ይላሉ፡- በመሰረቱ ሙስሊም ግለሰብ ሶላትን በወቅቱ ጠብቆ መስገድ ተገቢው ነው። ምክንያቱም ጥበበኛው አላህ ለሶላት ውስን ወቅት አስቀምጧል። በተመደበው […]

ስንት ረከዓ እንደሰገድኩ ተምታታብኝ

ጥያቄ:- አንድ ለሰላት የቆመ ሰው ሦስት ይሁን አራት ስንት ረከዓ እንደሰገደ እርግጠኛ መሆን ካልቻለና ከተጠራጠረ ምን ማድረግ ይኖርበታል? መልስ፡- የሸሪዓ ህግ የሚለው በጥርጣሬ ጊዜ አንድ ሰው እርግጠኛ የሆነበትን አሊያም ወደ እርግጠኛነት የቀረበበትን ነው መከተል ያለበት። በሰሂህ ሙስሊም እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም እንዲህ ብለዋል:- “ከናንተ መካከል አንዳችሁ በሰላቱ የተጠራጠረ እንደሆነ ሦስት ይስገድ አለያም አራት […]