በኢሜል (email) ኒካህ ማድረግ ይቻላል ወይ?

Home የፈትዋ ገጽ ቤተሰብ በኢሜል (email) ኒካህ ማድረግ ይቻላል ወይ?

ጥያቄ፡- በኢሜል (email) ኒካህ ማድረግ ይቻላል ወይ?


መልስ፡- መልሱን አስመልክቶ የሰሜን አሜሪካው የፊቅህ ካውንሲል ሊ/መንበር ዶክተር ሙዘሚል ሲዲቂ እንዲህ ብለዋል፡-

እንደ ሙስሊም ምሁራን አባባል ከሆነ አንድን ሰው በደብዳቤ ወይም በስልክ መዳር አይቻልም። በኢሜል ዙሪያም ይህንኑ ማለት እንችላለን። ትዳር በኢስላም ትክክለኛና ህጋዊ የሆነ ኮንትራት (ዐቅድ አሽ-ሸርዒ) ነው። ስለሆነም ማን ማንን እንደሚያገባ በግልፅ መታወቅ አለበት። ሸሪዓ ጋብቻ ይፋ እንዲሆን እፅንኦት ይሠጣል። በዚህ ላይ አንድም የተደበቀ ነገር እንዲኖር አይፈቅድም። ለዚህም ነው በኒካህ ወቅት ምስክሮች መገኘታቸው አስፈላጊ እንዲሆን የሆነው።

መጋባት የሚፈልጉ ተጣማሪዎች በቦታው የሌሉ ከሆነ ወኪል የሚሆናቸውን ሰው በመመደብ ጋብቻውን መፈፀም ይችላሉ። ማግባት የሚፈልገውም አካል ወኪሉን/ወኪሏን መመደብ ይገባዋል/ይገባታል። ወኪልን በኢሜል፣ በፋክስ ወይም በስልክ መመደብ ይቻላል። ወኪሉም የወከለውን ሰው ውክልና በመቀበል “ተቀብያለሁ (ቀቢልቱ)” ማለት ይኖርበታል። በቦታው የሌሉትን ተጋቢዎች በቅርብ የሚያውቁ ሁለት ምስክሮችም በጋብቻው ውል ላይ መኖር አለባቸው።