በኒካህ ጊዜ አንዲት ሴት ከወር አበባ ፅዱ መሆን ይኖርባታል ወይ?

Home የፈትዋ ገጽ ቤተሰብ በኒካህ ጊዜ አንዲት ሴት ከወር አበባ ፅዱ መሆን ይኖርባታል ወይ?

ጥያቄ፡- ኒካህ በሚደረግበት ጊዜ አንዲት ሴት ከወር አበባ ፅዱ መሆን ይኖርባታል ወይ ማለትም የኒካህ እና የወር አበባዋ ጊዜ ቢጋጭ ችግር አለው ወይ?


መልስ፡- ሸሪዓችን እንደሚያስተምረን ሴት ልጅ የወር አበባ ላይ እያለች አሊያም የወሊድ ደሟ ሣይቋረጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም ክልክል ነው። እንደ ሙስሊም ሊቃውንት አባባል ከሆነ ሴት ልጅን በወር አበባ ላይ እያለች መዳሩ ችግር የለውም። የተፈታች ሴት ግን የዒዳ ጊዜዋን ሣትጨርስ ማግባት የለባትም። አላህ (ሱ.ወ) በቁርዓኑ እንዲህ ብሏል

وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا عَرَّضْتُم بِهِ مِنْ خِطْبَةِ النِّسَاءِ أَوْ أَكْنَنتُمْ فِي أَنفُسِكُمْ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّا أَن تَقُولُوا قَوْلًا مَّعْرُوفًا وَلَا تَعْزِمُوا عُقْدَةَ النِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ الْكِتَابُ أَجَلَهُ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي أَنفُسِكُمْ فَاحْذَرُوهُ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ

“ሴቶችንም ከማጨት በርሱ ባሸሞራችሁበት ወይም በነፍሶቻችሁ ውስጥ (ለማግባት) በደበቃችሁት በናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ አላህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ (ስለዚህ ማሸሞርንና ማሰብን ፈቀደላችሁ፡፡) ግን በሕግ የታወቀን ንግግር የምትነጋገሩ ካልኾናችሁ በስተቀር፤ ምስጢርን (ጋብቻን) አትቃጠሩዋቸው፡፡ የተጻፈውም (ዒዳህ) ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ፡፡” (አል-በቀራህ 2፤ 235)

የተፈታችና (ነፍሠጡር ያልሆነች) የዒዳ ጊዜዋ ሦስት የወር አበባ ማየት ነው። ዒዳዋም የሚያበቃው ሦስተኛ ዙር የወር አበባ ጊዜዋ ያበቃ እንደሆነ ነው።